1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ቡድን የቱሪዝም መድረክ በፓሪስ

ዓርብ፣ ሐምሌ 26 2016

ፈረንሳይ በምታስተናግደው የዘንድሮው የፓሪስ ኦሎምፒክ 2024 የምትሳተፈው ኢትዮጵያ መድረኩን ከስፖርት ውድድሩ ባሻገር የሀገር ባህል፣ ታሪካዊ የቱሪስት መስህቦችን ማስተዋወቂያ አጋጣሚም አድርጋዋለች።

https://p.dw.com/p/4j2p3
ፓሪስን ያደመቀው የኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ቡድን የቱሪዝም መድረክ
ፓሪስን ያደመቀው የኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ቡድን የቱሪዝም መድረክ ምስል Haimanot Tiruneh/DW

የቱሪዝም መድረክ በፓሪስ

 

ሰሞኑን ፓሪስ እየደመቀች የምትገኘው በማስተናገድ ላይ ባለችው የፓሪስ 2024 የኦሎምፒክ ብቻ አይደለም። በፓሪስ ኦሎምፒክ የምትሳተፈው ኢትዮጵያ ከአትሌቶቿ ባሻገር በጎዳና ባህላዊ የቡና ማፍላት ሥርዓት የታጀበ የኢትዮጵያን ባህልና ታሪካዊ የቱሪስት መስህቦችን በሚያስተዋውቅ፤ ለዚህም ሌላ የኢትዮጵያን የኦሎምፒክ ጀግኖች ፎቶዎች ባካተተው ልዩ ዝግጅትም ነው። ይህ ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ በሚል ስያሜ በፓሪስ ፈረንሳይ እየተካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያን ገጽታ የማስተዋወቅ ልዩ ዝግጅት በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ፣ በኢትዮጵያ ቱሪዝም ሚኒስቴር እና ፓሪስ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስተባባሪነት የዘጋጀ መሆኑን ከፓሪስ ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ የላከችው ዜና ያስረዳል። 

 ሃይማኖት ጥሩነህ 

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ