1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምጣኔ ሀብት ማሻሻያው ያስከተለው የገበያ ሁኔታ በሐዋሳ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 9 2016

በኢትዮጵያ ተግባራዊ የተደረገውን የምጣኔ ሀብት ማሻሻያ ተከትሎ በሲዳማ ፣ በደቡብ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች በሚገኙ ከተሞች በፍጆታ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ጭማሪ እየተስተዋለ ይገኛል ፡፡ ዋጋ ለመጨመር መሠረታዊ ምክንያት እንደሌለ የሚገልጹት የየክልሎቹ ንግድ ቢሮዎች ለዚህም “ ስግብግብ “ ሲሉ የጠሯቸውን ነጋዴዎች ተጠያቂ ያደርጋሉ ፡፡

https://p.dw.com/p/4jVhA
Äthiopien l Markt in Hawasa
ምስል Shewangizaw Wegayoh/DW

የምጣኔ ሃብት ማሻሻያው በሐዋሳ ያሳደረው የገበያ ተጽዕኖ

ሸማቾችና የምጣኔ ሀብት ማሻሻያው

በሀዋሳ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ስመኝ ንጉሴ እና አስናቀች ዱማሎ ዛሬ ሐሙስ በሚቆመው የአረብ ሠፈር ገበያ ለሸመታ መምጣታቸውን ይናገራሉ ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሸቀጦች ዋጋ መናር እንዳሳሰባቸው ለዶቼ ቬለ የተናገሩት ስመኝ እና አስናቀች በተለይም የምግብ ሸቀጦች ዋጋ የሚቀመስ አልሆነም ይላሉ ፡፡

ዶላር ጨምሯል መባሉን ተከትሎ ሁሉም የሸቀጥ አይነት መጨመሩን የጠቀሱት አስተያየት ሰጪዎቹ “ ከቅርብ ቀናት በፊት በ 1ሺህ 30 ብር የገዛነው አምስት ሊትር ዘይት አሁን 1 ሺህ 200 ብር ገብቷል  ፤  180 ብር የነበረው 1 ኪሎ ምሥር አሁን 200 ብር ሆኗል ፡፡ የሚገርመው ጤፍና ሽንኩርትን ጨምሮ  ከዶላር ጋር ግንኙነት የሌላቸው ምርቶች ናቸው ዋጋቸው የጨመረው ፡፡ ዛሬ ላይ ሰው በቀን አንዴ ለመብላት ተቸግሯል ፡፡ በቀጣይ ምን ሊሆን እንደሚችል አናውቅም “ ብለዋል ፡፡

የገበያው ሁኔታ በሓዋሳ
ዶላር ጨምሯል መባሉን ተከትሎ ሁሉም የሸቀጥ አይነት መጨመሩን የጠቀሱት አስተያየት ሰጪዎቹ “ ከቅርብ ቀናት በፊት በ 1ሺህ 30 ብር የገዛነው አምስት ሊትር ዘይት አሁን 1 ሺህ 200 ብር ገብቷል  ፤  180 ብር የነበረው 1 ኪሎ ምሥር አሁን 200 ብር ሆኗል ፡፡ ምስል Shewangizaw Wegayoh/DW

የምርት እጥረት እና የዋጋ ግሽበት መፍትሄ

የንግድ ቢሮዎች እርምጃ

በኢትዮጵያ ተግባራዊ የተደረገውን የምጣኔ ሀብት ማሻሻያ ተከትሎ በሲዳማ ፣ በደቡብ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች በሚገኙ ከተሞች በፍጆታ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ጭማሪ እየተስተዋለ ይገኛል ፡፡ ዋጋ ለመጨመር መሠረታዊ ምክንያት እንደሌለ የሚገልጹት የየክልሎቹ ንግድ ቢሮዎች ለዚህም “ ስግብግብ “ ሲሉ የጠሯቸውን ነጋዴዎች ተጠያቂ ያደርጋሉ ፡፡የዋጋ ጭማሪውም ከማሻሻያው በፊት በገቡ ሸቀጦች ላይ ጭምር መታየቱን የጠቀሱት የንግድ ቢሮዎቹ “ እስከአሁን በሺህዎች በሚቆጠሩ የንግድ ድርጅቶችን በማሸግ ከእሥር እስከ ገንዘብ ቅጣት የሚደርሱ እርምጃዎች መውሰዳቸውን አስታውቀዋል ፡፡

«ቀውስ ውስጥ ገብቷል» የተባለው የምጣኔ ሃብት

ዶቼ ቬለ አስተያየታቸውን የጠየቃቸው በሸቀጦች ንግድ ላይ የተሠማሩ ነጋዴዎች ግን በንግድ ቢሮዎቹ እየተወሰደ የሚገኘው እርምጃ ቸርቻሪዎችን እንጂ ከላይ ያሉ አከፋፋዮችን አይነካም ይላሉ ፡፡ በችርቻሮ የንግድ ዘርፍ በመሠማራታቸው በቀጥታ ከሸማቾች ጋር እንደሚገናኙ የጠቀሱት አስተያየት ሰጪዎች “ የዋጋ ጭማሪው በመቀባበል የሚመጣው ከላይ ከመርካቶ አከፋፋዮች በመነሳት ነው  ፡፡ መንግሥት መሥመሩን ተከትሎ ከላይ እስከ ታች መቆጣጠር ሲገባው የሚያተኩረው ግን ቸርቻሪዎች ላይ ብቻ ነው ፡፡ ሙሉ ሥራ ካልተሠራ የዋጋ ጭማሪውን በቀላሉ መፍታት ማስቸገሩ አይቀርም “ ብለዋል ፡፡

የሕዝብ ቁጥር ዕድገት እና የዋጋ ግሽበት በኢትዮጵያ

የምጣኔ ሀብት ማሻሻያው ፈተና እና ዕድሎች

ዶክተር ደገላ ኤርጌኖ በኢትዮጵያ ሲቪል  ስርቪስ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህርና ተመራማሪ ናቸው ፡፡ ዶክተር ደገላ መንግሥት እየወሰደ የሚገኘው የምጣኔ ሀብት ማሻሻያ ፈርጀ ብዙ ነው ይላሉ ፡፡  ማሻሻያው ከአጭርና ከረጅም ጊዜ አንጻር ፈተናዎችም ዕድሎችም ያሉት መሆኑን ነው ባለሙያው ለዶቼ ቬለ በሰጡት አስተያየት የጠቀሱት ፡፡

በሓዋሳ የገበያ ሁኔታ
ዶቼ ቬለ አስተያየታቸውን የጠየቃቸው በሸቀጦች ንግድ ላይ የተሠማሩ ነጋዴዎች ግን በንግድ ቢሮዎቹ እየተወሰደ የሚገኘው እርምጃ ቸርቻሪዎችን እንጂ ከላይ ያሉ አከፋፋዮችን አይነካም ይላሉ ፡፡ምስል Shewangizaw Wegayoh/DW

የዓለም የምጣኔ ሃብት ምክክር መድረክ

ማሻሻያው ከአጭር ጊዜ እንጻር በምንዛሬ ለውጥ ምክንያት የማምረቻ ግብዓቶች ዋጋ መጨመሩ እንደማይቀር የጠቀሱት የምጣኔ ሀብት ባለሙያው “ ይህም የህብረተሰቡ ዕለት ተዕለት የሚገለገልባቸው ምርቶች ዋጋ እንዲያሻቅብ በማድረግ የዋጋ ግሽበትን ሊያባብስ  ይችላል ፡፡ በውጤቱም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች በእጅጉ ይጎዳል ፡፡ ብለዋል ፡፡

የምጣኔ ሀብት ማሻሻያው ፈተና ብቻ ሳይሆን ዕድሎቹም እንዳሉት የጠቆሙት ባለሙያው “አሁን ያለውን የባንክ ሥርዓት በማዘመን የውጭ የገንዘብ ፍሰትን በአግባቡ መምራትና ማስተዳደር ከተቻለ ማሻሻያው ለዕድገት አጋዥ የሆነ ጠቀሜታ ይኖረዋል ፡፡ በተለይ የውጭ ባለሀብቶችን በመሳብ የወረት ፍሰት እንዲጨምር ያደረጋል ፡፡ እንዲሁም በመደበኛ እና በጥቁር ገበያ መካከል ያለውን የገንዘብ ግብይት በማጥበብ በፋይናንስ ዘርፍ ነጻ ውድድርን ለመፍጠር ያስችላል “ ብለዋል ፡፡

ሸዋንግዛው ወጋየሁ

ታምራት ዲንሳ

ኂሩት መለሰ