1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«ፖሊሲ የማውጣት ሉዓላዊነትን የሚገድብ ማሻሻያ ውጤቱ ቀውስ ጋባዥ ትርፉም ሀገራዊ ዕዳ ነው»

ሐሙስ፣ ሐምሌ 25 2016

ኢዜማ "የገንዘብ ፖሊሲን ጨምሮ አጠቃላይ ሀገራዊ የምጣኔ ሀብት እድገትን በሚመለከቱ ጉዳዮች መንግሥት በቀጥታ እና በንቁ ሁኔታ ጣልቃ መግባት ካልቻለ ከጥልቅ ድኅነት መውጣትም ሆነ ማኅበራዊ ፍትሕን ማረጋገጥ እንደማይቻል" በጽኑ እንደሚያምን በመግለጫው ገልጿል። ሌሎች ፓርቲዎች ውሳኔው በጊዜ ሂደት አደገኛ ያሉትን ውጤት እንደሚያስከትል አሳስበዋል።

https://p.dw.com/p/4j16u
Äthiopien | Geldscheine Währung
ምስል MICHELE SPATARI/AFP

በኢትዮጵያ የኤኮኖሚ ማሻሻያ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስተያየት

በኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃው ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስተያየት

የኢትዮጵያ መንግሥት በዚሁ ሳምንት መጀመርያ ይፋ ያደረገውን የኢኮኖሚ ማሸሻያ ተከትሎ "በሀገር እና በሕዝብ ላይ ለሚደርስ የምጣኔ ሐብት፣ የማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ምስቅልቅል ሙሉ ኃላፊነቱን ይወስዳል" ሲል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ገለፀ። ኢዜማ "ፖሊሲ የማውጣት ሉዓላዊነትን የሚገድብ ማሻሻያ ውጤቱ ቀውስ ጋባዥ፣ ትርፉም ሀገራዊ ዕዳ ነው" በሚል 
ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ በውጭ አበዳሪዎች የፖሊሲ ጫና የብር የመግዛት አቅም በገበያ እንዲወሰን ተደርጓል። ብሏል።በጉዳዩ ላይ በቀጣዩ ሳምንት መግለጫ እንደሚሰጡ የገለፁ ፓርቲዎች ውሳኔው በጊዜ ሂደት አደገኛ ያሉትን ውጤት እንደሚያስከትል ገልፀዋል። መንግሥት እንደሚለው ግን ማሻሻያው "በከፍተኛ ጥንቃቄ የተዘጋጀ" እና ዘላቂ ሀገራዊ ጥቅም ያለው ነው።የኢትዮጵያ የኤኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ-ግብር የሚያስከፍለው ዋጋ በማን ላይ ይበረታል?

የኢዜማ መግለጫ ዝርዝር ምን ይላል?

ኢዜማ "የገንዘብ ፖሊሲን ጨምሮ አጠቃላይ ሀገራዊ የምጣኔ ሀብት እድገትን በሚመለከቱ ጉዳዮች መንግሥት በቀጥታ እና በንቁ ሁኔታ ጣልቃ መግባት ካልቻለ ከጥልቅ ድኅነት መውጣትም ሆነ ማኅበራዊ ፍትሕን ማረጋገጥ እንደማይቻል" በጽኑ እንደሚያምን በመግለጫው ገልጿል።

መንግሥት ያለበትን "ሥር የሰደደ" ያለውን የውጭ ምንዛሪ ችግር ለመፍታት ሲል ተግባራዊ እንዳያደርግ ውትወታ አድርጌበታለሁ ያለው የብርን የመግዛት አቅም በገበያ እንዲወሰን የማድረግ ጉዳይ በውጭ አበዳሪዎች የፖሊሲ ጫና እውን መሆኑንም ፓርቲው አስታውቋል። በፓርቲው የትይዩ ካቢኔ ፀሐፊ አቶ ንጋቱ ወልዴ ይህንኑ ገልፀዋል።

የኢዜማ አርማ
የኢዜማ አርማምስል Yohannes G/Egziabher/DW

የኢትዮጵያ የኤኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ-ግብር የሚያስከፍለው ዋጋ በማን ላይ ይበረታል?እርምጃው የዋጋ ንረትን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያባብስ፣ ለጊዜው ማስታገሻ ከመሆን ባለፈ ችግሩን በዘላቂነት ሊፈታ የሚችል የመፍትሔ ሐሳብ አለመሆኑንም ፓርቲው አመልክቷል።

በሀገር ውስጥ ምርት ራስን መቻል ባልተረጋገጠበት፣ ምርታማነትን የሚያበረታታ የፀጥታ ሁኔታ በሌለበት፣ በውጭ ግብአት ላይ ከፍተኛ ጥገኛ የሆነ የምጣኔ ሀብት ባለበት ይህንን ማድረጉም ተገቢ አለመሆኑም በአስረጂነት ተጠቅሷል። ውሳኔውን ተከትሎ ለሚከሰት ችግር ሙሉ ኃላፊነቱ የመንግሥት እንደሚሆንም ፓርቲው አቋሙን ይፋ አድርጓል።

በጉዳዩ ላይ በቀጣዩ ሳምንት መግለጫ እንደሚሰጡ የገለፁ ፓርቲዎች ውሳኔው በጊዜ ሂደት አደገኛ ያሉትን ውጤት እንደሚያስከትል ገልፀዋል።የኢትዮጵያ የኤኮኖሚ ማሻሻያ “ቆንጠጥ የሚያደርግ ሆኖ ማስተካከል ይጠይቃል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ "የማክሮ ኢኮኖሚ ለውጡን በቁንጽል ሳይሆን በምልዐት መመልከት ይገባል" ሲሉ ዛሬ ጽፈዋል። አክለውም "አላማችን የኢትዮጵያን ብልጽግና ማረጋገጥ፣ አካኼዳችን ድኻ ተኮር፣ ትኩረታችንም ለችግር በመጠቃት ተጋላጭ የሆኑ ደካሞችን መደገፍ ነው"። ብለዋል። የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ ትናንት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት መብራሪያ ማሻሻያው "በከፍተኛ ጥንቃቄ የተዘጋጀ" እና ዘላቂ ሀገራዊ ጥቅም ያለው ነው።

ሰሎሞን ሙጬ

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ