1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲው፤ ተስፋና ስጋቱ

ሰኞ፣ ሐምሌ 22 2016

የኢትዮጵያ መንግስት በሂደት ስመለከት ቆየሁ ያለውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራምን በትናንትናው እለት ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህ ማሻሻያ ውስጥ ዛሬ ገቢራዊ የሆነው የብር የመግዛት አቅምን በ30 በመቶ ማዳከም የማሻያው ጉልህና አነጋጋሪ እርምጃ ተደርጎ ተወስዷል፡፡

https://p.dw.com/p/4isQu
Birr - Äthiopien Währung
ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

የኢትዮጵያ የማክሮ ኤኮኖሚ ማሻሻያ አንድምታዉ ምን ይሆን ?

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲው፤ ተስፋና ስጋቱ

የኢትዮጵያ መንግስት በሂደት ስመለከት ቆየሁ ያለውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራምን በትናንትናው እለት ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህ ማሻሻያ ውስጥ ዛሬ ገቢራዊ የሆነው የብር የመግዛት አቅምን በ30 በመቶ ማዳከም የማሻያው ጉልህና አነጋጋሪ እርምጃ ተደርጎ ተወስዷል፡፡

መንግስት የማሻሻያው ዓለማ የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋትና ዘላቂነትን የሚደግፍ ዘመናዊና ጤናማ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማዕቀፍ መመሥረት፤ ፈጠራን በማበረታታት ምቹ የኢንቨስትመንትና የንግድ ዘርፍ ተወዳዳሪነት ማሳደግ ብሎም የሀገር ውስጥ ምርትና ምርታማነት ዐቅምን ማጠናከር እና ጥራት ያለው አገልግሎት ለማቅረብ የመንግሥትን ዐቅም ማሳደግ ነው ብሏል።

የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ግን የማሻሻያው የአተገባበር ሂደት ውስጥ በዜጎች ላይ የሚጥል በርካታ ተግዳሮቶች አሉ ይላሉ፡፡

በዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የጸደይ ጉባኤ ስለ ኢትዮጵያ ምን ተባለ?

የማሻሻያው አስፈላጊት

መንግስት ትናንት ይፋ ያደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሙ የውጭ ምንዛሪ መዛባትን ማስተካከል እና የረጅም ጊዜ የውጭ ክፍያ ሚዛን ጉድለትን መፍታት፣ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፉን በማዘመን የዋጋ ንረትን መቀነስ፣ የዕዳ ተጋላጭነትን በመፍታት እና የሀገር ውስጥ ገቢን በማሳደግ ሀገራዊ የልማት ፍላጎቶትን በሀገር ውስጥ ዐቅም ለማሳካት ምቹ መደላድል በመፍጠር የፋይናንስ ዘርፉን ጤናማነት ማጠናከርና የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል ቁልፍ ዓላማና ግቦቹ መሆኑን አትቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ
መንግስት ትናንት ይፋ ያደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሙ የውጭ ምንዛሪ መዛባትን ማስተካከል እና የረጅም ጊዜ የውጭ ክፍያ ሚዛን ጉድለትን መፍታት፣ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፉን በማዘመን የዋጋ ንረትን መቀነስ ታላሚ አድርጓልምስል Seyoum Getu/DW

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲሱ ገዥ ማሞ ምኅረቱ ምን ይጠብቃቸዋል?

በዚህ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ በገበያ ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓትን መዘርጋት አንዱና ዋነኛው ተደርጎ ቀርቧልም፡፡

የማሻሻያው መጠበቅና አስገዳጅ ሁኔታው

የምጣኔ ሃብት ተመራማሪው ዶ/ር ደግዬ ጎሹ ይህኛው የመንግስት እርምጃ ዋነኛው ማጠንጠኛው የብድር ቅድመ ሁኔታ ማሟያ እንደመሆኑ ረዘም ያለ ድርድር ስደረግበት የነበረውና ስጠበቅም የነበረ ነው ብለውታል፡፡ ነገር  ግን የማሻሻያው ወቅታዊነት ላይ ጥያቄ አንስተዋል፡፡ “የማሻሻያው ማጠንጠኛ የብድር ቅድመ ሁኔታ በማመቻቸት ያንኑን ማግኘት ነው” የሚሉት የምጣኔ ሃብት ባለሙያው መንግስት በዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው በአበዳሪዎች ጫና መሆኑን አስረድተዋል፡፡ “መንግስት የልማት እቅዶቹን ለመፈጸም ምንም አማራጭ አለመኖሩ መሰል ሪፎርም እንዲጠበቅ ብያደርግም ጊዜው አሁን አይደለም” ብለዋልም፡፡

የኢትዮጵያ የኤኮኖሚ አካሄድ

ሪፎርሙ የተገበረበት ጊዜ ትክክለኛነት

ለዚህም ምክንያት ብለው ያቀረቡት፤ “የማክሮ ኢኮኖሚ አለመመጣጠን ባለበት ሁኔታ መሰል ትልልቅ ሪፎርሞችን ማካሄድ መዛባቱን ያባብሳል” የሚለውን ሃሳብ ነው፡፡ ለዚህም ማሳያ ስሰጡ ከጎርጎሳውያኑ 2015 ጀምሮ እስከ ባለፈው 2023 ድረስ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የሚያመነጨው ምርት በ35 በመቶ መቀነሱን ነው፡፡ የሰሞነኛው የዋጋ መረጋጋት መስተዋልም ከመዋቅራዊ ችግሮች መፈታት ሳይሆን ከዜጎች የመግዛት አቅም ማሽቆልቆል ጋር አያይዘውታል፡፡

የኢትዮጵያ ብር ከወቅቱ ገበያ አንጻር
ማክሮ ኢኮኖሚ አለመመጣጠን ባለበት ሁኔታ መሰል ትልልቅ ሪፎርሞችን ማካሄድ መዛባቱን ያባብሳል” ባለሞያምስል Eshete Bekele/DW

የኢትዮጵያ የኤኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ-ግብር የሚያስከፍለው ዋጋ በማን ላይ ይበረታል?

የማሻሻያው ጥቅምና ተግዳሮቱ

ማሻሻያው በአጭርም ሆነ በረጅም ጊዜ የሚያመጣው ፋይዳና ተግዳሮት መኖሩን ባለሙያው አልሸሸጉም፡፡ ነገር ግን ተግዳሮቱ ሳይከፋ አይቀርም የሚል ምልከታቸውን አጋርተዋል፡፡ “ጥቅሙ መንግስት የውጪ ምንዛሪን በበቂ ሁኔታ በማግኘት የልማት ውጥኖቹን እንዲያሳካበት ይረዳዋል፡፡ ከዚህ በፊት የነበረው የብድር ሁኔታ ክምች ላይም ማስተካከያ እንዲደረግ ይረዳል” በማለት ጥቅሞቹን ጠቃቅሰዋል፡፡ ጉዳቱም ግን የከፋ ነው ያሉት ባለሙያው፤ “የማክሮ ኢኮኖሚው ማሻሻያ በየደረጃው መደረግ ስኖርበት በአንዴ የተደረገው ማሻሻያው የዋጋ ግሽበትን ማባባስ፣ አሁን ባለው የግጭት ሁኔታ የታለመውን የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ማሻሻል እና ምርታማነት ማሳደግ ላይ ጥያቄ የሚጭር በመሆኑ በታለመለት ደረጃ መሄዱ አጠራጣሪ ነው” የሚለውን ምልከታቸውን ጠቁመዋል፡፡ ሪፎርሙ ስላለው አሁናዊ የጸጽታ ተግዳሮት ምንም አለማለቱ እንዳስገረማቸውም አንስተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከፊል ገጽታ
ሻሻያው በአጭርም ሆነ በረጅም ጊዜ የሚያመጣው ፋይዳና ተግዳሮት መኖሩን ባለሙያው አልሸሸጉም፡፡ ነገር ግን ተግዳሮቱ ሳይከፋ አይቀርም የሚል ምልከታቸውን አጋርተዋል፡፡ምስል Seyoum Getu/DW

ሃገር በቀል የኤኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ ግብር

ትናንት ይፋ የተደረገው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ በባንክ በ57 ብር ገደማ ስሸጥ የነበረው አንድ የአሜሪካ ዶላር በአንድ ጀንበር ዛሬ ዋጋው ከ74 ብር ተሻግሯል፡፡  የአሜሪካ መንግስት ይህን የኢትዮጵያን ውሳኔ በመደገፍ ውሳኔው የበለጠ ነፃ እና ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት ይረዳል ብሏል፡፡ ለዚህም ድጋፉን ችሯል፡፡ አሜሪካ የተደረገው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ተግባራዊ እንዲሆንም ከልማት አጋሮች ጋር በመሆን ድጋፍ እንደምታደርግ አረጋግጣለች፡፡

ሥዩም ጌቱ

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሰ