የህዳሴ ግድብ አራተኛ ዙር የውኃ ሙሌት ተጠናቋል መባሉ እና አንደምታዉ
ሰኞ፣ ጳጉሜን 6 2015ኢትዮጵያ በግዙፉ አባይ (ናይል) ወንዝ ላይ የምታስገነባው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አራተኛው ዙር (ዓመት) የዉኃ ሙሌት መጠናቀቅ በትናንትናው እለት ተገልጿል፡፡ ይህ የተገለጸው ረዘም ላለ ጊዜ በግድቡ ዙሪያ ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የሚያደርጉት የሦስትዮሽ ድርድር ተቋርጦ ከቀጠለ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ነው፡፡ሕዳሴ ግድብ፤ የግብጽና ሱዳን ወታደራዊ ስምምነት ስጋት
ኢትዮጵያ አራተኛው ዙር የሕዳሴ ግድብ የዉኃ ሙሌት ማካሄዷን ተከትሎ ግብጽ የኢትዮጵያ ተግባር የመርሆች ስምምነትን የጣሰ ነው ብላለች። የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት በፌስቡክ ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ የግድቡን ዉኃ ሙሌት ያከናወነችው ሦስቱ አገራት መጋቢት 14 ቀን 2007 ዓ/ም የተፈራረሙትን ስምምነት ይጥሳል ብላለች። የግድቡ የዉኃ አሞላል ሂደት ተቋርጦ ለቀጠለው ድርድር ምን አንድምታ ይኖረው ይሆን?
በርካታ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃንም የሕዳሴው ግድቡ “አራተኛና የመጨረሻ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቋል” ሲሉ በትናንትናው እለት ዘግበዋል፡፡ ዶይቼ ቬለ ስለግድቡ አሞላል ሂደትና ስለ ዉኃ ይዘት መጠኑ ከግድቡ ግንባታ ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ እንዲሁም ከዉኃ እና ኢኒርጂ ሚኒስቴር ባለስልጣናት ተጨማሪ ማብራሪያን ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልሰመረም፡፡ በድንብር ተሻጋሪ ዉኃ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና የዉኃ ሚኒስቴርን የሚያማክሩት እንዲሁም የህዳሴ ግድቡ ተደራዳሪ ቡድን ኮሚቴ አባል ሆነው ሲሰሩ የቆዩት ዶ/ር ያዕቆም አርሳኖ እንዳሉን ግን ትናንት መጠናቀቁ የተበሰረው የአራተኛ ዙር የዉኃ ሙሌት እንጂ የግድቡ የዉኃ አሞላል ሂደቱ ገና የሚቀጥል ነው ብለዋል፡፡ “ትናንት የተገለጸው የግድቡ አራተኛ ዙር የዉኃ ሙሌት ነው እንጂ የግድቡ ግንባታና ዉኃ ይዘት አቅሙ ገና ይቀጥላል፡፡”የህዳሴ ግድብ ድርድርና የኢትዮጵያ ፍላጎት
ሌላው የህዳሴ ግድቡ ተደራዳሪ ቡድን አባልና የሃይድሮ ፖለቲክስ ምሁሩ ኢንጂነር ጌድዮን አስፋው ትናንት የመጨረሻ የተባለው የአራተኛው ዙር የግድቡ አመላል ሂደት እንጂ የግድቡ ግንባታ እና የዉኃ አያያዝ መጠኑ ገና የሚቀጥል ነው ብለዋል፡፡ “ባለፉት ወራት ደረጃ በደረጃ ሲካሄድ የነበረው የዉኃ ሙሌት ሂደቱ መጨረሻው ነው ለማለትነ ነው፡፡ ሌሎች ሙሊቶች ወደፊት ከግብታው ጋር የሚቀጥሉ ይሆናል፡፡”የህዳሴ ግድብ እና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ
እስካሁን በዲዛይኑ እንደታወቀው 74 ቢሊየን ኪዩብክ ዉኃን ሊይዝ እንደሚችል ታምኖ እየተገነባ ያለው የህዳሴ ግድቡ የዉኃ አሞላል ሂደት እስከ 7 ዓመትም ሊወስድ እንደሚችል ከዚህ ቀደም በተቀመጠው እቅድ መታየቱን የግድቡ ተደራዳሪ ቡድን ኮሚቴ አባል ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት ዶ/ር ያዕቆም አንስተዋልም፡፡ “ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ በኩል የተቀመጠውና በግብጽም በኩል ተቀባይነት አግኝቶ የነበረው የግድቡ አመላል ሂደት እስከ 7 ዓመታት ሊሄድ እንደሚችል ነው፡፡” እስካሁን የዉኃ አመላል ሂደቱ ከአጋማሽ በላይ መሄዱንም ዶ/ር ያዕቆብ እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡ እንደ ዶ/ር ያዕቆም ማብራሪያ የግድቡ አመላል ሂደቱ እንደ ግድቡ ግንባታ ፍጥነትና የዉኃ ግንት ሁኔታ የሙሌት ሂደቱ ከ7 ዓመታትም ሊያልፍ ይችላል፡፡
ለዓመታት ያወዛገበው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር ረዘም ላለ ጊዜ ከተቋረጠ በኋ ከጢቂት ሳምንታት በፊት የግብጽ፣ ኢትዮጵያ እና ሱዳን ተወካዮች በተገኙበት በካይሮ መጀመሩ የሚታወስ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ግን በግድቡ ዉኃ አሞላልን ጨምሮ ሌሎች ሂደቶች ላይ መቋጫ ስምምነት ሳይደረስ ከዚህ በፊትም ባስቀመጠችው አቅጣጫ አራተኛውን የግድቡ ዉኃ ሙሌትን ይፋአድርጋለች፡፡ ይህ ክስተት እንደገና የተጀመረው ድርድር ላይ አሉታዊ ተጽእኖ አይፈጥርም ይሆን የተባሉት ኢንጂነር ጌድዮን አስፋው፤ “ድርድር በተደረገ ቁጥር የሙሌቱ ጉዳይ እንደ አዲስ አይነሳም” ብለዋል፡፡
ዶ/ር ያዕቆብ አርሳኖ በፊናቸው በዚህ ላይ ባከሉት አስተያየታቸው “ኢትዮጵያ በራሷ መንገድ ስትሄድ የግብጽን ጥቅም የመጉዳት እቅድ የላትም” ብለዋል፡፡
የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫት አቅም ከፍ በማድርግ ኢኮኖሚዋን ከመደገፍ ባሻገር ድንበር ተሻጋሪ ወንዝን የታችኛው ተፋሰስ አገራት ጥቅም ሳትጎዳ የመጠቀም ዲፕሎማሲያዊ ክዋኔን የሚያሳይም ይባልለታል፡፡ለታላቁ የህዳሴ ግድብ የደን ምንጣሮ 4 ወራት የተሻገረው የክፍያ ጥበቃ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እሳቸውን ጨምሮ በርካታ የአገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት የህዳሴ ግድቡ የሚገነባበትን ስፍራ ከጎበኙበት ፎቶ ጋር ባጋሩት መረጃ “ብዙ ፈተና ነበረው፤ ወደኋላ እንድንመለስ ብዙ ተጎትተን ነበር፤ በውጭ ጫና ነበረብን፤ ከፈጣሪ ጋር የመጣውን ሁሉ ተቋቁመን ለዚህ ደርሰናል” ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የዳገቱ ጫፍ ላይ ደረስን እንጂ ዳገቱን ወጥተን አልጨረስነውም” በማለትም ለግድቡ የሚደረጉ ማናቸውም ድጋፎች እስከ ፍጻሜው እንድንቀጥል በመልእክታቸው ጠይቀዋል፡፡
ሥዩም ጌቱ
አዜብ ታደሰ
ታምራት ዲንሳ