1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ6ኛው ዙር ቀሪ እና የማሟያ ምርጫ ሊደረግ ነው

ቅዳሜ፣ ሰኔ 15 2016

አሁን ባለው ተጨባጭ ሁናቴ ምርጫ ለማስፈፀም የፀጥታ ችግር የሌላለባቸው የተባሉት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ አፋር፣ ሶማሌ እና ማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ 1112 መደበኛ እና 34 የተፈናቃይ የምርጫ ጣቢያዎች ድምፅ ይሰጣል ተብሏል።

https://p.dw.com/p/4hO5X
Äthiopien | Erklärung vom Nationaler Wahlausschuss
ምስል Solomon Muchie/DW

ነገ እሁድ በሚደረገው የማሟያ ምርጫ ላይ የምርጫ ቦርድ መግለጫ

6ኛው ዙር ቀሪ እና የድጋሚ ምርጫ

በፀጥታ መናጋትና በሰላም እጦት ምክንያት 6ኛው ዙር ምርጫ ሳይደረግባቸው በቀሩት አራት ክልሎች ነገ እሑድ ሰኔ 16 ቀን 2016 ዓ. ም ምርጫ ይደረጋል።

አሁን ባለው ተጨባጭ ሁናቴ ምርጫ ለማስፈፀም የፀጥታ ችግር የሌላለባቸው የተባሉት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ አፋር፣ ሶማሌ እና ማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ 1112 መደበኛ እና 34 የተፈናቃይ የምርጫ ጣቢያዎች ድምፅ ይሰጣል ተብሏል።

ቦርዱ ዛሬ በሰጠው መግለጫ በምርጫው 12 የፖለቲካ ድርጅቶች ይሳተፋሉ።

ኢትዮጵያ አሁን ከምትገኝበት የፀጥታ ሁኔታ አንፃር "ምርጫ ለማካሄድ አስቻይ ኹኔታዎች እንደሌሉ" በመግለጽ፤ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጀት (መኢአድ) እና እናት ፓርቲ ከምርጫው ራሳቸውን ማግለላቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ የምርጫ ፣የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር ማሻሻያ አዋጅና ፋይዳው

ከሦስት ዓመታት በፊት በተከናወነው ስድስተኛው ሀገር አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ የፀጥታ መናጋትና የሰላም እጦት በብዙ የሀገሪቱ አካባቢዎች ምርጫ እንዳይከናወን አድርጓል።

የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሜላተወርቅ ኃይሉ ዛሬ አመሻሽ ላይ በሰጡት መግለጫ ነገ ጥዋት 12 ሰዓት የሚጀምረው ምርጫ ሰላማዊ እና ቀልጣፋ መሆኑን የሚያረጋግጥ 29 ቡድን ተቋቁሟል። ሦስት ዓመታት ባልመረጡት መንግሥት የተመሩ ሕዝቦች አሁን ለሁለት ዓመታት መምረጣቸው ለውጡ ምንድን ነው? የሚለውን ጥያቄ ጠይቀናቸዋል። "መብት ስለሆነ" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ሁለት ፓርቲዎች ከቀሪ እና ድጋሚ ምርጫ ራሳቸውን ስለማግለላቸው 

ምርጫ ለማካሄድ አስቻይ ኹኔታዎች እንደሌሉ በመጥቀስ ምርጫዉ እንደማይሳተፉ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጀት (መኢአድ) እና እናት ፓርቲዎች ገልጸው ነበር። ይህ ምን ማለት ነው የተባሉት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ "ፓርቲዎቹ ምርጫውን ለማድረግ አስቻይ ሁኔታ የለም የሚሉበትን ሁኔታ የሚያሳይ ተጨባጭ ማስረጃ እስካሁን አላቀረቡም። በቦርዱ እምነት ግን ምርጫውን ለማድረግ አስቻይ ሁኔታዎች አሉ" ብለዋል።

የበኒ ሻንጉል ጉሙዝ ክልል የምርጫ ዝግጅትና የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ቅሬታ

በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ምርጫ ያልተደረገባቸው ቦታዎች ጉዳይ 

በስድስተኛው ሀገር አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ ፤ ምርጫው አሁን ይደረግባቸዋል ከተባሉት አራት ክልሎች በተጨማሪ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎችም ምርጫ ያልተደረገባቸው ሥፍራዎች ጥቂት አይዱሉም። የትግራይ ክልልም የራሱ ሌላ መልክ ቢኖረውም እንዲሁ። ስለዚህ ጉዳይም ዶቼ ቬለ የቦርዱን ሰብሳቢ ጠይቋቸዋል። "ሰላም፣ አስቻይ ሁኔታ ሲኖር" ሕግና ሥርዓትን ጠብቆ ምርጫ ይደረጋል የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

አስተያየት በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነምግባር አዋጅ ማሻሻያ ላይ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ባሉ 40 የምርጫ ጣቢያዎች ድምፅ አይሰጥም

ቦርዱ ነገ ምርጫ ከሚደረግባቸው ቦታዎች ውስጥ በሶማሊ ክልል በእለቱ የምርጫ ካርድ ወስደው የሚመርጡባቸው ቦታዎች አሉ ብሏል። በሌላ በኩል ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ባሉ አርባ የምርጫ ጣቢያዎች አሁንም የፀጥታ ሥጋት ያለባቸው ወይም አስቻይ ሁኔታ የሌለባቸው በመሆኑ ደጋሜ ምርጫ አይደረግም ተብሏል።

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ