1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምርት እጥረት እና የዋጋ ግሽበት መፍትሄ

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 5 2014

መንግስት ያለምንም የውጭ ምንዛሬ ፈቃድ መሰረታዊ የፍጆታ ምርቶች ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ የፈቀደው አሁን የተባባሰውን የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት እና በርካታ የውጭ ሀገር የመኖሪያ ፍቃድ ያላቸው ኢትዮጵያዊያን የራሳቸውን ሚና መጫወት እንዲችሉ መሆኑን ያስረዳል። እንደ ምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ግን ውሳኔው የአጭር ጊዜ እንጂ ዘለቂ መፍትሄ አይሆንም።

https://p.dw.com/p/49tvZ
Äthiopien - Die Lebenshaltungskosten in Äthiopien - Markt in Addis Abeba
ምስል Seyoum Getu/DW

የምርት እጥረት እና የዋጋ ግሽበት መፍትሄ

 

የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስቴር ባለፈው ሳምንት አጋማሽ መሠረታዊ የምግብ ሸቀጦች ያለምንም የውጭ ምንዛሬ ፈቃድ (በፍራንኮ ቫሉታ) በቀጥታ እንዲገቡ ውሳኔ አስተላልፎ ነበር፡፡ ሚኒስቴሩ ለአገሪቱ ጉምሩክ ኮሚሽን በላከው ውሳኔ መሰረት፤ እንደ ዘይት፣ ስንዴ፣ ስኳር፣ የህጻናት ወተት እና ሩዝ ያሉ መሰረታዊ የምግብ ሸቀጦች ያለምንም የውጭ ምንዛሬ ፍቃድ በጉምሩክ ኮሚሽን በኩል በቀጥታ ይገባሉ። አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡት የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች መሰል ውሳኔ ለአጭር ጊዜ ችግር ምላሽ ቢሆንም ለዘለቄታዊ መፍትሄው ብዙ መስራትን ይጠይቃል ብለዋል፡፡ 

መንግስት ያለምንም የውጭ ምንዛሬ ፈቃድ (በፍራንኮ ቫሉታ) መሰረታዊ የፍጆታ ምርቶች ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ የፈቀደው አሁን የተባባሰውን የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት እና በርካታ የውጭ ሀገር የመኖሪያ ፍቃድ ያላቸው ኢትዮጵያዊያን የራሳቸውን ሚና መጫወት እንዲችሉ መሆኑን ያስረዳል። የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ዘመዴነህ ንጋቱ በተለይም ለዶይቼ ቬለ ባጋሩት ሙያዊ አስተያየት ውሳኔው ለምርት እጥረትና ለዋጋ ንረቱ መልስ የሚሰጥ ነው ይላሉ፡፡

Äthiopien - Die Lebenshaltungskosten in Äthiopien - Markt in Addis Abeba
ምስል Seyoum Getu/DW

ባለሙያው ይህ ውሳኔ የአጭር ጊዜ እልባት ብቻ እንደሚሆን ገልጸው ዘለቄታዊው መፍትሄ ግን ምርታማነትን በማሳደግ አቅርቦት ከፍ እንዲል ማድረግ ነው ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል ሰሞኑን መንግስት እያጤንኩት ነው ስላለውና ይፋ ስላደረገው የነዳጅ ዋጋ እና ድጎማን በተመለከተ አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ መፍትሄ ያሉትን ሃሳብም አጋርተዋል።

ሌላው የፖለቲካል ኢኮኖሚ ተንታኝ  አቶ ሸዋፈራሁ ሽታሁን ከዚህ ይልቅ መፍተሄው ሌላ ነው በማለት ሞግተዋል፡፡

ስዩም ጌቱ

ኂሩት መለሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ