1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ ወታደሮቿ ድንበር አቋርጠዋል የሚለውን የሶማሊያን ውንጀላ አስተባበለች

ሐሙስ፣ ሰኔ 20 2016

የኢትዮጵያ ወታደሮች ድንበሬን ጥሰው ወደ ግዛቴ ገብተዋል በሚል ጎረቤት ሀገር ሶማሊያ በተባበሩት መንግሥታት መድረክ ላይ ያቀረበችው ክስ ሀሰት ነው ሲል የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ነቢዩ ተድላ እንዳሉት ሶማሊያ በኢትዮጵያ ላይ ያቀረበችው ክስ " መሰረተ ቢስ ክስ ነው"።

https://p.dw.com/p/4hZqL
Ethiopia Ministry of Foreign affairs podium | Addis Abeba, Ethiopia
ምስል Solomon Muchie/DW

ኢትዮጵያ ወታደሮቿ ድንበር አቋርጠዋል የሚለውን የሶማሊያን ውንጀላ አስተባበለች

ሶማሊያ ስለ ኢትዮጵያ ወታደሮች ያቀረበችው ክስ ትክክል አይደለም መባሉ

በሶማሊያ ወቅታዊ ጉዳይ በመከረው የመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ጉባኤ ላይ የሶማሊያ ተወካይ የሆኑት ግለሰብ፣ የኢትዮጵያ ጦር ኢትዮጵያ ከሶማልያ ጋር በምትዋሰንባቸው አካባቢዎች በሕገ-ወጥ መንገድ የሀገራቸውን ድንበር ጥሶ ከመግባት ባለፈ ከሀገሪቱ የፀጥታ ኃይላት ጋር የተኩስ ልውውጥ ማድረጉንም ተናግረው ነበር።

ዘገባዎች እንዳመለከቱት ከሆነ ይህ ክስተት ቅዳሜ እለት የሆነ ሲሆን የኢትዮጵያ ወታደሮች ሒራን በተባለው የሶማሊያ ክልል ዘልቀው በመግባት አል ሸባብ ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ያሳያል።

አል ሸባብ ሰፊውን የሶማልያ ክፍል ተቆጣጥሮ በሚገኝባት ሶማሊያ ውስጥ በሀገሪቱ ሰላም በማስከበር ላይ ላለው የአፍሪቃ ሕብረት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ (ATMIS) የጦር ሠራዊት ካዋጡ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ እስከ ሦስት ሺህ የሚደርሱ ወታደሮቿ የቡድኑን ጥቃት በመመከት ላይ ይገኛሉ።የኢትዮ-ሶማሊያ ዲፕሎማሲያዊ ትኩሳት ወዴት ?

ይሁንና የኢትዮጵያ ወታደሮች የተባለውን ድንበር ጥሶ የመግባት ድርጊት አለመፈፀማቸውን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ነቢዩ ተድላ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።

አምባሳደር ነቢዩ ተድላ፤ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ
አምባሳደር ነቢዩ ተድላ፤ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ምስል Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia

ኢትዮጵያ በቀጣይ በሶማሊያ ሰላም ማስከበር ላይ የሚኖራት ሚና

በሌላ በኩል ሶማሊያ ውስጥ በቅርቡ ተልእኮውን የሚጠናቀቀው "የአፍሪካ ሕብረት የሽግግር ተልዕኮ በሶማሊያ" የተባለውን ጥምር ኃይልን ተክቶ በሚገባው ዓለም አቀፍ ሰላም አስከባሪ ኃይል ውስጥ፣ የኢትዮጵያ ሠራዊት ስለሚኖረው ተሳትፎ ከሶማሊያ መንግሥት፣ ከአፍሪካ ሕብረትም ሆነ ከተባበሩት መንግሥታት የደረሰው ምንም ነገር እንደሌለ ቃል ዐቀባዩ አስታውቀዋል።

ከኢትዮጵያ ጋር ውዝግብ ውስጥ በገባቸው ሶማሊያ በአፍሪካ ሕብረት የፀጥታ እና ሰላም ምክር ቤት ውሳኔ አግኝቶ፣ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ሲፀድቅ የሀገሪቱን ዋና ዋና መሠረተ ልማቶችን እና የመንግሥት ተቋማትን ለመጠበቅ ይሰማራል ተብሎ በሚጠበቀው አዲስ አለም አቀፍ ኃይል ውስጥ የኢትዮጵያ ወታደሮች እንዳይካተቱ የሶማሊያ መንግሥት ከዚህ ቀደም ብሎ አቋሙን ይፋ አድርጓል።የኢትዮ-ሶማሊያ ዲፕሎማሲያዊ ትኩሳት ወዴት ?

ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶማሌላንድ ጋር  የወደብ ኪራይ ስምምነት መፈጸሟ ከሶማሊያ ጋር ዲፕሎማሲያዊ መሻከር ውስጥ አስገብቷታል።
ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶማሌላንድ ጋር ከወራት በፊት የጦር ሰፈር ምስረታ እና የወደብ ኪራይ ስምምነት መፈጸሟ ከሶማሊያ ጋር ዲፕሎማሲያዊ መሻከር ውስጥ አስገብቷታል። ምስል MICHELE SPATARI/AFP

የኢትዮጵያ መንግሥት ይህ የሶማሊያ የፀጥታ አማካሪ ናቸው በተባሉ ሰው ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የጀመረችውን የወደብ ጉዳይ የተመለከተ እንቅስቃሴዋን ካላቆመች አዲስ በሚሰማራው ሰላም አስከባሪ ኃይል ሀገራቸው የኢትዮጵያን ወታደሮች እንደማትቀበል መግለፃቸውን ኢትዮጵያ እና ራስ ገዝ ሶማሊላንድ ከተፈራረሙት የመግባቢያ ሰነድ ስምምነቱ ጋር ምንም የሚያያይዘው ነገር እንደሌለ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢዩ ተድላ ከዚህ በፊትም ዛሬም ደግመው ተናግረዋል።የኢትዮ-ሶማሊያ ዲፕሎማሲያዊ ትኩሳት ወዴት ?

የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ማሳሰቢያ

ከዚሁ ከሶማሊያ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የተደረገውን የወደብ ተጠቃሚነት የሚያስገኝ የመግባቢያ ስምምነት ትታዋለች ወይም ሰርዛዋለች በሚል ትናንት በማሕበራዊ መገናኛ ዐውታሮች መሰራጨቱን ተከትሎ ሕዝብ እየተሰራጩ ካሉ ሀሰተኛ ይዘቶች እንዲጠነቀቅ ሲል መክሯል።

ጽሕፈት ቤቱ አካባቢያዊ፣ ክልላዊ እና አለምአቀፋዊ ጉዳዮችን በይፋዊ የመገናኛ ዘዴዎች ብቻ የሚያሰራጭ መሆኑንም አስታውቋል።

 

ሙሉ ዝግጅቱን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።

 

ሰለሞን ሙጨ

ነጋሽ መሀመድ

ፀሀይ ጫኔ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ