1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምጣኔ ሃብት ማሻሻያው በአማራ ክልል ግብይት ላይ ምን አስከተለ?

ሐሙስ፣ ነሐሴ 9 2016

በቅርቡ ተግባራዊ መደረግ የጀመረውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሙ ተከትሎ የሸቀጦች ዋጋ ማሻቀቡን በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች ነዋሪዎች አመልክተዋል፡፡ በተለይም ዶላር በገበያ ዋጋ መወሰኑ በገበያው ላይ አለመረጋጋት ፈጥሯል፡፡ የአገር ውስጥ ምርቶች ሳይቀር ዋጋቸው በማይታመን ሁኔታ ማሻቀቡን ሸማቾች በምሬት የሚናገሩት፡፡

https://p.dw.com/p/4jW9u
Äthiopien Bahir Dar | Markt
ምስል Bahir Dar/DW

የኤኮኖሚ ማሻሻያ መርሃn ግብር እና የአማራ ክልል የንግድ ሁኔታ

የኢትዮጵያ መንግስት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያና የዶላር ዋጋ በገበያ እንዲመራ ካደረገ ወዲህ የሸቀጦች ዋጋ በእጅጉ በመጨመሩ ሸማቹ ማህበረሰብ ለከፍተኛ የኑሮ ውድነት መዳረጉን በአማራ ክልል የሚገኙ ነዋሪዎች ተናግረዋል፣ የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ “ነጋዴው ማህበረሰብ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርሙን እንዲገነዘብ ስራ እየተሰራ መሆኑን ተቅሶ ያላግባብ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉት ላይ ደግሞ እርምጃ እየወሰድሁ ነው” ብሏል።

 

በኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃው ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስተያየት

በቅርቡ ተግባራዊ መደረግ የጀመረውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሙ ተከትሎ የሸቀጦች ዋጋ ማሻቀቡን በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች ነዋሪዎች  አመልክተዋል፡፡ በተለይም ዶላር በገበያ ዋጋ መወሰኑ በገበያው ላይ አለመረጋጋት ፈጥሯል፡፡  የአገር ውስጥ ምርቶች ሳይቀር ዋጋቸው በማይታመን ሁኔታ ማሻቀቡን ሸማቾች በምሬት የሚናገሩት፡፡

በባህር ዳር ከተማ የሚገኝ የገበያ ስፍራ
በቅርቡ ተግባራዊ መደረግ የጀመረውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሙ ተከትሎ የሸቀጦች ዋጋ ማሻቀቡን በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች ነዋሪዎች  አመልክተዋል፡፡ምስል Bahir Dar/DW

 

አስተያየታቸውን ከሰጡን ነዋሪዎች መካከል የጎንደር ከተማ ነዋሪ የዋጋ ንረቱ የጀመረው ገና የማክሮ ኢኮኖሚ ፕሮግራሙ ሳይተገበር “የዶላራ ዋጋ ሊጨምር ነው” ተብሉ መወራት ከጀመረ ጀምሮ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ አሁን በገበያ ውስጥ ያልጨመረ የሀገር ውስጥም ሆነ ከውጪ የሚገባ እቃ ፈልጎ ማግኘት እንደማይቻል አብራርተዋል፡፡ የቁጥጥር ስርዓቱ ደካማ መሆኑን ጣመለከቱት እኚህ ነዋሪ፣  “ዋጋ ያልጨመረ ሸቀጥ  የቱ ነው ብዬ ልንገርህ?” ሲሉ ነው የገበያውን ንረት የገለፁት፡፡

በኢትዮጵያ የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች እንዲከፈቱ መፈቀዱ

ወደፊት ከውጪ ሚገቡ እቃዎች ዋጋቸው ይጨምራል በሚል እሳቤ የሸቀጦች ዋጋ በእጅጉ ማደጉንና ኑሮ የዝቅተኛና መካከለኛ የከተማ  ነዋሪውን እየፈተነው እንደሆነ ደግሞ በሸሜን ሸዋ ዞን የሸዋሮቢት ከተማ ነዋሪ ለዶቼ ቬሌ አመልክተዋል፡፡

አንዳንድ ነጋዴዎች ዋጋ መጨመር ብቻ ሳይሆን ምርት የሚደብቁም እንዳሉ፣ የሚመለከተው አካልም የክትትልና ቁጥጥር ጉድለት አለበት ሲሉ በምዕራብ ጎጃም ዞን የደንበጫ ከተማ ነዋሪ ተናግረዋል፡፡ የዶላር ምንዛሬ በገበያ መወሰኑ ከተነገረ ጀምሮ የሸቀጦች ዋጋ በእጥፍ ጨምሯል ነው ያሉት፣ አንዳንድ ነጋዴዎችም ምርትን በመደበቅ ሂደት ላይ እንደሆኑ አስረድተዋል፣ በተለይ አካባቢው ወቅታዊ የክልሉ የሰላም ሁኔታ እንቅፋት ፈጠረበት በመሆኑ የክትትልና ቁጥጥር ስራውንም አዳክሞታል ብለዋል፡፡

የመንግስት አማካይ የዋጋ ግሽበትን ወደ 12 በመቶ የማውረድ ዕቅድ እና ተግዳሮቱ

እንደነዋሪዎቹ አስተያየት ከተማ ውስጥ ከዚህ በፊት እስከ 5 ብር ትራንስፖርት ይጠየቅበት የነበረ የከተማ ውስጥ የትራንስፖርት ታሪፍ እስከ 15 እና 20 ብር ደርሷል፡፡ በምዕራብ ጎጃም ዞን የፈረስ ቤት ከተማ ነዋሪ ከገጠር የሚመጣ ለምግብ ፍጆታ የሚውል እህል ሳይቀር የየኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ ዋጋው በመጨመሩ አብዛኛው ዝቅተኛ የከተማ ነዋሪ ሳይበላ ማደር መጀመሩን ነው የሚናገሩት፣ ወቅታዊ የፀጥታው ሁኔታ የቀን ሥራ ሰርቶ ለማደር አላስችለው ያለው ደሀ ህዝብ እየተጎዳ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡

የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያና አንደምታዎች

በምስራቅ ጎጃም ዞን የቢቸና ከተማ ነዋሪ ገበያው ሁኔታ አስፈሪ እየሆነ እንደሆነና አንዳንዱ ለልመና ሌላው ደግሞ ለቅሚያ እየተዘጋጀ እንደሆነ የወደፊቱን አስከፊ ያሉትን ሁኔታ ተናግረዋል፡፡

የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ፋንታው ፈጠነ የገበያወ መረጋጋት ለመፍጠር ሁለት ነገሮች በዋናነት እንደሚከናወኑ አብራርተዋል፣ የመጀመሪያው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርሙን ጥቅም ማስረዳትና ማስተማር፣ ከዚያ አልፎ ያልተገባ የገበያ አለመረጋጋት በሚፈጥሩት ላይ ደግሞ እርምጃ መውሰድ ነው ብለዋል፡፡

በባህር ዳር ከተማ የሚገኝ የገበያ ስፍራ
በምስራቅ ጎጃም ዞን የቢቸና ከተማ ነዋሪ ገበያው ሁኔታ አስፈሪ እየሆነ እንደሆነና አንዳንዱ ለልመና ሌላው ደግሞ ለቅሚያ እየተዘጋጀ እንደሆነ የወደፊቱን አስከፊ ያሉትን ሁኔታ ተናግረዋል፡፡ምስል Bahir Dar/DW

 

“ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በፊት በነበረው ዋጋ እንዲሸጡ ለሻጮች የግንዛቤ ማሽጨበጫ ትምህርት ሰጣቸዋል፣ ምክር ሰጣቸዋል፤ አልስተካከልም ካሉ ግን እርምጃ ይወሰዳል፣ ሱቃቸው እንዲታሸግ ደረጋል፣ ትምህርት ከተሰጡ በኋላ ይከፈትላቸዋል፣ የዋጋ ዝርዝር አውጥተውና ህዝብ በግልፅ ከሚያየው ቦታ እንዲለጥፉ ይደረጋል፣ ከዚያ ባለፈ አሁንም ያን የማያደርግ ካለ ሌሎች እርምጃዎች ይወሰዳሉ የማስተካከያ እርምጃም ተወሰደባቸው አሉ ” ነው ያሉት፡፡

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲው፤ ተስፋና ስጋቱ

ሰሞኑን ከማክሮ ኢኮኖሚው ማሻሻያ ጋር በተያያዘ ምርት የደበቁ የዶላር ዋጋ ቢጨምርም ባይጨምርም በአገር ውስጥ ምርቶች ላይ ያልተገባ ዋጋ በጨመሩ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱንም አስረድተዋል፡፡ እስካሁን በተደረገው የገበያ ማረጋጋት ከሽንኩርትና የግንባታ እቃዎች በስተቀር በአብዛኛዎቹ የክልሉ አካባቢዎች የሌሎቹ ሸቀጦች ዋጋ ወደነበረበት እየተመለሰ እንደሆነም ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

ዓለምነው መኮንን

ታምራት ዲንሳ

ኂሩት መለሰ