1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዜጎች ሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ጠየቀ

ሐሙስ፣ መጋቢት 5 2016

ፓርቲው የዜጎች ግዲያ መበራከትና ፍትህ አለመስፈን በክልሉ በሰኔ ይካሄዳል በተባለው ምርጫ ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር ይችላል የሚል ስጋቱን ገልጿል። የከፍተኛ ፖሊስ መኮንን ጨምሮ በግለሰቦች ላይ በመተከል ዞን እና አሶሳ ዞን ግድያ የፈጸሙ ወደ ህግ አለመቅረባቸው ስጋት የፈጠረና የፍትህ አካላትን ተአማኒነትንም ጥያቄ ውስጥ ያስገባ ድርጊት ነው ብሏል፡፡

https://p.dw.com/p/4dWmP
የግለገል በለስ ከተማ
የግለገል በለስ ከተማ ምስል privat

የዜጎች ሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ጠየቀ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት ወራት በግለሰቦች ላይ የሚፈጸሙ ግዲያዎች መበራከታቸውን በክልሉ ውስጥ የሚንቃቀሰው የቦሮ ዲሞክራቲክ ፓርቲ አስታወቀ፡፡ ፓርቲው ትናንት ባወጣው መግለጫ የዜጎች ግዲያ መበራከት እና ፍትህ አለመስፈን በክልሉ ሰኔ ወር ይካሄዳል ተብሎ በታሰበው ምርጫ ላይ ተጽህኖ ሊያሳድር ይችላል የሚል ስጋቱን ገልጸዋል፡፡ ግዲያው አንድ የከፍተኛ ፖሊስ መኮንን ጨምሮ በግለሰቦች ላይ በመተከል ዞን እና አሶሳ ዞን ውስጥ ግዲያ እና እገታዎች መፈጸማቸውን ገልጸዋል፡፡ ገዳዩች ወደ ህግ አለመቅረባቸው በህብተሰቡ ውስጥ ስጋት መፈጠሩንና የፍትህ አካላት  ተአማኒነትን ጥያቄ ውስጥ ያስባ ድርጊት ነው ብሏል፡፡ የክልሉ ፍትህ ቢሮ በበኩሉ የግዲያ ወንጀል ጉዳዮችን እየመረመረ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የምርጫ ጥሪ በቦሮ ፓርቲ

በግለሰቦች ላይ የሚፈጸሙ ግዲያዎች መበራከት

የቦሮ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ በበትናትነው ዕለት ባወጣው መግለጫው እንዳስታወቀው ባለፉት ሁለት ወራት በግልገል ከተማ አንድ ከፍተኛ የፖሊስ አመራር ባልታወቁ ሰዎች መገደሉን፣ በፓዌ አንድ የህግ ባለሙያ እንዲሁም ባለፈው ሳምንት የካቲት 27/2016 ዓ.ም ደግሞ በአሶሳ ከተማ አቅራባቢያ ትግዕስት ጥላሁን የተባለች የጤና ባለሙያ በግፍ መገደሏዋን የፓርቲው  የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር መብራቱ አለሙ ለዶይቼቨለ ተናግረዋል፡፡ እነዚህ ድርጊቶች በጊዜ እልባት ባለማግኘታቸው በክልሉ ይካሄዳል ተብሎ የታቀደውን ምርጫ ላይ ተጽህኖ ሊያደስር ይችላል ብሏል፡፡ ከግለሰቦች ግዲያም በተጨማሪ በመተከል ዞን ማንዱራ የተባለ  ወረዳ ውስጥ የታጣቂዎች እንቅስቃሴ መኖሩን አመልክተዋል፡፡ ይሄም በክልሉ በሰኔ ወር ለማካሄድ የታቀደውን ምርጫ ሊያውክ ስለሚችም ከወዲው መንግስት የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል፡፡የቦሮ ዴሞክራክ ፓርቲ የምርጫ ምልክቱን እና ማኒፌስቶውን አስተዋወቀ


በካማሺ ዞን ሴዳል በተባለ አካባቢም ከሱዳን ተሻገሩ የተባሉ zaይሎች ከሳምንት በፊት በዜጎች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውንም ፓርው አክልዋል፡፡ እነዚህን ድርጊቶች የፈጸሙ አካላት እስካሁን ወደ ህግ አለመቅረባቸውን በመግለጽ የክልሉ መንግስት የዜጎች ደህንነት ማስጠበቅና ወንጀሎችን ወደ ህግ ማቅርብ እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡ የዚህ ፍትህ መጓተት በህብረተሰቡ ዘንድ የፍትህ ተቋማት ላይ አመኔታ ማጣትን እያመጣ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ 

የግልገል በለስ ከተማ
የግልገል በለስ ከተማምስል privat


የግድያ ወንጀሎችን ጉዳይ በምርመራ ሂደት ላይ ይገኛል


የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፍትህ ቢሮ በበኩሉ በተለያዩ አካባቢዎች ተፈጽመዋል የተባሉ ግዲያ ወንጀሎችን በማጣራት ላይ እንደሚገኝ ለዶቸቬለ ተናግረዋል፡፡ በክልሉ ፍትህ ቢሮ ዐቃቤ ህግ የሆኑት አቶ ጃለታ ፉፋ አሶሳ እና ግልገል በለስ ከተማ ጨምሮ በሰዎች ላይ የተፈጸሙ ግዲያዎችን ጉዳይ ቢሮአቸው ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡ ድርጊቱ ውስብስብ በመሆኑ የድርጊቱ ፈጻሚዎችን በቀላሉ ለማግኘት ረጅም ጊዜ መውሰዱንም አክለዋል፡፡ 

የቦሮ ዴሞክራክ ፓርቲ
በፓርቲው መግለጫ የተጠቀሱ ከታጣቂዎች እንቀስቃሴ በክልሉ ሊካሄድ የታሰበውን ምርጫ ሊያደናቅፍ ይችላል ሲል የቀረበውን ስጋት አስመልክቶ ማብራሪያ እንዲሰጡን  ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር፣ ከክልሉ ሠላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ እንዲሁም ከመተከል ዞን አስተዳዳሪ መረጃ ለማግኘት ያደረኩት ተደጋጋሚ ጥረቶች ስልካቸውን ባለማንሳታቸው አልተሳካም፡፡ በክልሉ ሰላም መሻሻልን ተከትሎ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከዚህ ቀደም ምርጫ ባልካሄደባቸው አካባቢዎች ሰኔ 6/2016 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ ማቀዱን የካቲት 26/2016 ዓ.ም ይፋ ባደረገው መረጃ አመልክተዋል፡፡
ነጋሳ ደሳለኝ 
ኂሩት መለሰ
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር