1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን መግለጫ

ቅዳሜ፣ ጥር 4 2016

የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ( ገና ) ሲከበር በውጭ የሚኖሩ አንድ ጳጳስ ስለ መንግሥት እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን በተመለከተ የተናገሩትን ንግግር ካላወግዘች የጥምቀት በዓልን ለማክበር እንደማትችል ከመንግሥት እንደተገለፀላት ያስታወቀችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያ እንዲህ ያለው ጉዳይ ተቀባይነት የለውም አለች።

https://p.dw.com/p/4bCah
Ethiopian Orthodox church press briefing in Addis Abeba Ethiopia today
ምስል Seyoum Hailu/DW

የጥምቀት በዓል አከባበር እና የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን መግለጫ

የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ( ገና ) ሲከበር በውጭ የሚኖሩ አንድ ጳጳስ ስለ መንግሥት እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን በተመለከተ የተናገሩትን ንግግር ካላወግዘች የጥምቀት በዓልን ለማክበር እንደማትችል ከመንግሥት እንደተገለፀላት ያስታወቀችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያ እንዲህ ያለው ጉዳይ ተቀባይነት የለውም አለች። 

ቤተ ክርስትያን ሰላምን ከመሻት ውጭ ሌላ አቋም የላትም ያሉት የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም በጳጳሱ ንግግር ላይ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የሚሰጥበት ቢሆንም "ቤተ ክርስትያን የራሷ ነፃነት ያላት" መሆኗ ሊዘነጋ አይገባም ሲሉ በማስያዣ የማትሠራ መሆኗን ተናግረዋል።

 የትግራይና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ.ክ ዉዝግብ

ስለ ቤተ ክርስትያኗ "አዛዣችን በዝቷል" ያሉት ብፁዕ አቡነ አብርሃም "ማስፈራሪያ አይገዛንም" ሲሉ ለእምነቱ የማይሞት እንደሌለ በማስታወስ አሳስበዋል። 

ዋና ሥራ አስኪያጁ አክለውም ሰሞኑን ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ የሚወጣ ነገር በሙሉ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች እየተፈተሸ መኾኑን እና ድርጊቱ ቤተ ክርስቲያኗን መድፈር መኾኑን እና ተገቢ እንዳልሆነ አብራርተዋል። 

የቤተ ክርስትያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ከሀገር ኮብልለዋል በሚል የሚነገረው ሰሞነኛ መረጃ ሀሰተኛ ወሬ መሆኑንና በቅዱስ ፓትርያርኩ ፈቃድ ፣ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አውቆት ለአገልግሎት ከሀገር የወጡ መሆኑን ገልፀዋል።

የቤተ ክርስትያኗ ማብራሪያ 

ከሳምንት በፊት በውጭ የሚኖሩ አንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ጳጳስ የኢትዮጵያን መንግሥት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን አስመልክቶ በተናገሩት የውግዘት ቃል ምክንያት መንግስት ቅያሜውን ገልጾ ፣ ቤተክርስትያን መልስ እንድትሰጥበት ማሳሰቡን ፣ ቤተ ክርስትያኒቱም በጉዳዩ ላይ እንደተወያየችበት የገለፁት የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ቤተ ክርስትያኗ በዓለ ጥምቀቱን ለማክበር እንዲህ አይነቱን  አስቀድማ እንድታወግዝ መጠየቁ አግባብ አለመሆኑን ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ( ገና ) ሲከበር በውጭ የሚኖሩ አንድ ጳጳስ ስለ መንግሥት እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን በተመለከተ የተናገሩትን ንግግር ካላወግዘች የጥምቀት በዓልን ለማክበር እንደማትችል ከመንግሥት እንደተገለፀላት ያስታወቀችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያ እንዲህ ያለው ጉዳይ ተቀባይነት የለውም አለች። ምስል Massimo Percossi/Ansa/ZUMA Press/IMAGO

በጀርመን የኢኦተቤ/ክርስቲያን ምሥረታ 40ኛ ዓመት


"ቤተ ክርስትያን የራሷ ነፃነት አላት። የራሷ ክብር አላት። ሁሉም ያም ይሄንን አድርጊ ፣ ይሄም ይህንን አድርጊ ስላላት እየተጌተተች የተባለችውን የምታስተናግድ አትሆንም" 

ሃይማኖትን ሽፋን እያደረጉ እንደፈለጉ መናገር አይፈቀድም

"መንግሥት አኩራፊ ሊሆን አይገባም" ያሉት ብፁዕ አቡነ አብርሃም ቤተ ክርስትያን ከሰላም ውጭ ሌላ አቋም እንደሌላት ተናግረዋል። በተባለው ንግግር ላይ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የሚሰጥበት መሆኑንም ገልፀዋል። "በዘፈቀደ፣ በደመነፍስ፣ ሃይማኖትን ሽፋን እያደረጉ እንደፈለገ ማለትም ደግሞ ከቤተ ክርስትያኒቱም ጋር አይሄድም" ብለዋል። 

"ቤተ ክርስትያን አቤቱታ የምታቀርብበት ነገር የለም ማለት አይደለም" ሲሉ ይልቁንም ጠባቂ ያጣች መሆኗን ብፁዕ አቡነ እብርሃም ገልፀዋል። 

"ሰላምን ማን ያምጣ'' ? የሚለው ባለቤት ያጣ ይመስላል

ሰሞኑን መንግሥት ቤተ ክርስትያኗን የደፈረበትን ድርጊት በቅጥሯ እየፈፀመ መሆኑን ቤተ ክርስትያኗ ይታወቅልኝ ብላለች።

ጥምቀት በአዲስ አበባ
ጥምቀት በአዲስ አበባምስል Solomon Muchie/DW

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን የሰላም ጥሪ

ሰላምን ማን ያምጣ? ማን ያስርጽ የሚለው ጉዳይ ባለቤት ያጣ ይመስላል ? ሲሉ የጥምቀት በዓል አከባበርን እና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ ላይ የተናገሩት ብፁዕ አቡነ አብርሃም የቤተ ክርስትያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ኮበለሉ የሚባለው መረጃ ሐሰት እንደሆነ አረጋግጠዋል። 

"ለሃይማኖቱ የማይሞት የለም"

በሃይማኖት ከመጣ ቤተ ክርስትያኗ አትገዙ ብላ ማወጅ እንደምትችል፣ ነገር ግን አትገዙ የሚለው ደረጃ ላይ እንዳልደረሰች በመግለጫቸው የተናገሩት የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም "በደል ይቁም፣ ሰላም ከሀገር እስከ ሀገር ይስፈን" የሚል ጥሪም አድርገዋል።

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ