1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስላምን ለማምጣት መንግስት ምሁራንን ሊያደምጥ ይገባል ተባለ

ቅዳሜ፣ ኅዳር 7 2017

የስራ ጊዜው ሊጠናቅቅ 3 ውራት ብቻ የቀሩት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኢትዬጰያ ከሚገኙ 56 የግል እና የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከተውጣጡ የማህበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት አካሂዷል።በውይይቱ የተሳተፉ ሙህራን እንደገለፁት መንግስት ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ፊቱን ማዞር እና ምሁራንን ማድመጥ ይገባዋል።

https://p.dw.com/p/4n4S2
የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን
የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽንምስል Hanna Demissie/DW

ስላምን ለማምጣት መንግስት ምሁራንን ሊያደምጥ ይገባል ተባለ

ህዳር 06 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኢትዬጰያ ከሚገኙ 56 የግል እና የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከተውጣጡ የማህበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት አካሂደዋል። 
የስራ ጊዜውን ሊጠናቅቅ  3 ውራት ብቻ የቀሩት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን  የሁለቱን ክልሎች ማለትም የአማራ እና ትግራይ ሙሉ በሙሉ አለማወያየቱ እንድሁም በኦሮምያ ክልል  በተወስኑ አካባቢዎች  ብቻ ወይይት ማድረጉ ይታውቃል

በውይይቱ ወቅት ኮሚሽኑ  እንደ እንቅፋት  ያነሳው የፅጥታ ችግር ፣የሀገራዊ  ምክክር ኮምሽኑን አላማ አለመረዳት፣ በኮምሽኑ እምነት ማጣት፣ እና   ጥርጣሪ  የፖለቲካ ቁርጠኝነት ማጣት፣ የሚዲያዎች የተሳሳተ መረጃ  መስጠት እና ሌሎችም  በተፈለገው ልክ እንዳይሄዱ እንዳደረጉዋቸው ተናግረዋል።
ውይይቱን የተካፍሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወካዮች  መንግስት  የሀገርን ስላም  ማስክበር  ሀላፊነት አለበት  ሀገርን እና ህዝብን ወደፊት ለማራመድ  በርግጠኝነት   ፍላጎት ካለው  ወደከፍተኛ  ትምህርት  ተቋማት መምህራን  ፊቱን  ማዞር አለበትም ተብሏል።

ሙህራን በውይይቱ፤ መንግስት  የሀገርን ስላም  ማስክበር  ሀላፊነት አለበት ብለዋል።
ሙህራን በውይይቱ፤ መንግስት  የሀገርን ስላም  ማስክበር  ሀላፊነት አለበት  ሀገርን እና ህዝብን ወደፊት ለማራመድ  በርግጠኝነት   ፍላጎት ካለው  ወደከፍተኛ  ትምህርት  ተቋማት መምህራን  ፊቱን  ማዞር አለበት ብለዋል።ምስል Hanna Demissie/DW

DW ያነጋገራቸው  የከፍተኛ ትምህርት ተቋም  ለውይይት መቅረቡ ትክክል ነው  የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኢትዮጵያ ለተፈጠረው ችግር ሁሉ መፍትሔ ባያመጣም የውይይት ባህልን ማስጀምር  መቻሉ በራሱ ትልቅ ነገር እንደሆነም ገልጸዋል።

ከፍተኛውን መቀመጫ ቁጥር በያዘውየፓለቲካ ፓርቲ አመራር ተጠቁመው በአብላጫ ድምፅ የተመረጡ 11 ኮምሽኖችን ይዞ ወደ ስራ የገባው የምክክር ኮምሽን በጀቱ ሙሉ በሙሉ የሚደጎመው በመንግስት  ሆኖ ሳለ ሀገራዊ ኮምሽኑ  በርግጥ መንግስት የማይፍልገውን ሀሳብ ለማስተናገድ ያለው አቅም  አሳማኝ  ባለመሆኑ ማህበረሰቡ ቢጠራጠር  አይፈረድበት  የሚል ሀሳቦች ቀርበዋል። በውይይቱ ኮምሽኑን የሚመለከቱ ጥያቂዎች ምላሽ በመስጠት የተቀሩትን ለሚመለካተው አካል እንደሚያቀርብ አሳውቆዋል።

ሙሉ ዝግጅቱን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።

ሀና ደምሴ
ፀሀይ ጫኔ