1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመንና የፈረንሳይ ግጥምያ  1 - 0 ተጠናቀቀ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 8 2013

የጀርመን ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ከዓለም እግር ኳስ አሸናፊ ከሆነዉ ከፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ጋር ባደረገዉ የመጀመርያ የአዉሮጳ ሻንፒዮና ግጥምያ አልቀናዉም። ምንም እንኳ ቡድኑ ጥሩ የጨዋታ ብቃትን ቢያሳይም፤አምስት ቁጥርን ለብሶ በተከላካይ ቦታ ላይ ይጫወት የነበረዉ ማትስ ሁምልስ በራሱ ግብ ላይ አንድ አስቆጥሮአል። ጨዋታዉ 1-0 ተጠናቆአል።

https://p.dw.com/p/3uxSj
Deutschland München | UEFA Euro 2020 | Frankreich v Deutschland
ምስል Matthias Hangst/REUTERS

«ሁለቱም ጠንካራ ቡድኖች ናቸዉ፤ የሚገኙትም ምድብ «F» ወይም የሞት ምድብ በሚባለዉ ዉስጥ ነዉ»

የጀርመን ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ከፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ከመጋጠሙ በፊት፤

 

በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ለአንድ ዓመት ተቋርጦ ባለፈዉ አርብ ሮም ጣሊያን ውስጥ በቱርክ እና የጣሊያን  ቡድን ጨዋታ የጀመረው የአውሮጳ የእግር ኳስ ሻምፕዮና ዛሬ በአምስተኛ ቀኑ ጀርመን ከዓለም የእግር ኳስ ሻንፒዮና ከሆነዉ ከፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ጋር ይጋጠማል። የሁለቱ ወዳጅ ሃገራት ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታቸዉን የሚያካሂዱት በታዋቂዉ የጀርመን የእግር ኳስ ቡድን ባየር ሙንሽን መቀመጫ በሆነዉ በሙኒክ ከተማ በሚገኘዉ ግዙፍ «አልያንዝ አሪና» ስቴድዮም ነዉ። እዚህ በማዕከላዊ አዉሮጳ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት «በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ አራት ሰዓት» የሚጀምረዉ ግጥምያ በተለይ በጀርመን በጉጉት እየተጠበቀ ነዉ። የኮሮና የዝዉዉር ገደብ አዉሮጳዉያንን እንደልብ እንዳይዘዋወሩ በእግር ኳሱም ዓለም ብዙም እንዳይገናኙ ካደረገ ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በኋላ የሁለቱ ሃገራት የብሄራዊ እግር ኳስ ግጥምያ ነዋሪዉን ዳግም ወደለመደዉ አይነት የማኅበራዊ ኑሮ መመለሻ የመጀመርያ ርምጃ ነዉም ተብሎለታል። 75,021 ሰዎችን የመያዝ አቅም ያለዉ የሙኒኩ የእግርኳስ ስቴድዮም በኮሮና ስጋት ብቻ ዛሬ ቦታዉ ላይ ተገኝተዉ ጨዋታዉን መከታተል የሚችሉ 15 ሺህ ሰዎች ብቻ ናቸዉ። ይሁንና በጀርመን የተለያዩ አካባቢዎች በቀበሌዉ፤ በየመንደሩ እና በየማኅበራቱ ሰፋፊ የቴሌቭዥን ስክሪን ተሰቅሎ ሕዝብ የእግርኳስ ጨዋታዉን መጀመር የፊሽካ ጩኸት እተጠባበቀ ነዉ ። በፈረንሳይስ? እዚህ ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት የፈረንሳይዋን ዘጋብያችንን ሃይማኖት ጥሩነህን ስለሁኔታዉ ጠይቄያታለሁ።

Fussball Deutschland Fanfest während des WM-Gruppenspiels Deutschland 2014
ምስል Daniel Reinhardt/dpa/picture alliance

ሃይማኖት ጥሩነህ

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሰ