1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካእስያ

ዩክሬን በአፍሪቃ ተሰሚነት ለማግኘት የምታደርገው ጥረት

ቅዳሜ፣ ሰኔ 22 2016

ሶቭየት ኅብረት ስትፈረካከስ ነጻ በወጣችው በዩክሬን የ32 ዓመታት ዲፕሎማሲያዊ ታሪክ አንድ የዩክሬን ፕሬዝዳንትም ሆነ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪቃ ሀገራትን ጎብኝቶ አያውቅም። አሁን ግን ይህ ቀስ በቀስ እየተቀየረ ነው። በሌላ በኩል ሩስያ በግንቦት ወር በአፍሪቃ ተጨማሪ 4 ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮዎችን ለመክፈት ዝግጅት ላይ መሆንዋን አስታውቃለች።

https://p.dw.com/p/4hf8z
የዩክሬን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲሚትሪ ኩሌባ በግንቦት 2015 ዓ.ም.አዲስ አበባ ውስጥ መግለጫ ሲሰጡ
የዩክሬን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲሚትሪ ኩሌባ በግንቦት 2015 ዓ.ም.አዲስ አበባ ውስጥ መግለጫ ሲሰጡ ምስል ASSOCIATED PRESS/picture alliance

ዩክሬን በአፍሪቃ ተሰሚነት ለማግኘት የምታደርገው ጥረት

በርካታ የአፍሪቃ ሀገራት ከቀድሞዋ ሶቭየት ኅብረት ዘመን አንስቶ ከሩስያ ጋር ጥልቅ ታሪካዊ ግንኙነት አላቸው። ሶቭየት ኅብረት ለአንዳንዶቹ ሀገራት የትጥቅ ትግል ድጋፍ ስታደርግ የነበረች  ሀገርም ናት።    ዩክሬን ግን ከአፍሪቃ ሀገራት ጋር ይህን መሰል የቅርብ ግንኙነት የላትም።  በዚህ የተነሳም ዩክሬን አሁን ከአፍሪቃ ሀገራት ጋር ግንኙነቷን ለማጥበቅ አንድ ብላ መንቀሳቀስ ጀምራለች። ዩክሬን ፣ሞስኮ በአፍሪቃ ያላትን ተጽእኖ ለመቀነስ ዲፕሎማሲያዊ እና ስልታዊ እንቅስቃሴዎችን እያካሄደች ነው። ዓላማዋም በአፍሪቃ የሩስያን ፕሮፓጋንዳን እና ወታደራዊ ተሳትፎዎች ማዳከም ነው። ዶቼቬለ ያነጋገራቸው የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኝ ሊያ ኩሳ እንዳሉት የከዚህ በፊቱ የዩክሬን አካሄድ የተሳሳተ ነበር። ስህተቷም በአፍሪቃ የሶቭየት ኅብረት ውርስ አካል መሆንዋን ለማሳወቅ አለመሞከርዋ ነው። 
« ዩክሬን የሶቭየት ውርስ አካል ነኝ ማለቱ አልተሳካላትም። ይህ ደግሞ የስልት ስህተት ነው። ዩክሬን የታሪኩ አካል መሆንዋን ለማሳወቅ አልሞከረችም።ምክንያቱም በርካታ ዩክሬናውያን የሶቭየት ኅብረት አካል ሆነው በመላ አፍሪቃ መሐንዲሶች ቴክኒሽያኖች መምህራን እና ሐኪሞች ነበሩ። » ዩክሬን ከአፍሪቃ ሃገራት ጋር ለመተሳሰር የጀመረችው ጥረት
በኩሳ እምነት ዘመናዊቷ ዩክሬን በተለይም ከሩስያ ወረራ በኋላ ከሶቭየት ኅብረት የቀድሞ ታሪክ ጋር የሚያገናኛትን ነገር አትፈልግም። የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንም ከ10 ዓመት አካባቢ አንስቶ ነበር ከአፍሪቃ ጋር ግንኙነቱን እንደገና ማጠናከር የጀመሩት። መደበኛ ወታደራዊ ድጋፍ ከመስጠት አንስቶ በተቀናቃኝ የፖለቲካ መሪዎች ላይ የተሳሳተ መረጃ የመስጠት ዘመቻዎችን ነበር የሚያካሂዱት። ከጦርነቱ በፊት ዩክሬን በአፍሪቃ ሀገራት አስር ኤምባሲዎች ብቻ የነበሯት ሲሆን በአንጻሩ ሩስያ በ43 የአፍሪቃ ሀገራት ኤምባሲዎች አሏት። ይህን ሰፊ ልዩነት ለማጥበብ ዩክሬን አሁን ጥረቷን አጠናክራለች ይላሉ ኩሳ
« ለዚህ ነው ጦርነቱ ሲጀመር አገራችን ከአፍሪቃ አገራት ጋር ግንኙነቷን ወደ ማሻሻል የሄደችው ።ሌሎች አገራት እንደሚያስፈልጉን እንረዳለን። ከሩስያ ጋር ከምናካሂደው ጦርነት ጋር በተያያዘ
አቋማችንን እንድናሻሻል ውይይት ለመጀመር ሌሎች ምዕራባውያን ያልሆኑ ሀገራት ያስፈልጉናል። »ናይጀሪያዊው ዲፕሎማት ኦቤግዌ ኤጉኦጉ በሰጡት አስተያየት ዩክሬን በአፍሪቃ ይህን ነው የሚባል  ዲፕሎማሲ ታሪክ  የላትም። ይህንንም በየካቲት 2014 ዓመት የተጀመረው የሩስያ ዩክሬን ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆም ለተመድ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ የ28 የአፍሪቃ ሀገራት ድጋፍ ሲያገኝ 17ቱ ድምጻቸውን አቅበው 7ቱ ደግሞ መቃወማቸው ያረጋግጣል።ከዚህ በኋላ ነው ዩክሬን በተመድን ጠንካራ አቋም እንዲኖራት አፍሪቃን መያዝ በጣም አስፈላጊ መሆኑን የተገነዘበችው።

የአፍሪቃ መሪዎች ዩክሬን ቡቻ ውስጥ የጅምላ መቃብር በሚገኝበት ስፍራ አቅራቢያ ያለ ቤተ ክርስቲያን ሲጎበኙ
የአፍሪቃ መሪዎች ዩክሬን ቡቻ ውስጥ የጅምላ መቃብር በሚገኝበት ስፍራ አቅራቢያ ያለ ቤተ ክርስቲያን ሲጎበኙምስል Valentyn Ogirenko/REUTERS

የዩክሬን የሲቪል ማኅበረሰብ አባላት በኢትዮጵያምክንያቱም  በተመድ የአፍሪቃ ድምጽ ትልቁን ስፍራ የሚይዝ ነው። ሶቭየት ኅብረት ስትፈረካከስ  ነጻ በወጣችው በዩክሬን  የ32 ዓመታት ዲፕሎማሲያዊ ታሪክ አንድ የዩክሬን ፕሬዝዳንትም ሆነ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪቃ ሀገራትን ጎብኝቶ አያውቅም። አሁን ግን ይህ ቀስ በቀስ እየተቀየረ ነው።  በሌላ በኩል ሩስያ በግንቦት ወር በአፍሪቃ ተጨማሪ 4 ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮዎችን ለመክፈት ዝግጅት ላይ መሆንዋን አስታውቃለች ።ይህም በአፍሪቃ ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮዎች ቁጥር ወደ 47 ያሳድገዋል።  ሌላው ዩክሬን በአፍሪቃ ተጽእኖዋን ለማጠናከር  የምትሞክርበት መንገድ የምግብ ዲፕሎማሲ ነው።

የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በሩስያ ጉብኝታቸው ወቅት ከሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ሲነጋገሩ
የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በሩስያ ጉብኝታቸው ወቅት ከሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ሲነጋገሩምስል AP

ከጦርነቱ በፊት ዩክሬን ለአፍሪቃ በቆሎ በማቅረብ ሁለተኛ ደረጃ የምትይዝ አገር ነበረች። በስንዴ አቅራቢነት ደግሞ የመጀመሪያውን ቦታ ትይዛለች። ከዚህ ሌላ ዩክሬን ለናይጀሪያ ለኢትዮጵያና ለኬmneያና ሶማሊያ የስንዴ እርዳታም ሰጥታለች። በተመሳሳይ መንገድ ሩስያም ለአፍሪቃ እህል በነጻ አቅርባለች። የሩስያን የእህል እርዳታ ከተቀበሉት መካከል ቡርኪና ፋሶና ማሊ ይገኙበታል።የአፍሪካ ልዑካን የሞስኮና ኪዬቭ የሰላም ጥረትያም ሆኖ ዩክሬን አሁንም ከአፍሪቃ ሀገራት የምትፈልገውን ድጋፍ ማግኘት አልቻለችም።ይህ የሆነበት ምክንያት ኤጉኡጉ  እንዳሉት የዩክሬን ዲፕሎማሲያዊ መልዕክት ባጋጠመው ችግር ነው።ይህ የሆነውም ፣በበርካታ የአፍሪቃ ሀገራት ተዓማኒነታቸውን ባጡት በምዕራባውያን ሀገራት ምክንያት ድምጿ በመሸፈኑ እና ለዩክሬን ድምጽ ሆነው  የሚናገሩትም በአፍሪቃ እንደቀድሞው ተሰሚ ባለመሆናቸው ነው። 

ኂሩት መለሰ 
ነጋሽ መሐመድ