1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያና አንደምታዎች

ዓርብ፣ ነሐሴ 3 2016

የውጭ ሚዛን ማስተካከያ ዘዴዎቹ የሃገሪቱን የገንዘብ ዋጋ መቀነስ ወይም ዲቫልዩ ማድረግ መሆኑን የተናገሩት የምጫኔ ሀብት ባለሞያው ፕሮፌሰር ወርቁ አበራ ኢትዮጵያግን ለአንድ ጊዜ ብቻ የብሩን ዋጋ በመቀነስ ፋንታ በገበያ እንዲመራ መወሰኗን ገልጸዋልውጤቱም ፣በይበልጥ የሚጎዳው ተራውን ሕዝብ፣መጠነኛ ደመወዝ ያለውንና ጡረተኞችን ነው ብለዋል።

https://p.dw.com/p/4jIDQ
Äthiopien | Marktplatz in Addis Abeba
ምስል Solomon Muchie/DW

የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ አንደምታዎች

 

ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ጋር ስታደርግ ከነበረው ድርድር በኋላ፣ የውጭ ምንዛሪ ግብይቷ በገበያ እንዲወሰን አድደርጋለች። ዓለም ዓቀፍ የገንዘብ ድርጅቶችመቀመጫቸውን ዋሽንግተን ዲሲ ካደረጉት፣የዓለም አቀፉ የገንዘብ ፈንድ/አይኤኤምኤፍ/ እና የዓለም ባንክ ብድር ለማግኘት እንደ ቅድመ ሁኔታ የሚቀመጡ፣የመዋቅር ማሻሻያ ፕሮግራሞች አከራካሪነታቸው እንደቀጠለ ነው። እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች፣ አንድን ተበዳሪ አገር፣የመንግስት ወጪ እንዲቀንስ አሊያም የወለድ ተመኖችን እንዲያሳድግ እስከመጠየቅ የሚደርሱ ናቸው።

የመዋቅር ማሻሻያ መርሐግብሮቹ፣የምዕራቡን ዓለም የኒዮሊበራል ርዕዮተዓለም ወይም የነጻ ገበያ የኢኮኖሚ ልማት ፕሮግራም፣ግብር ላይ እንዲውሉ በማድረግ፣ በማደግ ላይ በሚገኙ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገሮች ውስጥ ያለውን የመንግስት የኢኮኖሚ ተሣትፎ እንዲቀንስ ያደርጋሉ። በአይኤምኤፍ ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ተቺዎች ጭምር፣ ይህ የድርጅቱ አካሄድ፣ድኻዎችን የሚጎዳ ነው በሚል እንደሚያሳስባቸው፣አማንዳ ብሩስክ የተባሉ ደራሲ፣ የማኀበራዊ ፖሊስ መሠረቶችን በሚያትተው መጽሐፋቸው ላይ አስነብበዋል።መንግሥት ያደረገውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ እንዲሠርዝ መጠየቁ

እነዚሁ ተቺዎች የሚሉት፣ይህ የድርጅቱ አካሄድ፣በማኀበራዊ አገልግሎቶች ማለትም፣በትምህርት እና ጤና አጠባበቅ በመሳሰሉ መሰረታዊ ኢንቨስትመንቶች ላይ የመንግስት ተሳትፎን በመቀነስ የረጅም ጊዜ የምጣኔ ሃብት ልማት አደጋ ላይ ይጥላል ነው።አሕመድ

የምጣኔ ኃብት ምሁሩ ዕይታ

ዶይቸ ቨለ ያነጋገራቸው፣ የምጣኔ ኃብት ምሁሩ፣ ፕሮፌሰር ወርቁ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገሮች የመንግስት ተሣትፎ አስፈላጊነትን እንደሚከተለው ያስቀምጡታል።" የመንግስት ጣልቃ ገብነት፣በመንግስት ውስጥ ችግር ይፈጥራል የሚል ርዕዮተዓለም የሚከተሉ ግለሰቦችና  ድርጅቶች የሚያፈልቁት ዐሳብ ነው እንጂ ከኢኮኖሚ አንጻር ስንመለከተው፣ መንግስት በኢኮኖሚ መሳተፉ ኢኮኖሚውን ይጠቅመዋል እንጂ አይጎዳውም።"

Prof Worku Abera
ፕሮፌሰር ወርቁ የምጣኔ ኃብት ምሁሩ፣ ምስል Privat

አይኤምኤፍና የዓለም ባንክ የድህነት ቅነሳ ግብ ይዘው ይነሱ እንጂ፣ በተግባር እንደሚታየው ከሚሰጡት ብድር ጋር የሚያቀርቡት ፖሊሲ፣ የዋጋ ግሽበት በማስከተል የድኻ ዜጎችን ህይወት የሚያከብድ እንደሆነ ፕሮፌሰር ወርቁ ይናገራሉ።የውጭ ምንዛሪ በገበያ እንዲመራ ከተወሰነ ወዲህ ገበያው ምን ይመስላል?

"መንግስት የሚሰጣቸው ድጎማ ይቀንሳል፤ በሌላ በኩል ደግሞ የሚከፍሉት ታክስ ይጨምራል። ስለዚህ የእነሱ የኑሮ ደረጃ በጣም ዝቅ ሊል ይችላል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የውጭ የንግድ ሚዛን መስተካከል አለበት ይባላልና የውጭ ሚዛን ለማስተካከል መደረግ ያለበት ምንድነው በሚባልበት ጊዜ፣አንዱ ዘዴ የሃገሪቱን የገንዘብ ዋጋ መቀነስ ወይም ዲቫልዩ ማድረግ ነው ይባላል እና ኢትዮጵያ ውስጥ የተወሰደው እርምጃ እሱ ነው። ለአንድ ጊዜ ብቻ የብሩን ዋጋ በመቀነስ ፋንታ በገበያ ይወሰን የሚል ውሳኔ ነው የተወሰነው፤የርዕዮተዓለም ምንጩ ይሄ ነው።ውጤቱ በአጠቃላይ ስንመለከተው፣በይበልጥ የሚጎዳው ተራው ሕዝብ፣መጠነኛ ደመወዝ ላይ የሚኖረውን ጡረታ የወጡ ግለሰቦችን ነው የበለጠ የሚጎዳው ማለት ነው።"የኢትዮጵያ የኤኮኖሚ ማሻሻያ “ቆንጠጥ የሚያደርግ ሆኖ ማስተካከል ይጠይቃል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

የማሻሻያው የምጣኔ ኃብት ሥርጭት 

ማሻሻያው አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ወገኖች የሚጎዳ ቢሆንም የሚጠቅማቸው የኅብረተሰቡ ክፍሎች እንዳሉ የተናገሩት የምጣኔ ኃብት ምሁሩ፣ የሚያስከትለውን የኢኮኖሚ ስርጭት ውጤት እንደሚከተለው አብራርተዋል።"ገበያውን የመቆጣጠር ችሎታ ያላቸው፣ ባለሀብቶች ነጋዴዎች፣ጅምላ አከፋፋዮች የመሣሰሉት፣ ከውጪ የመጣውን ዕቃ ከሚገባው በላይ በመጨመር ዋጋውን፣ትርፍ ሊያተርፉ ይችላሉ።ውጤቱ ምንድነው ቢባል፣ሃገሪቱ ውስጥ  ያለውን ሀብት የማንሸራሽር ዝንባሌ፣ ከዳኻው ወደ ሀብታሙ የማስተላለፍ ሁኔታ ይፈጥራል ማለት ነው።"ብለዋል።

ታሪኩ ኃይሉ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ