1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስለ ሀገራዊዉ ምክክር የተሰበሰበ የህዝብ አስተያየት

ማክሰኞ፣ ሰኔ 11 2016

በመንግሥት ከተሰየመ ሁለት ዓመታትን ያስቆጠረው ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን «ኢትዮጵያ እየመከረች ነው» በሚል መሪ ቃል አዲስ አበባ ላይ የመጀመሪያው ምዕራፍ ምክክርን አካሂዷል። የኮሚሽኑዋና ኮሚሽነር "አዲስ ውጤት ለማግኘት፣ በአዲስ መንገድ መሄድ አስፈላጊ እንደመሆኑ" ሁሉም እኩል ተሳትፊ የሚደረግበት ታሪካዊ ያሉት መድረክ መፈጠሩን ገልፀዋል።

https://p.dw.com/p/4hCPE
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምክክር
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምክክርምስል Seyoum Getu/DW

ስለ ኢትዮጵያ የሀገራዊ ምክክር የህዝብ አስተያየት

በመንግሥት ከተሰየመ ሁለት ዓመታትን ያስቆጠረው ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን «ኢትዮጵያ እየመከረች ነው» በሚል መሪ ቃል አዲስ አበባ ላይ የመጀመሪያው ምዕራፍ ምክክርን አካሂዷል። የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ "አዲስ ውጤት ለማግኘት፣ በአዲስ መንገድ መሄድ አስፈላጊ እንደመሆኑ" ሁሉም እኩል ተሳትፊ የሚደረግበት ታሪካዊ ያሉት መድረክ መፈጠሩን ገልፀዋል። 

"በልዩነታቸው አንድ የሆኑትን ሕዝቦቻችንን፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያበጡ በመጡ የሀሳብ ልዩነቶች ሀገራችንን ከልቀት ወደ ድቀት፣ ከፍቅር ወደ ጥላቻ፣ ከአንድነት ወደ መነጣጠል፣ ከሰላም ወደ ጦርነት እየጎተቷት የመጧትን ምክንያቶች ነቅሶ በማውጣት፤ በሰከነ እና በተረጋጋ እንዲሁም ከበሬታ ባለበት ሁኔታ ተቀራርቦ በመመካከር ወደ መግባባት መድረስ ምንም አማራጭ የሌለው ብቸኛ ሀገራዊ መፍትሔ መሆኑን ግንዛቤ ወስደናል ብየ አምናለሁ።»
አዲስ ውጤት ለማግኘት፣ በአዲስ መንገድ መሄድ አስፈላጊ ነው - ዋና ኮሚሽነር 
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ "አዲስ ውጤት ለማግኘት፣ በአዲስ መንገድ መሄድ አስፈላጊ እንደመሆኑ" ሁሉም እኩል ተሳትፊ የሚደረግበት ታሪካዊ ያሉት መድረክ መፈጠሩን ገልፀዋል።

"በልዩነታቸው አንድ የሆኑትን ሕዝቦቻችንን፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያበጡ በመጡ የሀሳብ ልዩነቶች ሀገራችንን ከልቀት ወደ ድቀት፣ ከፍቅር ወደ ጥላቻ፣ ከአንድነት ወደ መነጣጠል፣ ከሰላም ወደ ጦርነት እየጎተቷት የመጧትን ምክንያቶች ነቅሶ በማውጣት፤ በሰከነ እና በተረጋጋ እንዲሁም ከበሬታ ባለበት ሁኔታ ተቀራርቦ በመመካከር ወደ መግባባት መድረስ ምንም አማራጭ የሌለው ብቸኛ ሀገራዊ መፍትሔ መሆኑን ግንዛቤ ወስደናል ብየ አምናለሁ"

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን ምስል Seyoum Getu/DW

የኮሚሽኑ የሥልጣን ጊዜ 

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በምክክር ሂደቱ ተሳታፊዎች በሚናገሩት፣ በሚያፈልቁት ሀሳብ፣ በሚሰጡት አስተያየት ምንም ችግር እንደማይገጥማቸው ዋስትና እንደሚሰጥ፣ በዚህ ዙሪያ ከመንግሥት ጋር ስምምነት እንዳለውም አስቀድሞ አስታውቋል። ኮሚሽኑ የሥልጣን ጊዜው ሊጠናቀቅ ዘጠኝ ወራት ይቀሩታል። 

ኢትዮጵያ ውስጥ በልሂቃን መካከል በአገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት አለመኖሩ፤ በመካከላቸው ያለው አለመተማመን እና ጥርጣሬ የዴሞክራሲ የሽግግር ሂደቱን ፈታኝ በማድረጉ አስፈላጊነቱ ታምኖበት የተጀመረው እና በኢትዮጵያ ለሚስተዋለው የፖለቲካ ቀውስ፤ የሰላም መደፍረስ እና የፀጥታ አለመረጋጋት እልባት ይሰጣልተብሎ ከመነሻው ተስፋ የተጣለበት የብሔራዊ ምክክር መድረክ ምን ያህል እርምጃ እየሁደ ነዉ? የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን አስተያየት አሰባስበናል። 

ሃና ደምሴ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ 
አዜብ ታደሰ