1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪካ ልዑካን የሞስኮና ኪዬቭ የሰላም ጥረት

ሰኞ፣ ሰኔ 12 2015

አስር ነጥቦችን ያካተተው የሰላም ዕቅድ፤ በዋናነት የአገሮች ሉዑላዊነት መከበር ያለበት መሆኑን፣ ማንኛውም አገር የደህንነት ዋስትና ሊኖረው እንደሚገባ፣ የሸቀጥና እህል ንግዶች ዝውውር ሊደናቀፍ የማይገባው መሆኑን በመሰረታዊነት ያካተተ ነው

https://p.dw.com/p/4SlvL
Afrikanische Delegation zu Besuch in Russland
ምስል AP

የአፍቃ መሪዎች የሰላም ጥረት

በደቡብ አፍርካው መሪ ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፉዛ የሚመራ የአፍርካ መሪዎች የሰላም ቡድን በሳምንቱ መጨረሻ በኪይቭና ሞስኮ በመገኘት 16 ወራት የዘለቀውን የሩስያና  ዩክሬን ጦርነት የሚያበቃበትን የሰላም ሀሳብ ለፕረዝዳናት ዘለንስኪና ፕሬዝዳንት ፑቲን አቅርበዋል።
በሁለቱ አገሮች እየተካሄደ ያለው አውዳሚ ጦርነት እንዲቆምና በአካባቢው ሰላም እንዲሰፍን የሚያስችሉ የተለያዩ የሰላም ዕቅዶች በተለያዩ አገሮች በግል ቀርበው የንበር ቢሆንም፤ ይኸኛው ግን  በሰባት የአፍርካ መሪዎች በጋራ የቀረበና የአህጉሩንም ስሜትና ፍላጎት የሚያንጸብርቅ በመሆኑ በአንድንዶች የተለየ ተደርጎ ተወስዷል።
የዛምቢያ፣ ኮሞሮስ፣ ኮንጎ፤ ኡጋንዳ፤ ሴነጋልና ግብጽ መሪዎችና ወኪሎቻቸው የሚገኙበት የአፍሪካ የሰላም ቡድን የተመራው በደቡብ አፍርካው ፕሬዝድንት ሲሪል ራማፉዛ ሲሆን፤ የሰላም ዕቅዱንም በመጅመሪያ ዓርብ ዕለት በኪየቭ ለፕረዝዳንት ዜለንስኪና ባማግስቱ ቅዳሜ ደግሞ በሳንትፒተርስበርግ ከተማ ለፕሬዝድንት ፑቲን ዓቅርቧል።
 አስር ነጥቦችን ያካተተው የሰላም ዕቅድ፤ በዋናነት የአገሮች ሉዑላዊነት መከበር ያለበት መሆኑን፣ ማንኛውም አገር የደህንነት ዋስትና ሊኖረው እንደሚገባ፣ የሸቀጥና እህል ንግዶች ዝውውር  ሊደናቀፍ የማይገባው መሆኑን በመሰረታዊነት ያካተተ ነው።፡፤ የጦር እስረኞች መፈታት፣ የሰባዊ እርዳታ መተላለፍና የፕሬዝድንት ፑቲን የወንጀል ክስ መነሳት የመሳሰሉትም ለሰላም ውይይቱ እንደቅድመ ሁኒታ የቀረቡ መሆናቸው ተገልጿል። 
መሪዎቹ ዓርብ እለት ለፕሬዝዳንት ዘለንስኪ የሰላም ሀስቡን ሲያቀርቡ፤ በሳቸውና በሉዕካቸው የቀረበው የሰላም ሀስብ፤ የዩክሬን መንግስት   ያቀረበውን የሰላም ዕቅድ ከግምት  ውስጥ ያስገባ መሆኑን ጠቅሰው፤ ጦርነቱ መቆም እንዳለበት ቡድናቸው አጥብቆ እንደሚያምን አስታውቀዋል። “ ይህ ጦርነት በድርድርና ዲፕሎማሲ አማካይነት መቆም ይኖርበታል፤ አሁን ያለው የጦርነት ስሜትም መብረድ ይኖርበታል” በማለት ይህ እንዲሆን የቡድናቸው ፍላጎት መሆኑን አስታውቀዋል። ፕረዝዳንቱ ሁለቱ አገሮች የእህልና ማደባሪያ  ዝውውር እንዳይስተጓጎል ዋስትና መስጠት ያለባቸው መሆኑን በማሳሰብም፤ አፍሪካ በጦርነቱ ዋጋ እየከፈለ እንደሆነንና አንዱ ቡድናቸው ወደ እዚህ የመጣበት ምክኒይትም ይህን ለመግለጽ ጭምር መሆ አክለው አስታውቀዋል።
ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ግን የሩሲያ ወታደሮች በዩክሬን ምድር ላይ ሆነው ድርድር የማይታሰብ መሆኑን በመግለጽ፤ መሪዎቹ ከቻሉ የጦር እስረኖች ልውውጥን እንዲያመቻቹ ነበር ያሳሰቡት።
በማግስቱ በሴንትፒተርስበርግ የተገኙት የአፍርካ መሪዎች ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር ባደረጉት ውይይትም፤ የሰላም ዕቅዳቸው ከሌሎች የሰላም ዕቅዶች ጋር የማይቃረን መሆኑን በመጥቀስ፤ ይህ ጦርነት በድርድር መቆም እንዳለበት በጽኑ የሚያምኑ መሆኑን  ፕሬዝዳንት ራማፉዛ አጥብቀው አሳስበዋል፤ “ ሁልጊዜ በጦርነት መቆየት አይቻልም። ሁሉም ጦርነቶች አንድ ወቅት ሊቆሙና ሰላም ሲሰፍን የግድ ነው” በማለት እዚህ የመጡት ይህን መልእክት በግልጽ ለማስተላለፍ መሆኑን ገልጸዋል። 
ፕሬዝዳንት ፑቲን፤ በቅድሚያ መሪዎቹ ለችግሩ ትኩረት ሰጥተው ያቀረቡትን የሰላም ሀሳብ የሚያደንቁ መሆኑን በመግለጽ፤ ውይይትና ድርድርን የማትቀበለው ግን ዩክሬን ናት በማለት በበኩላቸው የቀረበውን ሀሳብ እንድሚያጤኑትና፤ ያም ሆኖ ግን፤ ማንኝውም የሰላም ሀሳብ አዲሱን የአካባቢውን እውነታ ያጤነና የተቀበለ መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል።  የእህልና ማዳበሪያ እጥረትን በሚመለከት ግን በተደርሰው ስምምነት መሰረት  በጥቁር ባህር  እንዲተላለፍ ከተደረገው  የእህል መጠን  አፍሪካ የደረሰው 3 ከመቶ ብቻ እንደሆነና ሌላው  በምራባውያኑ አገሮች እንዲቀር እንድተደረገ በመግለጽ እጥረቱ የተባባሰበት ምክንያት ነው ያሉትን አብራርተዋል።
መሪዎቹ በሁለቱም ከተሞች በተገኙባቸው ወቅቶች ጦርነቱ እንዳልቆመና እንዲያውም ተጠናክሮና በስፋት እንደቅጠለ ነው ።
ወደ የአገሮቻቸው የተመለሱት የሰላም ቡድኑ አባላት ግን  ተልኳቸው  አሁኑኑ ሰላም ያመጣል ብለው እንዳላሰቡና የተደርጉት ግንኙነቶችና ውይይቶች ግን ጠቃሚዎች እንደሆኑ ነው በተለያዩ ዝዴዎች ሲገልጹ የተሰሙት። የሰላም ቡድኑ ተልዕኮ በትልቁ በዩክሬን ለግዜው ሰላም ባያምጣም፤  በሚቀጥሉት ተከታታይ ወራት የሚክሄዱት የአፍሪካና  ሩሲያ፤  እንዲሁም  ደቡብ ፍሪካ የምታስተናግደው የብሪክስ ጉባኤዎች የተሳኩ እንዲሆኑ በማድረግ በኩል ግን ስኬትማ መሆኑን በፕሪቶሪያ  ዩንቨርስቲ ፕሮፊሰር የሆኑት ሚስተር ጃኬ ሲሊየርስ ይናገራሉ፤ “ የመጀመሪያው የብሪክስና የአፍርካና ሩስያ ጉባኤዎች የተሳኩ እንዲሆኑ ሊረዳ  ይችላል። በኪይቭናን ሴንት ፒተርስ በርግ የተደረጉት ውይይቶችና የቀረበው የሰላማ ዕቅድ አፍሪካ በተለይም ደቡብ አፍሪካ በዚህ የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት አቋማቸው ምን እንደሆነ የሚገልጽ ነው” በማለት በዚህ በኩል ከምራባውያን የሚመጣውን ጫና  ለመቋቋም የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል።
ሚስተር ሲልየርስ አክለውም ደቡብ አፍርካ የአለማቀፉ ፍርድ ቤት ፈራሚ አባል በመሆኗ  ቻይና ብራዚል፣ ሩሲያ ህንድና ደቡብ ፍሪካ አባል በሆኑበት የብሪክስ ስብሰባ ክስ የተመሰረተብቸውን ፕሬዝድንት ፑቲንን ለመጋበዝና ለማስተናገድ ችግር የነበረባት ሲሆን፤ ያሁኑ  የሰላም  ሀሳብ  የፕሬዳንቱን ክስ መነሳት ስለሚጠይቅና በሂደትም ላይ ስለሆነ የምዕራባውያንን ጫን ለመቋቋም የሚያግዝ ሊሆን ይችላል በማለት በዚህ በኩል የቡድኑ ተልኮ የተሳካ ነው ማለት ይቻላል ብለዋል ። 
ገበያው ንጉሴ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
እሸቴ በቀለ