1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ሙዚቃአፍሪቃ

አርአያ እና ሁለገብ የሙዚቃ ሰው ፤ አደም መሐመድ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 26 2016

የየማህበረሰባቸውን ባህል ወግ እና ስረዓት በሙዚቃቸው ለማሳየት፣ ብሎም ለማሳደግ ለሚውተረተሩቱ ደግሞ ፈተናው በዚያው ልክ ነው። አደም እንደሚለው እርሱ ተወልዶ ያደገበት ማህበረሰብ ያለው ቱባ ባህል መገለጥ በሚገባው ልክ አለመገለጡ እርሱ እና መሰሎቹ የበለጠ እንዲተጉ ገፋፍቷቸዋል።

https://p.dw.com/p/4araD
አርቲስት አደም መሐመድ ፤የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋች ፣ ደራሲ እና ድምጻዊ
አርቲስት አደም መሐመድ ፤የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋች ፣ ደራሲ እና ድምጻዊ ምስል Privat

የአርቲስት አደም መሐመድ የሙዚቃ ህይወት

ሙዚቃን እንደ መጽሀፍ የሚገልጡ ፤ ሙዚቃን ከእንጀራነት ባሻገር የህይወታቸው አካል አድርገው በሚዚቃ እና ለሙዚቃ ኖረው ያለፉ እና ያሉ አያሌ ባለሞያዎች ስለመኖራቸው በብዙ አጋጣሚዎች ሲወሳ ይሰማል ፤ ይታያል። በዚህ ረገድ በተለይ የየማህበረሰባቸውን ባህል ፣ ወግ እና ስረዓት ከሌሎች መስኮች በተሻለ ለተቀረው ዓለም ለማስተዋወቅ የሚጥሩ የሙዚቃ ሰዎች ሲገኙ የሙዚቃ ተልዕኮ እና ግቡ ከማዝናናት ብሎም የህይወት መንገድ ከማድረግ ባሻገር በሌላ የህይወት ክፍል የማህበረሰብ ባለውለታ ሆኖ ይገኛል። እዚሁ ሀገራችን ውስጥ ብዙ ጥረው ነገር ግን በወቅቱ ጥቂት አልያም ምንም ያልተባለላቸው የሙዚቃ ሰዎች ዘመን አልፎ ዘመንን ሲተካ የሙዚቃ ስራቸውን ተረድቶ ክብሩን የሚገልጥበት ጊዜ ይመጣል ፤ ከረፈደም ቢሆን ያለፈ ስራው ዋጋ ያገኝለታል።የኤለክትሪክ ሞተር ሳይክል መገጣጠም የጀመረው ወጣት ባለበት ዘመን ፣ ገና በወጣትነቱ ጊዜ ሳያልፍበት ይህንኑ ዕድል ማግኘት ግን በእርግጥ መታደል ይሆናል፤ ጤና ይስጥልን የከወጣቶች ዓለም ዝግጅት አድማጮቻችን በዛሬው ዝግጅታችን ተወልዶ ያደገበትን ማህበረሰብ ባህል ፤ ወግ ስረዓት በሙዚቃው እያዋ ለተቀረው ማህበረሰብ እያስተዋወቀ ስለሚገኝ እና ለወጣቶችም አርአያ ስለሆነ አንድ የአፋን ኦሮሞ ድምጻዊ  የህይወት ተሞክሮ እንቃኛለን።ትውልድ እና ዕድገቱ በአሁኑ ምዕራብ ጉጂ ዞን ፣ ቡሌ ሆራ ወረዳ ማጤ ቡሌቲ ቀበሌ ትሰኛለች ። ሙዚቃን ገና በአፍላ የልጅነት ዕድሜው በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንደጀመረ ይናገራል ። አርቲስት አደም መሐመድ ።
ከአንደኛ ደረጃ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ከፍ ያለው ታዳጊው አደም በአቅራቢያ ባገኘው ጀማሪ ባንድ ውስጥ መሳተፍ ጀመረ ። አደም በተለይ ኪቦርድ የተሰኘውን የሙዚቃ መሳሪያ ለመጫወት የነበረው ከፍተኛ ፍላጎት የገጠር ልጅ በመሆኑ ብቻ ፈተና ቢገጥመውም በትዕግስት እግሩን ማስገባት ችሏል። ይህ ምናልባትም የወደፊት ህይወቱ ቅኝት መሰረቱ ሳይሆን አይቀርም።የድምፃዊና ጋዜጠኛ ግርማ ነጋሽ የምስጋናና የዕዉቅና ዝግጅት
ገና በልጅነት ዕድሜው የተወለደው እና እያደገ የሄደው የሙዚቃ ፍላጎቱ  መልክ መያዝ የጀመረው ግን በአፍላ የወጣትነት ዕድሜው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱ አጠናቆ በሮቤ የመምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ በነበረው ቆይታ ነበር ። አደም በኮሌጁ ውስጥ በተለይም በሙዚቃ የትምህርት ክፍል መጫወት የጀመረው የኪቦርድ የሙዚቃ መሳሪያ ዛሬ ለደረሰበት የሙዚቃ ስራዎቹ ዕድገት መሰረት ጥሎለታል። 
የሙዚቃው ኢንዱስትሪ እጅግ በጣም ፈጣን እድገት የሚታይበት፣ ተለዋዋጭና ከፍተኛ ፉክክር ያለበት ነው። የሙዚቃ ምርጫ ይለዋወጣል፤ ዛሬ ተወዳጅ የሆነ ሙዚቃ ወዲያው ይሰለቻል፤ አሮጌ ቴክኖሎጂዎች በአዲስ ይተካሉ፤ የቆዩ ስልቶችም በአዲስ መልክ ይቀርባሉ። የየማህበረሰባቸውን ባህል ወግ እና ስረዓት በሙዚቃቸው ለማሳየት፣ ብሎም ለማሳደግ ለሚውተረተሩቱ ደግሞ ፈተናው በዚያው ልክ ነው።  አደም እንደሚለው እርሱ ተወልዶ ያደገበት ማህበረሰብ ያለው ቱባ ባህል መገለጥ በሚገባው ልክ አለመገለጡ እርሱ እና መሰሎቹ የበለጠ እንዲተጉ ገፋፍቷቸዋል። ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: ገንዘብ ወይስ ጥረት?
ለሚ ለሚ የሚሉ መጣሪያዎች በተሰጣቸው ነጠላ የሙዚቃ ስራዎች እና በሌሎቹም ትልቅ ስም እና ዝና ሊጎናጸፍበት ችሏል።
ድምጻዊት ጫልቱ ቡቶ ፤ ልክ እንደ አደም ሁሉ ጉጂ ካፈራቻቸው ድምጻውያን መካከል አንዷ ናት ። ከአደም ጋር የረዝም ጊዜ ጓደኝነት ብቻ ሳይሆን የራሳቸውን የባህል ሙዚቃ ለማሳደግ ከሚታትሩቱ ናት ። ስለ አደም ስትናገር በእርግጥ እርሱ ሁለገብ የሙዚቃ ሰው እና ህልመኛ ነው ትላለች። 
ስም እና ዝናን ያተረፉ ኢትዮጵያውያን ድምጻውያን እጅጉን በርካቶች የመሆናቸውን ያህል ሁለገብ የሙዚቃ ሰዎች ስለመሆናቸው የሚመሰከርላቸው ግን እጅጉን ጥቂቶች ስለመሆናቸው ነው። በሚወክሉት ማህበረሰብ ወይም ቋንቋ የዜማ እና ግጥም ደ,ራሲ ፣ የሚቃ መሳሪያ ተጫዋች እንዲሁም ድምጻዊ ሆነው በአንድ ቦታ የተገኙ የሙዚቃ ሰዎቻችን በእርግጥ ጥቂት ናቸው ። ከጉጂ የኦሮሞ ማህበረሰብ የተገኘው አደም መሀመድ  ባለችው ጥቂት አቅም ነገር ግን ሁለገብ የሙዚቃ ሰው መሆኑን ለማሳየት ደፋ ቀና እያለ ያለ የሚዚቃ ሰው ስለመሆኑ የሙያ አጋሩ ጫልቱ ትመሰክራለች።
 ቄሮ ታመነ ፤ የሙዚቃ ድግሶችን በማስተባበር እና መድረክ በመምራት ይታወቃል። አደምን የሚያውቀው ከ10 ዓመት በፊት ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመርዳት ርብርብ ሲደረግ ከነበረበት ጊዜ አንስቶ ሲሆን የተወለደበትን አካባቢ  ባህል ለማስተዋወቅ የሄደበት ርቀት የማህበረሰቡ አምባሳደር እና ተስፋ የሚጣልበት አርቲስት ነው ይላል ።«ስሟ ጊታር ነው» ድምፃዊ ዮሃንስ ጌታቸው
ስኬት የብርቱ ጥረት ዉጤት ናት ይባላል። አደም ዛሬ ለደረሰበት ስኬት ያለፈው ዉጣ ውረድ እንዲሁ በዋዛ የሚታይ አይደለም ይላል። የሚዚቃ ስራውን በገንዘብ ለመደገፍ በረሃ ወርዶ በወርቅ ፍለጋ ላይ እስከመሰማራት መድረሱን ያስታውሳል ።
እውነት ነው ፤ ነገ መድረሻውን አስቀድሞ የተረዳ ምንም እንኳ መንገዱን መጥረግ አድካሚ ምናልባትም ዋጋ የሚያስከፍል ቢሆን እንኳ ይጋፈጠዋል እንጂ አያፈገፍግም። አደም ያደረገውም ይክንኑ ነው። ዛሬ በአካባቢው ባህላዊ ሙዚቃዎች ትልቅ ስም እና ዝናን ገንብቷል። ነገር ግን አልቆመም። በሙዚቃ ውስጥ እያደገ የመጣ ታታሪ ሙያተኛ መሆኑን የሚገልጸው ቄሮ ታመነ ፤ አደም አሁን ከጉጂ ባሻገር ተገልጧል ይላል።  
አርቲስት አደም መሀመድም በዚሁ የኦሮሚያ የሙዚቃ አልበሙ ሌሎቹ ቋንቋውን የማይረዱቱጋ እንዲደርስ ታሳቢ ማድረጉን ይገልጻል ይህ ለእርሱ ህልሙም ነበር።  ገና የምኖረው ህልም አለኝ ይላል ።የወጣቶች የአዲሱ ዓመት ተስፋ እና ስጋት
እንግዲህ አድማጮቻችን በድምጻዊ አደም መሐመድ የሙዚቃ ህይወት ላይ ያጠነጠነው የከወጣቶች ዓለም ዝግጅታችንም የእስካሁኑን ይመስል ነበር ፤ ለአብሮነታችሁ ምስጋናችን ትልቅ ነው ። ጤና ይስጥልን። 
ታምራት ዲንሳ
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር 
 

አርቲስት አደም መሐመድ ፤የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋች ፣ ደራሲ እና ድምጻዊ
ስም እና ዝናን ያተረፉ ኢትዮጵያውያን ድምጻውያን እጅጉን በርካቶች የመሆናቸውን ያህል ሁለገብ የሙዚቃ ሰዎች ስለመሆናቸው የሚመሰከርላቸው ግን እጅጉን ጥቂቶች ስለመሆናቸው ነው።ምስል Privat
አርቲስት አደም መሐመድ ፤የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋች ፣ ደራሲ እና ድምጻዊ
ስኬት የብርቱ ጥረት ዉጤት ናት ይባላል። አደም ዛሬ ለደረሰበት ስኬት ያለፈው ዉጣ ውረድ እንዲሁ በዋዛ የሚታይ አይደለም ይላል። የሚዚቃ ስራውን በገንዘብ ለመደገፍ በረሃ ወርዶ በወርቅ ፍለጋ ላይ እስከመሰማራት መድረሱን ያስታውሳል ።ምስል Privat