1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስፖርት፤ ሐምሌ 5፤ 2013 ዓ.ም

ሰኞ፣ ሐምሌ 5 2013

በዓለማችን የኮሮና ስርጭት ከተስፋፋ በኃላ ተዘግቶ የነበረዉ የማኅበራዊ የስፖርት መገኛኛ መድረክ ቀስ በቀስ መድረኩን እየከፈተ ነዉ። ሰሞኑን በዓለማችን የአዉሮጳ የእግር ኳስ ሻንፒዮና የመጀመርያዉ እና ሰፊዉ ማኅበራዊ መድረክ ሆኖ ሰንብቶአል።

https://p.dw.com/p/3wM9u
EURO2020 I Italien - England
ምስል Christian Charisius/dpa/picture alliance

የእንግሊዙ የእግር ኳስ ቡድን አዲስ ታሪክን መፃፍ አልቻለም

በዓለማችን የኮሮና ስርጭት ከተስፋፋ በኃላ ተዘግቶ የነበረዉ የማኅበራዊ የስፖርት መገኛኛ መድረክ ቀስ በቀስ መድረኩን እየከፈተ ነዉ። ሰሞኑን በዓለማችን የአዉሮጳ የእግር ኳስ ሻንፒዮና የመጀመርያዉ እና ሰፊዉ ማኅበራዊ መድረክ ሆኖ ሰንብቶአል። ትናንት ለንደን በሚገኘዉ በወንብሊ ስቴድዮም ለዋንጫ የተጋጠሙት የእንጊሊዝ እና የጣልያን ቡድን በጣልያን አሸናፊነት ተጠናቆአል። የኢንጊሊዙ ሳዉዝ ጌት የወጣት ብሔራዊ የእግርኳስ ቡድን ከ 55 ዓመት በኋላ አዲስ ታሪክን በዌንብሌ ስቴድየም ለመፃፍ የነበረዉ ምኞት ሳይሳካ ቀርቶአል። ኮፓ አሜሪካ ግጥምያ በፍፃሜዉ አርጄንቲና ብራዚልን በማሸነፍ ቻንፒዮና ስትሆን፤ ታዋቂዉ የእግር ኳስ ተጫዋች ሊዮኔል ሜሲም የዘመናት ህልሙ በመጨረሻ እዉን ሆንዋል። ዘንድሮ ቶኪዮላይ የሚካሄደዉ የኦሎምፒክ ግጥምያ በኮሮና ተኅዋሲ ስርጭት ምክንያት ያለተመልካች እንደሚካሄድ ይፋ ሆንዋል። በአንፃሩ የጀርመን የእግርኳስ ግጥምያ የቡንደስ ሊጋዉ ተመልካቾች በቀጣዩ የዉድድር ዘመን ወደ ስቴድየም ሊመለሱ እንደሆነ ተነግሮአል። በፈረንሳይ የምትገኘዉ የዶቼ ቬለ የስፖርት አዘጋጅ ሃይማኖት ጥሩነህ በሳምንቱ መጨረሻ በዓለማችን የተከናወኑ አበይት የእስፖርት ክንዉኖችን አሰባስባ ልካልናለች።

ሃይማኖት ጥሩነህ

አዜብ ታደሰ