1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን ያስተናገደችዉ የአዉሮጳ እግርኳስ ሻንፒዮና 2024 እና አንድምታዉ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 11 2016

የአውሮጳ የእግር ኳስ ሻምፒዮና በስፔን አሸናፊነት ተጠናቋል። አዘጋጅ ሃገር ጀርመን፤ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ለማለፍ ባትችልም፤ ሃገሪቱ የእግርኳስ እንግዶቿን ጋብዛ በማስተናገድዋ፤ በሃገሪቱ የሚታዩ የተለያዩ ያልተጠበቁ ችግሮች በኳስ ዝግጅቱ ምክንያት ፋታ ሰጥተው ነዉ የሰነበቱት። 17 ኛዉ የአውሮጳ የእግርኳስ ሻንፒዮና አመርቂ ነበር?

https://p.dw.com/p/4iJMv
EURO 2024: Schweiz - Deutschland (Vorrunde)
ምስል Matthias Koch/picture alliance

ጀርመን ያስተናገደችዉ የአዉሮጳ እግርኳስ ሻንፒዮና 2024 እና አንድምታዉ

 

የአውሮጳ የእግር ኳስ ሻምፒዮና በስፔን አሸናፊነት ተጠናቋል። አዘጋጅ ሃገር ጀርመን፤ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ለማለፍ ባትችልም፤ ሃገሪቱ የእግርኳስ እንግዶችን ጋብዛ በማስተናገድዋ፤ በሃገሪቱ የሚታዩ የተለያዩ ቀዉሶች በኳስ ዝግጅቱ ምክንያት ደብዘዝ ብለዉ ነዉ የሰነበቱት።   

ጀርመን በጎርጎረሳዊዉ 2006 ዓ.ም የዓለም እግርኳስ ዋንጫ ስታዘጋጅ «ዓለም በወዳጅ ሃገር በእንግድነት» በሚል መርህ ለአራት ሳምንታት የዓለም እግር ኳስ አፍቃሪን ተቀብላ ማስተናገድዋ ዛሬም በተለይ በጀርመናዉያን ዘንድ በደስታ የሚታሰብ ነዉ።  በጎርጎረሳዉያኑ 2006 ሰኔ እና ሐምሌ ወር ላይ ወደ ጀርመን በእንግድነት የገቡት የእግርኳስ አፍቃሪ የዓለም ህዝቦች፤ ሃገሪቱን ህዝብ እንግዳ ተቀባይ፤ ደስተኛ፤ እና ግልፅ ሆኖ  ብቻ ሳይሆን ያገኙት፤ የነበረዉ ጥሩ የአየር ፀባይ እና ፀሐይዋ ድምቀት፤ ልክ የመብራት ማብርያ ማጥፋያ ሲነካ እንደሚበራ እንደሚጠፋ ሁሉ ተስማሚ የአየር እንዲኖር የታዘዘ ያህል እስኪመስል ፣ የሰመረ ነበር። ሃገሪቱ ጥቁር፤ ቀይ እና ወርቃማ ቀለም በያዘዉ ሰንደቃላማ ደምቃና ተዉጣ፤ ህዝቡ በደስታ ሲቦርቅ ያየ እዉነት ጀርመናዉያን እንዲህ ናቸዉ እንዴ ሲል ያልጠየቀ አልነበረም ።

በ 2006  ዓ.ም  በጀርመን ተዘጋጅቶ የነበረዉ፤ የዓለም እግርኳስ ዋንጫ ወቅት እንደሚጣፍጥ ተረት ሁሉ፤ «የበጋ ተረት» የሚል ስያሜን ተሰጥቶት በጀርመን የታሪክ ማህደር ሰፍሯል። ከ18 ዓመታት በኋላ ሰሞኑን በጀርመን አዘጋጅነት የተካሄደዉ 17 ኛዉ የአውሮጳ የእግርኳስ ሻንፒዮና እንደ 2006  ዓመተምህረቱ  የዓለም ዋንጫ ዝግጅት በአስደናቂ ስሜት  ህዝቡ ተደስቶ የተጠናቀቀ የበጋ ተረት ሊባል ይችል ይሆን?

"ኳስ ይዞታ" የተሰኘው የእግር ኳስ መጽሐፍን የደረሱት ዳግሩን ሂንትዜ ለDW ይህን ብለዋል።  

«ይህ ባለፈዉ ነገር ላይ መመስረት እና በዝያ መሰረት ለመናገር መሞከር አንዱ የጀርመን ባህሪ ነዉ። በ 2006  ዓ.ም  የዓለም ዋንጫ ዝግጅት ወቅት፤ የነበረዉ ስሜት አስደሳች ራስን የመዉደድ ስሜት ሁሉ የታየበት ነበር።  አሁን ግን ሌላ ጊዜ፤ ሌላ ወቅት ፤ ሌላ ቦታ ላይ ነዉ የምንገኘዉ። እናም እውነታውን መመርመር ይኖርብናል። ዘንድሮ በ 2024 ዓ.ም  ህዝብን እንደገና አንድ ላይ ማምጣት መሰብሰብ እንችል እንደሆን ነዉ አስበን የነበረዉ።»

በጎርጎረሳዊዉ 2012 ዓ.ም የዓለም እግር ኳስ መዲና በርሊን የጀርመን ደጋፊዎች
በጎርጎረሳዊዉ 2012 ዓ.ም የዓለም እግር ኳስ መዲና በርሊን የጀርመን ደጋፊዎች ምስል Soeren Stache/dpa/picture alliance

በጎርጎረሳዉያኑ 2006 ዓ.ም የዓለም እግርኳስ ዋንጫ በተዘጋጀበት ወቅት፤ የኮሮና ወረርሽኝ፣ የስደተኞች ቀውስ፣ ሩስያ በዩክሬን ያስነሳችዉ ጦርነት፤ ብሎም ቀኝ አክራሪዎች በፖለቲካዉ መንደር ጎልተዉ የወጡበት ጊዜ አልነበረም። በአሁኑ ወቅት በተለይ በአውሮጳ በተካሄደዉ ምርጫ በምስራቅ ጀርመን ክፍሎች ቀን አክራሪዎች ጠንካራ ሆነዉ የወጡበት ጊዜ ሆንዋል። በዚህም አሁን የተካሄደዉ የአውሮጳ እግርካስ ሻምፒዮና ማህበራዊ ውህደት እየተበጣጠሰ ባለበት እና ፣ አነስተኛ ቡድኖች እርስ በእርስ ተራርመዉ ወደ ጋራ ሃሳብ እና መግባባት መምጣት ያቃታቸዉ ወቅት ነዉ።   

ይሁንና ይላሉ፤ በኮለኝ ከተማ በሚገኝዉ ከፍተኛ የስፖርት ኮሌጅ መምህርና የፖለቲካ ጉዳይ ምሁር  ዩርገን ሚትታግ፤ ይሁን ጀርመን የአዉሮጳ እግርኳስ ሻንፒዮናን ያዘጋጀችዉ ትክክለኛ ወቅት ነዉ። እንደ 2012 ዓ.ምቱ ጊዜ አስደሳቹ  የበጋ የተረት ጊዜ ተብሎ ባይሰየምም፤ በትንሹም ቢሆን የበጋ የተረት ወቅት እንደነበር የማይካድ እንደነበር ተናግረዋል።   

«በርግጥም በጀርመን የሚታየዉ ስሜት የአውሮጳ የእግርኳስ ሻንፒዮና ከመጀመሩ በፊት ከነበረዉ ይበልጥ አዎንታዊ ነው። የአዉሮጳ እግርኳስ ግጥምያ ለበርካታ ዜጎች ትልቅ ክብረ በዓል ሆኖ ቆይቷል። ከውጭ አገር የመጡ እንግዶችም አብረው ሲያከበሩ ቆይተዋል። ለምሳሌ ከደህንነት ጋር በተገናኘ ስጋት አልታየም። የእግርኳስ ግጥምያዉ የጀርመንን ሕዝብ ምናልባትም በትንሹም ቢሆን አቀራርቦም ይሆናል።»

በርካታ ጀርመናዉያን ከረጅም ጊዜ በኋላ በዘንድሮዉ የአዉሮጳ እግርኳስ ሻንፒዮና በድጋሚ ከብሔራዊ ቡድናቸው ጎን መሰለፋቸዉ ሌላዉ መልካም ዜና ነበር። ምንም እንኳ አስተናጋጅ ሃገር ጀርመን ከስፔን ጋር ሽቱትጋርድ ከተማ ላይ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ለማለፍ ባካሄደችዉ ግጥምያ በስፔን ሁለት ለአንድ ተሸንፋ ከግጥምያ ዉጭ ብትሆንም፤ ደራሲ  ዳግርን ሂንትዜ እንደተናገሩት ለጀርመን በርግጥም በዋናነት የእግር ኳስ ግጥምያዉን ለማሸነፍ አልነበረም። 

በጎርጎረሳዊዉ 2024 ዓ.ም የአዉሮጳ ሻንፒዮና የጀርመን ቡድን ደጋፊዎች
በጎርጎረሳዊዉ 2024 ዓ.ም የአዉሮጳ ሻንፒዮና የጀርመን ቡድን ደጋፊዎች ምስል Gerhard Schultheifl/Jan Huebner/IMAGO

«ዋናው ጉዳይ አብረን እንሸነፋለን፤ አብረንም እናሸንፋለን የሚለዉ መርህ ነበር። እናም ተሸናፊዉ አሁን ብሔራዊ ቡድኑ ብቻ ሳይሆን ደጋፊዎችም ተሸንፈናል። ሁላችንም ተሸናፊዎች ነን። ምናልባትም አሁን ከቡድኑ ጀርባ እንደገና ተሰብስበን ተጫዋቾቹን፤ አሰልጣኙን እና የቡድኑን ሰራተኞች ሁሉ መውደድ መጀመር እንደምንችል ለመማር ጥሩ የትምህርት ጊዜ ሊሆን ይችላል።»

በሙኒክ ላይ ስፔን ከፈረንሣይ ጋር ባደረገዉ የግማሽ ፍፃሜ ግጥምያ ላይ የጀርመን ደጋፊዎች በስፔኑ ተከላካይ ማርክ ኩኩሬላ ላይ ከፈፀሙት የተቃዉሞ ፉጨት በስተቀር ዘንድሮ ጀርመን በአውሮጳ ሻምፒዮና ግጥምያ ጥሩ መስተንግዶን አሳያቷል። ድንቅ መንፈስ የታዩባቸዉ በሕዝብ ተጨናንቀዉ የነበሩት ስታዲየሞች እና በትልቅ እስክሪን የህዝብ እይታ ቦታዎች ከፍተና ስሜቶች እና የእግርኳስ ፍቅር የሰዎች መቀራረብ ታይቷል። በተለያዩ ስቴድዮሞች እና እርኳስ ግጥምያዉን በሰፊ የቴሌቭዥን ስክሪን በሚታይባቸዉ ጎዳናዎች ላይ የተሰማሩ በአጠቃላይ  22 ሺህ የጀርመን ፊደራል ፖሊስ መኮንኖችም ያለምንም ችግር ስራቸዉን አጠናቀዋል።  የአዉሮጳና እንግርኳስ ሻንፒዮና  2024 ን ለማየት ወደ ጀርመን የመጡ ከውጭ ሃገራት የእግር ኳስ አፍቃሪዎች እና ደጋፊዎች ባለፈዉ የዓለም እግር ኳስ ግጥምያን ካዘጋጀችዉ ከካታር በተቃራኒ በጀርመን እግር ኳስን ኖረዉ ተደስተዉ ጊዜያቸዉን ያሳለፉበት ወቅት ነበር።     

አዜብ ታደሰ / ኦሊቨር ፒፐር

አዜብ ታደሰ