1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በስምምነቱ ላይ የተነሱ ተቃውሞዎችና የተሰጡ አስተያየቶች

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 24 2016

የአውሮጳ ህብረት የውጭ ግንኑነት ቢሮ ትናንት በዚሁ ስምምነት ላይ ባወጣው መገለጫም፤ የሚደረጉ ስምምነቶች የሶማሊያን ሉአላዊነትና የግዛት አንድነት፣ የአፍሪቃ ህብረትን ቻርተርና የመንግስታቱ ድርጅትን መርኆች ከግምት ውስጥ ያስገቡ መሆን አለባቸው ብሏል። እነዚህ መርሆችና ድንጋጌዎች ለአካባቢው ሰላምና መረጋጋት ቁልፍ መሆናቸውንም አስታውቋል።

https://p.dw.com/p/4aphf
EU-Ungarn | Sitz der EU-Kommission in Brüssel
ምስል Yves Herman/REUTERS

በስምምነቱ ላይ የተነሱ ተቃውሞዎችና የተሰጡ አስተያየቶች

አወዛጋቢው የመግባቢያ ስነድ


ባለፈው ሰኞ በኢትዮጵያና ሶማሊላንድ የተፈረመውና ለኢትዮጵያ የባህር በር የሚያስገኝ ነው የተባለው የመግባቢያ ሰነድ እያወዛገበና ካንዳንዶችም ተቃዉሞ እየተሰማበት ነው። ከትናንት ወዲያ ሰኞ በአውሮፓውያኑ አዲስ አመት መባቻ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሀመድና የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲመሪ፤ ኢትዮጵያ በበርበራ ወደብ የባህር ህይል ሰፈር ለመገንባትና የንግድ ወደብ ለማግኘት የሚያስችላትንና በምትኩ ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ የነጻ አገርነት  እውቅና እንድትሰጥ፤  የሚያደርግ የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት መድረሳቸውን ሁለቱም በፊርማቸው አረጋግጠዋል።


የስምምነቱ ይዘት

በፊርማው ስነ ስርዓት ላይ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና የሶማሌላንዱ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ መሪ  በየብኩላቸው በሰጧቸው አስተያየቶች ስምምነቱን ታርካዊና የሁለቱንም ህዝቦች ጥቅም የሚያስጠብቅ ሲሉ አወድሰውታል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ስምምነቱ፤ በትብብር ለመልማት፤ ለማደግና የጋራ ሰላምን  ለማረጋገጥ የሚያስችል የጋራ ሰነድ ነው ሲሉ፤ የሶማሊያው ፕሬዳንት ደግሞ በስምምነቱ የተደሰቱ መሆኑን አውስተው በስምምነቱ መሰረትም አገራቸው ለኢትዮጵያ የባህር በር የምትሰጣት መሆኑን አስታውቀዋል። የድሬደዋ አስተዳደር የጠራው የድጋፍ ሰልፍ“በተደረሰው ስምምነት በጣም ተደስተናል፤ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይንም እናመስግናለን። በስምምነታችን መስረት ከባህራችን 20 ኪሎሜትር ድረስ የሚዘልቅ  መጠን እንሰጣለን፤ በምትኩ ኢትዮጵያ  ለሶማሊላንድ ነጻነት እውቅና በመስጠት የመጀምሪያዋ አገር ትሆናለች በማለት፤ አገራቸው የምትሰጠውንና የምትጠብቀውንም ግልጽ አድርገዋል ።  የስምምነቱ ሙሉ ይዘትና አፈጻጽም በአንድ ወር ግዜ ውስጥ ይፋ ይሆናል በተባለው በዚህ የመግባቢያ ስነድ፤ ኢትዮጵያ በበርበራ ወደብ የባህር ሀይልና የወደብ አገልግሎት ልታገኝ የምትችልበትን ቦታ ለ50 አመት በሊዝ ታገኛለች። ሶማሊላንድም በተጨማሪ መጠኑ ባይገለጽም ከኢትዮጵያ አየር መንገድም ድርሽ ሊኖራት እንደሚችል ተገልጿል።

የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ በአዲስ አበባ
የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ በአዲስ አበባምስል TIKSA NEGERI/REUTERS

በስምምነቱ ላይ የተነሱ ተቃውሞዎችና የተሰጡ አስተያየቶች 


የሶማሊያ መንግስት ግን ይህን ስምምነት አጥብቆ ነው የተቃወመው። የአውሮጳ ህብረት የውጭ ግንኑነት ቢሮ ትናንት በዚሁ ስምምነት ላይ ባወጣው መገለጫም፤ የሚደረጉ  ስምምነቶች የሶማሊያን ሉአላዊነትና የግዛት አንድነት፣ የአፍርካ ህብረትን ቻርተርና የመንግስታቱ ድርጅትን መርሆች ከግምት ውስጥ ያስገቡ መሆን አለባቸው በማለት፤  እነዚህ መርሆችና ድንጋጌዎች ለአካባቢው ሰላምና መረጋጋት ቁልፍ መሆናቸውን አስታውቋል። 


ሶማሊያ ላንድ፤ አገር ያልሆነች አገር! 

3.5 ሚሊይን ህዝብ ያላት ሶማሊላንድ እ እ ከ1991 አም ጀምሮ ከሶማሊያ በመገንጠል ነጻ አገር መሆኗን ብታሳውቅም፤ እስካሁን ግን እውቅና የሰጣት አንድም አገር የለም። ሆኖም በምርጫ ጭምር መንግስት በመመስረትና ተቋማትንም በመገንባት ከማዕከላዊው የሶማሊያ መንግስት የተሻለ መንግስታዊ መዋቅር እንዳላትና የተረጋጋ የፖለቲካ ስርዓትም እንዳለ ነው በብዙዎች የሜነገረው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና  የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲምስል TIKSA NEGERI/REUTERS


የሶማሊያ ተቃውሞ ምክንያት 

 

ይህ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የተደረሰው የመግባቢያ ስምምነት በተለይ ሶማሊያን ያሰጋበትን ምክንያት፤ ሳሃን የተባለውና በናይሮቢ የሚገኘው በሰላምና ልማት ላይ የሚሰራው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት የስትራቴጂ አማካሪ የሆኑት ሚስተር ማት ብራይደን ሲያብራሩ፤ “ አንደኛው  ኢትዮጵያ ከዚህ ስምምነት የደረሰችው እራሷን ነጻ አገር አድርጋ ከምትቆጥረዋ፤ ሶማሊያ ግን የራሷ አካል አድርጋ ከምትቆጥራት ሶማሊላንድ ጋር ነው። ይህም  ኢትያጵያን የሶማሊያ ላንድን ነጻነት እውቅና የሰጠች የመጀምሪያዋ አገር ያደርጋታል። ሶማሊያ በእርግጥ በግዛቲቱ ምንም አይነት ቁጥጥር የላትም ግን የግዛቷ አካል አድርጋ የምትቆጥራት በመሆኑ፤ ስምምነቱ ያሳስባታል።የዐቢይ የወደብ መሻት ከኢትዮጵያ ጎረቤቶች ተቃውሞ ቢገጥመውም አላፈገፈጉም  በዚህም ምክንያት የሞቃዲሾ አስተዳደር በተግባር ምንም ማድረግ ባይችልም የዲፕሎማሲ ዘመቻ ግን ያወጀ መሆኑን ገልጸዋል።

 
ስምምነቱ ያስነሳው ውዝግብ በአካባቢው ሰላምና መረጋጋት ላይ የሚኖረው ተጽእኖ

ሚስተር ብራይደን ይህ ሁኔታ በአካባቢው ሰላምና መረጋጋት ላይ ሊፈጥር የሚችለውን ተጠይቀው ሲመልሱም፤ “ ባጭር ግዜ የሚፈጠር ነገር ላይኖር ይችላል፤ ግን ይህ ሁኔታ በአካባቢው በአንድ በኩል በሱማሌና አጋሮቿ ለምሳሌ ኤርትራና ግብጽ ከአጋሮቻችው የአፍርካና የአረብ ሊግ አገራት ጋር በመሆን፤ በሌላ በኩል ኢትዮጵያና ሶማሊ ላንድ እንደዚሁ እነሱም ከአፍሪቃና የአረብ ሊግ አጋሮቻቸው ጋር በመሆን ወደ ፉክክር ሊገቡ ይችላሉ” በማለት በአካባቢው አገሮች መካከል ክፍፍል መፍጠሩ የማይቀር እንደሆነ አስገንዝበዋል፤ ከሁሉም መፍትሄው ዲፕሎማሲ እንደሆነና ለዚህም ሁለቱ ማለት  ሶማሊያና ሶማሌላንድ ለጥብቅና ውጤት ተኮር ውይይት መቀመጥ ያለባቸው መሆኑን በማሳሰብ ጭምር።

ገበው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር