1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሕዝብ ቁጥር ዕድገት እና የዋጋ ግሽበት በኢትዮጵያ

ቅዳሜ፣ የካቲት 19 2014

በስቶክሆልምና ኡፕሳላ ዩኒቨርሲቲዎች የምጣኔ ሃብት ተመራማሪና መምህር ዶክተር ጸጋዬ ተገኑ በተለይ ለዶይቸ ቨለ እንደገለጹት የኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ችግር ከአቅርቦት ዕጥረትና ከሕዝቡ ቁጥር መጨመር ጋር የተያያዘ ሲሆን የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ ካልተካሄደ በቀር ሊፈታ አይችልም።

https://p.dw.com/p/47eKu
Äthiopien Lalibela
ምስል Gabrielle Weise/Avalon/picture alliance

በኢትዮጵያ የሚታየው የዋጋ ግሽበት ችግር የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ ካልተካሄደ በቀር ሊፈታ እንደማይችል አንድ ከፍተኛ የምጣኔ ሃብት ምሑር አስታወቁ።
በስቶክሆልምና ኡፕሳላ ዩኒቨርሲቲዎች የምጣኔ ሃብት ተመራማሪና መምህር ዶክተር ጸጋዬ ተገኑ በተለይ ለዶይቸ ቨለ እንደገለጹት የኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ችግር ከአቅርቦት ዕጥረትና ከሕዝቡ ቁጥር መጨመር ጋር የተያያዘ ሲሆን የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ ካልተካሄደ በቀር ሊፈታ አይችልም።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከትናንት በስቲያ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ የዋጋ ግሽበት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት ትልቅ ፈተና እንደሆነ መናገራቸው ይታወቃል።

ታሪኩ ኃይሉ
እሸቴ በቀለ