1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አሸናፊ ያልተለየበት የፈረንሳዩ የምክር ቤት ምርጫ እና አንድምታዉ

ሰኞ፣ ሐምሌ 1 2016

ፕሬዚዳንት ማክሮ ካቢኔያቸዉን በትነዉ ለዳግም ለሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ምርጫ፤ መጥራታቸዉን ተከትሎ በተካሄደዉ ሁለተኛ ዙር ምርጫ አብላጫ ወንበሮችን ያገኙ እና መንግሥት ለመመስረት በቂ ዉጤት ያላገኙ ፓርቲዎች በጥምረት ለመስራት ለድርድር እና ለስልጣን ክፍፍል ተስማምተዉ መቀመጥ እንዳለባቸዉ ተመልክቷል። የምርጫዉ ዉጤት ያልተጠበቀ ተብሏል።

https://p.dw.com/p/4i1Ch
አሸናፊ ያለየበት የፈረንሳዩ የምክር ቤት ምርጫ 2024
አሸናፊ ያለየበት የፈረንሳዩ የምክር ቤት ምርጫ 2024ምስል Lionel Urman/ABACAPRESS/IMAGO

አሸናፊ ያለየበት የፈረንሳዩ የምክር ቤት ምርጫ

አሸናፊ ያለየበት የፈረንሳዩ የምክር ቤት ምርጫ

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኤማኑኤል ማክሮ ከሦስት ሳምንት በፊት በተካሄደዉ በአውሮጳ ህብረት የምክር ቤት ምርጫ ፓርቲያቸዉ ከባድ ሽንፈት ከገጠመዉ ወዲህ ካቢኔያቸዉን በትነዉ ለዳግም የምክር ቤት ምርጫ፤ መጥራታቸዉ ይታወቃል። በፈረንሳይ ባለፈዉ ሳምንት እሁድ የተካሄደዉን የመጀመርያ ዙር ምርጫ ተከትሎ ትናንት እሁድ በተካሄደዉ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ምርጫ፤ ዉጤት አስደናቂ እና ያልተጠበቀ ተብሎለታል። ይፋ በተደረገዉ ዉጤት መሰረት፤ ፖፑላር ፍሮንት (NPF) የተሰኘዉ የግራ ዘመም ፓርቲዎች ጥምረት በአስደናቂ ሁኔታ አብላጫውን ድምፅ ማግኘቱ ተመልክቷል። በዚህም የግራ ዘመም ፓርቲዎች ጥምረት በምክር ቤት 171 ወንበሮችን ፤ የፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮ  ማዕከላዊ ፓርቲ 152 ወንበሮችን እንዲሁም  በመጀመርያ ዙር አብላጫ ድምፅን አግኝቶ የነበረዉ፤ ስደተኛ ጠል የሚባለዉየማሪን ለፐን ፓርቲ ናሽናል ራሊ ፓርቲ ደግሞ 134 ወንበሮችን በማግኘት ሦስተኛ ደረጃን መያዙ ታዉቋል።  ይሁንና ሁሉም ፓርቲዎች መንግሥትን ለመመስረት በቂ መቀመጫን አላገኙም። በምርጫዉ ዉጤት መሰረት አብላጫ ወንበሮችን ያገኙ እና መንግሥት ለመመስረት በቂ ዉጤት ያላገኙት እነዚህ ፓርቲዎች በጥምረት ለመስራት ለድርድር እና ለስልጣን ክፍፍል ለመቀመጥ መስማማት እንዳለባቸዉ ተመልክቷል። የፈረንሳዩን የህግ መወሰኛ ምክር ቤት የሁለተኛ ዙር ምርጫ ዉጤትን በተመለከተ ፈረንሳይ ፓሪስ የምትገኘዉን ወኪላችን አነጋጋረናታል።

 

ሃይማኖት ጥሩነህ

አዜብ ታደሰ

ፀሃይ ጫኔ