1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
እምነትአፍሪቃ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን የሰላም ጥሪ

ረቡዕ፣ ግንቦት 16 2015

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ሁሉም ዜጋ በሀገሩ በእኩልነት፣ በሰላምና በፍቅር ተከባብሮ በአንድነት እንዲኖር ግጭቶችና አለመግባባቶች በውይይት እንዲፈቱ የሰላም ጥሪ አስተላለፈች ። የቤተ ክርስትያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ ከግንቦት 1 ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 16 ቀን፣ 2015 ዓ. ም ምልዐተ ጉባኤውን ሲያደርግ ሰንብቷል ።

https://p.dw.com/p/4Rlun
Äthiopien Addis Abeba | Pressekonferenz der äthiopischen orthodoxen Kirche:  Patriarch Aab Mathias
ምስል DW/S. Muche

«የሰላም ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል»

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ሁሉም ዜጋ በሀገሩ በእኩልነት፣ በሰላምና በፍቅር ተከባብሮ በአንድነት እንዲኖር ግጭቶችና አለመግባባቶች በውይይት እንዲፈቱ የሰላም ጥሪ አስተላለፈች ።  የቤተ ክርስትያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ ከግንቦት 1 ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 16 ቀን፣ 2015 ዓ. ም ምልዐተ ጉባኤውን ሲያደርግ ሰንብቷል ።  የጉባኤውን መጠናቀቅ በተመለከተ ዛሬ አመሻሽ ላይ መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ፓትርያርክ ብፁእ አቡነ ማትያስ «ምልዐተ ጉባኤው ለቤተ ክርስትያኗ አንድነት፣ ለሐዋርያዊ ተልእኮ መስፋፋት እና መንፈሳዊ እድገት ትኩረት በመስጠት ለቤተክርስያኗ እና ለሀገር ጠቃሚ ውሳኔዎችን አሳልፏል» ብለዋል ።

ቅዱስ ሲኖዶሱ ወቅታዊ ችግሮችን ታሳቢ በማድረግ በመላው ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት የሚያስችል የሰላም ኮሚቴ እንዲሰየም መወሰኑም በመግለጫው ተገልጿል ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ዛሬ በሰጡት መግለጫቸው ቀዳሚ አድርገው ያቀረቡት ሰላምን የተመለከተውን የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔ ነው ። «ወቅታዊውን ችግር ታሳቢ በማድረግ በመላው ሀገራችን ዘላቂ ሰላም ለማምጣት በብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ ካሉ ተቋማት ጋር የሚሠራ በሀገሪቱ መንግሥትም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና የሚኖረው የሰላም ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል ።» ብለዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእምን ጧፍ አብርቶ በጸሎት ስርዓት እንደታደመ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእምን ጧፍ አብርቶ በጸሎት ስርዓት እንደታደመምስል Mulugeta Ayene/AP Photo/picture-alliance

በሰሜኑ ኢትዮጵያ ጦርነት ምክንያት በትግራይ ክልል የሚገኙ ወገኖች ያሉበትን ከፍተኛ ችግር ታሳቢ በማድረግ አስቸኳይ ሰብዓዊ ርዳታ የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶሱ 20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ እንዲደረግ መወሰኑን የገለፁት ፓትርያርኩ በወቅታዊ ችግሮች ምክንያት በመላው ኢትዮጵያ ጉዳት ለደረሰባቸው ሁሉ በጥናት በመለየት ቤተ ክርስትያኗ ሁለንተናዊ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደረግ ውሳኔ ማስተላለፏንም አስታውቀዋል።

ከቤተ ክርስትያኗ ጋር በተያያዘ በኦሮሚያ ክልል የተከሰተው ችግር በንግግር እንዲፈታ ውሳኔ መተላለፉን፣ በኦሮሚያ እና ደቡብ ክልሎች ክፍት በሆኑ አህጉረ ስብከቶች እና በተደራቢነት በተያዙ ሀገረ ስብከቶች ዘጠኝ ኢጲስ ቆጶሳት እንዲሾሙ መወሰኑንም ቅዱስ ፓትርያርኩ አስታውቀዋል ።

ቤተ ክርስትያኗ በስተመጨረሻ የሰላም ጥሪ ለሁሉም አስተላልፋለች ።

ሰለሞን ሙጬ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አዜብ ታደሰ