1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሴቶች ማራቶን በፓሪስ ኦሎምፒክ

እሑድ፣ ነሐሴ 5 2016

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሄራዊ ቡድን በፓሪስ ኦሎምፒክ በነበረው ቆይታ አንድ የወርቅና ሶስት የብር ሜዳሊያዎችን በማግኘት ውድድሩን አጠናቋል። በዛሬው የሴቶች የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊቷ ትዕግስት አሰፋ 2ኛ ወጥታ ሶስተኛውን የብር ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ አስገኝታለች።

https://p.dw.com/p/4jLve
ሲፈን ሃሰን ውድድሩን ስታጠናቅቅ
ሲፈን ሃሰን የፓሪስ ኦሎምፒክ የሴቶች ማራቶንን ክብረ ወሰን በማሻሻል ጭምር የወርቅ ሜዳሊያውን አሸንፋለችምስል Naomi Baker/Getty Images

የሴቶች ማራቶን በፓሪስ ኦሎምፒክ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሄራዊ ቡድን በፓሪስ ኦሎምፒክ በነበረው ቆይታ አንድ የወርቅ እና ሶስት የብር ሜዳሊያዎችን በማግኘት ውድድሩን አጠናቋል። በዛሬው የሴቶች የማራቶን ውድድር፤ ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ኔዘርላንዳዊት ሲፈን ሃሰን የፓሪስ ኦሎምፒክ የሴቶች ማራቶንን ክብረ ወሰን በማሻሻል ጭምር የወርቅ ሜዳሊያውን አሸንፋለች ።  ኢትዮጵያዊቷ የማራቶን የክብረ ወሰን ባለቤት ትዕግስት አሰፋ ሁለተኛ ወጥታ ሶስተኛውን የብር ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ አስገኝታለች ። ይሁንና ትግስት ውድድሯን ልታጠናቅቅ ጥቂት ሜትሮች ሲቀራት በውድድሩ አሸናፊ ከሆነችው ሲፈን ሀሰን ጋር በተፈጠረ መነካካት በውጤቷ ላይ ተጽዕኖ ተፈጥሯል በማለት የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ክስ ማቅረቡ አስታውቋል።

ሲፈን ውድድሩን ለማጠናቀቅ 2 ሰዓት ከ22 ደቂቃ ከ55 ሰከንድ ወስዶባታል።ኬንያዊቷ ኤለን ኦቢሪ ሶስተኛ ወጥታ ነሐስ አግኝታለች። በውድድሩ ብርቱ ተፎካካሪ የነበረችው ኢትዮጵያዊቷ አማኔ በሪሶ አምስተኛ ወጥታለች።
የውድድሩ አሸናፊ ሲፈን ሀሰን በአስር እና አምስት ሺ ሜትር ውድድሮች የነሐስ ሜዳሊያዎችን አግኝታ የነበረ ሲሆን በሶስተኛ ውድድሯ ማሸነፏ ከመላው ዓለም አድናቆት አስገኝቶላታል ።ኬንያዊቷ ኤለን ኦቢሪ ሶስተኛ ወጥታ ነሐስ አግኝታለች።  የኦሎምፒክ የማራቶን ክብረ ወሰን በለንደን ኦሎምፒክ በኢትዮጵያዊቷ ቲኪ ገላና ተይዞ መቆየቱ ይታወሳል። 
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሄራዊ ቡድን በፓሪስ ኦሎምፒክ በነበረው ቆይታ አንድ የወርቅ እና ሶስት የብር ሜዳሊያዎችን በማግኘት ውድድሩን አጠናቋል።

ሃይማኖት ጥሩነህ
ልደት አበበ