1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ እግር ኳስ የምድብ «ሠ» የሞት ሽረት ግጥሚያ

ረቡዕ፣ ሰኔ 19 2016

በጀርመን አዘጋጅነት የጀመረው 17ኛው የአውሮጳ እግር ኳስ ጨዋታ ዛሬም ቀጥሎ ምሽቱን አራት ግጥሚያዎች ይኖራሉ ። ወደ 16ቱ የጥሎ ማለፍ ዙር ለማለፍ በሚደረጉ የምሽቱ የመጨረሻ ጨዋታዎች፦ ሎቫኪያ ከሩማንያ እንዲሁም ዩክሬን ከቤልጂየም ጋር ጨዋታቸው በአቻ ተጠናቅቋል ። ስሎቫኪያ ከሩማንያ አንድ እኩል ፤ ዩክሬን ከቤልጂየም ዜሮ ለዜሮ ።

https://p.dw.com/p/4hYKn
Deutschland | Fußball Europameisterschaft 2024 | Trikot mit Check24 Logo
ምስል Dennis Duddek/Eibner Pressefoto/picture alliance

በጀርመን አዘጋጅነት የጀመረው 17ኛው የአውሮጳ እግር ኳስ ጨዋታ ዛሬም ቀጥሎ ምሽቱን አራት ግጥሚያዎች ይኖራሉ ። ወደ 16ቱ የጥሎ ማለፍ ዙር ለማለፍ በሚደረጉ የምሽቱ የመጨረሻ ጨዋታዎች፦ ስሎቫኪያ ከሩማንያ እንዲሁም ዩክሬን ከቤልጂየም ጋር ጨዋታቸው በአቻ ተጠናቅቋል ። ስሎቫኪያ ከሩማንያ አንድ እኩል ፤ ዩክሬን ከቤልጂየም ዜሮ ለዜሮ ።

ከሰአታት በኋላ ደግሞ ጂዮርጂያ ከፖርቹጋል እንዲሁም ቼክ ከቱርክ ጋ ከተጋጠሙ በኋላ ወደ ቀጣይ ዙር ያለፉት 16ቱ አጠቃላይ ቡድኖች ይለያሉ ።

ከዛሬ ግጥሚያዎች በምድብ «ሠ» የሚገኙት አራቱም ሃገራት፦ ማለትም ሮማኒያ፤ ቤልጂየም፤ ስሎቫኪያ እና ዩክሬን እያንዳንዳቸው አራት ነጥብ ያላቸው መሆኑ ጨዋታውን እጅግ አጓጊ አድርጎታል ።

ከምድብ «ረ» ፖርቹጋል በ6 ነጥብ ትመራለች ። ቱርክ በ3 ነጥብ ትከተላለች ። ቼክ እና ጆርጂያ አንድ ነጥብ አላቸው የሚለያዩት በግብ ክፍያ ነው ።

የጨዋታው ዳኛ
የቤልጂየም እና ሩማኒያን ጨዋታው የመሩት ዳኛምስል Kirill Kudryavtsev/AFP/Getty Images

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ