1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ33ኛው የፓሪስ ኦሎምፒክ ፍጻሜ እና ኢትዮጵያ

ሰኞ፣ ነሐሴ 6 2016

በበርካታ ሁነቶች የተሞላው እና 329 ውድድሮችን ለ16 ቀናት ያስተናገደው 33ኛው የፓሪስ ኦሎምፒክ ትናንት እሁድ ምሽት በድምቀት ተጠናቋል። በአትሌቲክስ እና የዉሃ ዋና 34 አትሌቶችን በቀጥታ በውድድሩ ላይ ያሳተፈው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድን በአንድ ወርቅ እና ሶስት ብር በአጠቃላይ አራት ሜዳሊያዎች ከዓለም 47ኛ ደረጃ ይዞ አጠናቋል።

https://p.dw.com/p/4jONR
Frankreich | Olympische Spiele 2024 in Paris | Abschlusszeremonie Paris 2024 – Stade de France, Saint-Denis
ምስል Leah Millis/REUTERS

የነሐሴ 6 ቀን 2016 ዓ/ም የስፖርት ዝግጅት


በበርካታ ሁነቶች የተሞላው እና 329 ውድድሮችን ለ16 ቀናት ያስተናገደው 33ኛው የፓሪስ ኦሎምፒክ ትናንት እሁድ ምሽት በድምቀት ተጠናቋል። 
በአትሌቲክስ እና የዉሃ ዋና 34 አትሌቶችን በቀጥታ በውድድሩ ላይ ያሳተፈው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድን በአንድ ወርቅ እና ሶስት ብር በአጠቃላይ አራት ሜዳሊያዎች ከዓለም 47ኛ ደረጃ ይዞ አጠናቋል።

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ብሄራዊ ቡድን
በአትሌቲክስ እና የዉሃ ዋና 34 አትሌቶችን በቀጥታ በውድድሩ ላይ ያሳተፈው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድን በአንድ ወርቅ እና ሶስት ብር በአጠቃላይ አራት ሜዳሊያዎች ከዓለም 47ኛ ደረጃ ይዞ አጠናቋልምስል Haimanot Tiruneh/DW


የኦሎምፒክ ቡድኑ ዉጤት ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያስመዘገበችው ዝቅተኛው ነው ተብሏል። ይህም በአትሌቲክስ አፍቃሪው  ኢትዮጵያውያን ዘንድ  ብርቱ ትችት እና ቅሬታ አስከትሏል። 
በውድድሩ አትሌት ታምራት ቶላ በማራቶን የኦሎምፒክ ክብረ ወሰን በማሻሻል ጭምር ከ24 ዓመታት ጥበቃ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለኢትዮጵያ ወርቅ አስገኝቷል። ውጤቱ ቀደም ተብሎ በተደረጉ ውጤቶች የተበሳጨውን ደጋፊ ደስታ መመለስ የቻለ ነበር ። 

ታምራት ቶላ የወርቅ ሜዳሊያውን ከማሸነፉ ባሻገር ለ16 ዓመታት በኬንያዊው ሳሙኤል ዋንጂሩ የተያዘውን 2:23:07 የኦሎምፒክ ክብረወሰን  በ2:06:26 በመግባት ክብረ ወሰኑን ወደ ሀገር ቤት አምጥቷል።

 

 

ታምራት ቶላ የፓሪስ ኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ
ታምራት ቶላ የወርቅ ሜዳሊያውን ከማሸነፉ ባሻገር ለ16 ዓመታት በኬንያዊው ሳሙኤል ዋንጂሩ የተያዘውን 2:23:07 የኦሎምፒክ ክብረወሰን  በ2:06:26 በመግባት ክብረ ወሰኑን ወደ ሀገር ቤት አምጥቷል።ምስል JOEL CARRETT/AAP/IMAGO

 

የሴቶች ማራቶን በፓሪስ ኦሎምፒክ


በኦሎምፒክ ታሪክ እጅግ ወበቃማ በተባለለት የፓሪስ ኦሎምፒክ ለዚያውም ከተጠባባቂነት መጥቶ ማሸነፉ ለታምራት ከፍተኛ አድናቆን አስገኝቶለታል። አትሌት ታምራት ቶላ አሜሪካ ሂውስተን  ባስተናገደችው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የወርቅ ሜዳሊያ ማሸነፉ ይታወሳል።
በተመሳሳይ የሴቶች ማራቶን ተሳትፋ ብርቱ ፉክክር ያደረገችው ትዕግስት አሰፋ ለሀገሯ የብር ሜዳሊያ አስገኝታለች። 
በውድድሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ኔዘርላንዳዊት ሲፈን ሐሰን የኦሎምፒክ ክብረ ወሰን ጭምር በማሻሻል የወርቅ ሜዳሊያዉን አጥልቃለች። ሲፈን ቀደም ሲል በአስር እና አምስት ሺ ሜትር ውድድሮች የነሐስ ሜዳሊያ ወስዳ የነበረ ሲሆን በአንድ የኦሎምፒክ የውድድር መድረክ በትሌቲክስ ሶስት ሜዳሊያዎችን በማንሳት የመጀመሪያዋ ሴት አትሌት በመሆን አዲስ ታሪክ ጽፋለች። 
ለኢትዮጵያ ሌላውን የብር ሜዳሊያ ያስገኙት በ10 ሺ ሜትር ውድድር  በሪሁ አረጋዊ እንዲሁም በ800 ሜትር ለኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የብር ሜዳሊያ ያስገኘችው ጽጌ ዱጉማ ናት ። 

ትዕግስት አሰፋ በውድድር ላይ
በሴቶች ማራቶን ተሳትፋ ብርቱ ፉክክር ያደረገችው ትዕግስት አሰፋ ለሀገሯ የብር ሜዳሊያ አስገኝታለችምስል Christian Petersen/Getty Images


በዘንድሮው የፓሪስ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ ብዙ ተስፋ አድርጋባቸው ነገር ግን ውጤት ካጣችባቸው አትሌቶች መካከል በአሳዛኝ መልኩ  ውድድሩን ሳያጠናቅቅ ተደናቅፎ በመውደቅ በጉዳት የወጣው የ3 ሺ ሜትር ተወዳዳሪው ለሜቻ ግርማ አንዱ እና ተጠቃሽ ነው ። በርቀቱ የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤቱ ለሜቻ ውድድሩን ለማሸነፍ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶት የነበረ ሲሆን ውድድሩን ለማጠናቀቅ 100 ሜትር ገደማ ሲቀረው መሰናክሉ አደናቅፎት በመውደቁ ውድድሩን ሳያጠናቅቅ ቀርቷል። በዚህም የቶክዮው አሸናፊ ሞሮኮዋዊ ሱፍያኔ ኤል ባካሊ አሸናፊ ሆኗል። 

አትሌት ታምራት ቶላ በፓሪስ ኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያን አሸነፈ


በሌላ በኩል በተለያዩ ርቀቶች የተሻለ ሰዓት የነበራት እና ኢትዮጵያ ከአሁን በፊት ሞክራ በማታውቀው አንድን ሰው በሶስት የውድድር መስኮች ማሳተፍ ዉጤት የታጣበት አንዱ እና አነጋጋሪ የሆነ ጉዳይ ነበር ። የ10 ሺ ሜትር የዓለም ሻምፒዮናዋ አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ በ10 ሺ ፣ አምስት ሺ እና 1500 ሜትሮች ተሳትፋ በአንዱም የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ዉስጥ መግባት አልቻለችም ። ጉዳዩ በኦሎምፒክ ኮሚቴ እና በአሰልጣኟ ላይ ብርቱ ትችት እና ወቀሳ አስከትሎባቸዋል። 

በዘንድሮው ኢትዮጵያ በፓሪስ ኦሎምፒክ ያስመዘገበችው ዉጤት እንዲሁ ዝቅተኛ ነው ተብሎ ቀለል ተደርጎ የሚያልፍ ጉዳይ እንዳልሆነ አንጋፋ አትሌቶች ፣ አሰልጣኞች እና ለስፖርቱ ቅርበት ያላቸው ሰዎች በማህበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች እና የመገናኛ ብዙኃን ላይ ከሰጧቸው አስተያየቶች ለመረዳት ይቻላል።

አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ
የ10 ሺ ሜትር የዓለም ሻምፒዮናዋ አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ በ10 ሺ ፣ አምስት ሺ እና 1500 ሜትሮች ተሳትፋ በአንዱም የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ዉስጥ መግባት አልቻለችም ።ምስል JEWEL SAMAD/AFP

 

ለተመዘገበው ዝቅተኛ ውጤት እና አድሏዊ ለተባለው አሰራር የኦሎምፒክ ኮሚቴው ይጠየቅልን የሚሉ ድምጾችም ተበራክተው ተሰምተዋል። 
ለመሆኑ ለዚህ ሁሉ ጥፋት ምክንያት ተደርጎ የቀረበው በኦሎምፒክ ኮሚቴ ፣ በፓሪስ ኦሎምፒክ ተሳታፊ አትሌቶች እና የስፖርት ሰዎች መካከል የተፈጠረው ውዝግብ መነሻ እና መድረሻው ምን ይሆን ? 
ውድድሩን በቅርበት ስትከታተል የነበረው የፓሪሷ ወኪላችን ኃይማኖት ጥሩነህ ተከታዩን አጭር ዘገባ ልካልናለች።
33ኛው የፓሪስ ኦሎምፒክ በአሜሪካ የበላይነት ተጠናቋል ። እስከ ፍጻሜው ዕለት በቻይና እና አሜሪካ መካከል ሲደረግ የነበረው የወርቅ ሜዳሊያ ብልጫ የመውሰድ ትንቅንቅ ሁለቱም ሃገራት  በእኩል 40 የወርቅ ሜዳሊያዎች  ያጠናቀቁ ሲሆን አሜሪካ ባገኘችው ብር ሜዳሊያ ብዛት ቀዳሚ መሆን ችላለች ። በዚህም አሜሪካ በ40 የወርቅ፣ 44 የብር እና  42 የነሃስ በድምሩ 126 ሜዳልያዎችን በመሰብሰብ አንደኛ ሆና ውድድሩን አጠናቃለች።

አንጋፋው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከሩጫው ዓለም ራሴን የማግለያ ጊዜው አይታወቅም አለ


ቻይና በ40 ወርቅ ፣ 27 የብር እና 24 የነሐስ ሜዳሊያዎች በድምሩ  91 ሜዳሊያዎችን በማግኘት 2ኛ፣ ጃፓን በ20 የወርቅ 12 የብር እና 13 የነሐስ ሜዳሊያዎች በድምሩ 45 ሜዳሊያዎችን በማግኘት በ3ኛነት አጠናቃለች ። አውስትራሊያ 4ኛ እንዲሁም አስተናጋጇ ሀገር ፈረንሳይ 5ኛ ደረጃን በመያዝ ጨዋታውን አጠናቀዋል።
በውድድሩ ከአፍሪቃ ሃገራት ቀ,ዳሚ የሆነችው ኬንያ ስትሆን በ4 የወርቅ 2 የብር እና 5 የነሐስ ሜዳሊያዎችን በማግኘት በድምሩ 11 ሜዳሊያዎችን ማሳካት ችላለች።  
በፓሪስ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያዊው ታምራት ቶላ በማራቶን ያስመዘገበውን ጨምሮ 31 የኦሎምፒክ የዓለም ክብረ ወሰኖች ተሻሽለዋል። ይህም ከቶክዮ ኦሎምፒክ የ19 ክብረ ወሰኖች ብልጫ የታየበት ነው። 

የአሜሪካ ቅርጫት ኳስ ቡድን
ሜሪካ በ40 የወርቅ፣ 44 የብር እና  42 የነሃስ በድምሩ 126 ሜዳልያዎችን በመሰብሰብ አንደኛ ሆና ውድድሩን አጠናቃለች።ምስል Brian Snyder/REUTERS

ወደ እግር ኳስ ውድድሮች ስንሸጋገር በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ከተካሄዱ የእግር ኳስ ውድድሮች ውስጥ በኮሚቲ ሼልድ የዋንጫ ሽሚያ ጫወታ ሁለቱን የማንችስተር ከተማ ባላንጣዎች ያገናኘው ግጥሚያ ተጠቃሽ ነው። 

የፓሪስ ኦሎምፒክ 2024 ፤ ኢትዮጵያ በ 800 ሜትር ሜዳልያ አገኘች


ባለፈው ቅዳሜ ማንችስተር ሲቲን ከማንችስተር ዩናይትድ ባገናኘው ግጥሚያው በመደበኛ የጨዋታ ጊዜ አንድ አቻ መጠናቀቁን ተከትሎ አሸናፊው በመለያ ምት ተለይቷል። በዚህም ማንችስተር ሲቲ 7 ለ 6 በሆነ ጎል አዲሱን የውድድር ዘመን በዋንጫ አሟሽቷል። በጫወታዉ የተሻለ የኳስ ቁጥጥር የነበረው ማንችስተር ሲቲ ሲሆን ጎል ለማስቆጠር ቅድሚያ የወሰደው ግን ማንችስተር ዩናይድ ነበር። አሌክሳንድሮ ጋርናቾ የጎሏ ባለቤት ሲሆን ለሲቲ ጫወታው ሊጠናቀቅ ጥቂት ደቂቃዎች በቀሩበት በርናንዶ ሲልቫ አስቆጥሯል። 
ዋንጫው ለሲቲ 6ኛው የኮሙኒቲ ሼልድ ዋንጫ ሆኖ ተመዝግቦለታል።

ኮሚኒቲ ሼልድ ጫወታ
ባለፈው ቅዳሜ ማንችስተር ሲቲን ከማንችስተር ዩናይትድ ባገናኘው ግጥሚያው በመደበኛ የጨዋታ ጊዜ አንድ አቻ መጠናቀቁን ተከትሎ አሸናፊው በመለያ ምት ተለይቷል። ምስል David Cliff/AP/dpa/picture alliance

የኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ቡድን የቱሪዝም መድረክ በፓሪስ


በሌሎች የቅድመ የውድድር ዘመን ጫወታዎች በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት አርሴናል እና ሊቨርፑል ድል ቀንቷቸዋል። በኤሜሬትስ ዋንጫ የፈረንሳዩን ሊዮን የጋበዘው አርሴናል 2 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል። ለአርሴናል ጎሎቹን ተከላካዮቹ ሳሊቫ እና ጋብሬል አስቆጥረዋል። በውድድር ዓመቱ መድፈኞቹን የተቀላቀለው ጣልያናዊው ሪካርዶ ካላፎሪ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሜዳ ገብቷል። 
በተመሳሳይ የቅድመ ውድድር መርሃ ግብር ሊቨርፑል የስፔኑን ሴቪያ አስተናግዶ 4 ለ 1 በሆነ ሰፊ ጎል አሸንፏል። 
የጣልያኑን ኢንተር ሚላን በስትንፎን ብሪጅ ያስተናገደው ቼልሲ በበኩሉ አንድ አቻ በመውጣት ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል። 

ታምራት ዲንሳ 
ኂሩት መለሰ

የአርሴናል ተጫዋቾች ኦዲጋርድ እና ሃቨርትስ
በኤሜሬትስ ዋንጫ የፈረንሳዩን ሊዮን የጋበዘው አርሴናል 2 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል። ለአርሴናል ጎሎቹን ተከላካዮቹ ሳሊቫ እና ጋብሬል አስቆጥረዋል።ምስል Frank Augstein/AP Photo/picture alliance