1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ሙዚቃአፍሪቃ

የድምፃዊና ጋዜጠኛ ግርማ ነጋሽ የምስጋናና የዕዉቅና ዝግጅት

ሐሙስ፣ ነሐሴ 18 2015

በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ የሙዚቃ ባለሞያወች ማህበር አስተባባሪነት በቨርጂኒያ የተዘጋጀው የምስጋና ምሽትም አርቲስቱ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ጉዞ ውስጥ ላበረከተው አስተዋጾ ክብር ለመስጠት የተዘጋጀ መሆኑን ከአስተባባሪወቹ አንዱና የራስ ባንድ ድረም ተጫዋች አዲስ ምስጋናው ገልጿል።

https://p.dw.com/p/4VXrm
ድምጻዊና ጋዜጠኛ ግርማ ነጋሽ ላደረገዉ አስተዋፅኦ ዕዉቀና በተሰጠበት ስርዓት ላይ ሲያንጎራጉር
ድምጻዊና ጋዜጠኛ ግርማ ነጋሽ ላደረገዉ አስተዋፅኦ ዕዉቀና በተሰጠበት ስርዓት ላይ ሲያንጎራጉርምስል Abebe Felek

ኢትዮጵያዊዉ ድምፃዊና ጋዜጠኛ ግርማ ነጋሽ የሶስት ሙያዎች ባለቤት


በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ የሙዚቃ ባለሞያወች ማህበር አዘጋጅነት፣የድምጻዊና ጋዜጠኛ ግርማ ነጋሽን የሙያ ተሞክሮና አስተዋጾ ያከበረ የምስጋና ምሽት ቨርጂኒያ ውስጥ ተካሄደ። በዝግጅቱ የኢትዮጵያ የኪነጥበብ ባለሞያወችና የሙያ አፍቃሪያን የታደሙ ሲሆን አርቲስቱን የሚዘክሩ ዝግጅቶች ቀርበዋልም። በምሽቱ የክብር ምስጋና ሽልማት የተበረከተለት አርቲስት ግርማ ነጋሽ ለአዘጋጆቹ ምስጋናውን አቅርቧል።

በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ የሙዚቃ ባለሞያወች ማህበር አዘጋጅነት፣ ተወዳጁን ድምጻዊና ጋዜጠኛ ግርማ ነጋሽን የሙያ ተሞክሮና አስተዋጾ ያከበረ የምስጋና ምሽት ቨርጂኒያ ውስጥ ተካሄደ። በዝግጅቱ የኢትዮጵያ የኪነጥበብ ባለሞያወችና የሙያ አፍቃሪያን የታደሙ ሲሆን አርቲስቱን የሚዘክሩ ዝግጅቶች ቀርበዋል። በምሽቱ የክብር ምስጋና ሽልማት የተበረከተለት አርቲስት ግርማ ነጋሽ ለአዘጋጆቹ ምስጋናውን አቅርቧል። 

የአንጋፋው ድምፃዊ እና ጋዜጠኛ ግርማ ነጋሽ ሥራዎች

                                    የግርማ ነጋሽ ሙዚቃዎች ዛሬም ተወዳጅ ናቸዉ
ከ60 አመታት በላይ የእድሜ ባለጸጋ የሆነችው ‘የእኔ ሃሳብ’ን ጨምሮ የድምጻዊና ጋዜጠኛ ግርማ ነጋሽ ዘፈኖች ትውልድን፣ ዘመንን፣ ቦታና ሁነትን ተሻግረው ዛሬም ይዜማሉ፤ ይደመጣሉ። በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ የሙዚቃ ባለሞያወች ማህበር አስተባባሪነት በቨርጂኒያ የተዘጋጀው የምስጋና ምሽትም አርቲስቱ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ጉዞ ውስጥ ላበረከተው አስተዋጾ ክብር ለመስጠት የተዘጋጀ መሆኑን ከአስተባባሪወቹ አንዱና የራስ ባንድ ድረም ተጫዋች አዲስ ምስጋናው ገልጿል። 
ትውልድና እድገቱ አዲስ አበባ የሆነው አርቲስት ግርማ ነጋሽ ገና ከጅምሩ የሙዚቃን ሃሁ የቆጠረው ከአብሮ አደጉ ሰይፈ ዮሃንስና ከአርቲስት ጥላሁን ገሰሰ ጋ ነበር። ከ1952 ዓ/ም ጀምሮ በፖሊስ ኦርኬስትራና በብሄራዊ ትያትር ቤት ለአጭር ጊዜ ሰርቷል። በነዚህ በጣት በሚቆጠሩ አመታት ውስጥ ነው የኔ ሃሳብንና ምነው ተለየሽኝን ጨምሮ ዘመን ተሻጋሪ ዜማወችን ያቀነቀነው። 
ብዙም ሳይቆይ በቤተሰብ ተጸዕኖ ሳቢያ ሙዚቃን ተሰናበተና በኮካኮላ ኩባንያ ውስጥ  የሽያጭ ሰራተኝነት፣ ከዛም በማስታወቂያ ሚኒስቴር ውስጥ አገልግሏል። ከስፖርት ጋዜጠኝነት በተጨማሪ የአርብ ምሽት የባህል ሙዚቃ አዘጋጅና አቅራቢም ነበር። ጋዜጠኛ አዲሱ አበበ ሰለግርማ ሲናገር የማይናወጥ የሃቀኝነት ስበዕና መላበሱን ገልጿል። በምሽቱ የታደመው ወዳጁ አንጋፋው አርቲስት ማህሙድ አህመድም ብዙ ዘመን አልፈው ዛሬ ላይ ደርሰው ይህን ማየት በመቻሉ የተሰማውን ደስታ ገልጿል። 

                                                   ስለግርማ ነጋሽ የተዘጋጀ ፊልምም ታይቷል
በምሽቱ በሰሜን አሜሪካ የሙዚቀኞች ማህበር የተዘጋጀለትን ሽልማትና ክብር የተቀበለው አርቲስና ጋዜጠኛ ግርማ ነጋሽ ለተቸረው ክብር ምስጋናውን አቅርቧል። የብዙ ከያንያንን የህይወት ተሞክሮ በመዘከር የሚታወቀው ተወልደ በየነ በምሽቱ የግርማ ነጋሽን ህይወት የዳሰሰ ዘጋቢ ፊልም አዘጋጅቶ አቅርቧል። እንዲህ ያለው የሰራን ሰው የማመስገን ተግባር አስፈላጊነትም አጽንዖት ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስቧል። 
በምሽቱ በዲሲ፣ ቨርጂኒያና ሜሪላንድ የሚኖሩ አርቲስቶች ስራወቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን፣ የሙያው አፍቃሪያንም ለአርቲስቱ ያላቸውን ክብር ገልጸዋል።

ድምጻዊና ጋዜጠኛ ግርማ ነጋሽ የዕዉቅናና የክብር ሽልማት ሲሰጠዉ
ድምጻዊና ጋዜጠኛ ግርማ ነጋሽ የዕዉቅናና የክብር ሽልማት ሲሰጠዉምስል Abebe Felek

አበበ ፈለቀ

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ