1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ሥለ ግጭት የማቆም ስምምነቱ አንደኛ ዓመት

ሐሙስ፣ ጥቅምት 22 2016

የፕሪቶሪያ ግጭት የማስቆም ስምምነት ዋና ዉጤት "የጦር መሣሪያ ላንቃ መዘጋቱ" እንደሆነ የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር አስታወቀ። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምበሳደር መለስ አለም ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ከግጭት ማቆሙ ስምምነት በኋላ ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ መድረኮች የምትጠቀስበት ሁኔታ ካለፈው ዓመት የትለየ ሆኗል።

https://p.dw.com/p/4YKJg
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምበሳደር መለስ አለም
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምበሳደር መለስ አለምምስል Solomon Muchie/DW

ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ መድረኮች የምትጠቀስበት ሁኔታ ካለፈው ዓመት የትለየ ሆኗል

 

የፕሪቶሪያ ግጭት የማስቆም ስምምነት ዋና ዉጤት "የጦር መሣሪያ ላንቃ መዘጋቱ" እንደሆነ የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር አስታወቀ።የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምበሳደር መለስ አለም  ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ከግጭት ማቆሙ ስምምነት በኋላ ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ መድረኮች የምትጠቀስበት ሁኔታ ካለፈው ዓመት የትለየ ሆኗል። ስምምነቱ ኢትዮጵያ በብዙ መንገድ ከተለያዩ ሀገሮች ጋር ያላትን ግንኙነት መለወጡን የግለፁት አምበሳደር መለስ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ፣ ከአየርላንድ እንዲሁም ከአውሮጳ ሕብረት ጋር ያላትን ግንኙነት እንዲሻሻል ማድረጉን እንደምሳሌ ጠቅቀሰዋል። የፕሪቶርያዉ ስምምነት አፈጻፀምና የትግራይ ፖለቲከኞች ቅሬታ
የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት እና ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ( ሕወሓት ) ከአንድ አመት በፊት በዛሬው እለት  የገቡት ተኩስ  ስምምነት እልቂትን እና ደም መፋሰስን እንዲያስቆም ከመፈለግ ባሻገር፣ ውጊያው ለከፋ የሰብዓዊ ድጋፍ መቃረጥ የተጋለጡ ሰዎች እርዳታ እንዲያገኙ፣ የቀድሞ ተዋጊዎች ትጥቃቸውን አስረክበው ወደ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመለሱ ማድረግን ጭምር ያለመ ነበር።
ስምምነቱ ለኢትዮጵያ ምን አስገኘ የሚለውን ጥያቄ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ዛሬ አቅርበንላቸው "ሰላም" አስገኝቷል ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
ኢትዮጵያ በጦርነቱ ምክንያት ይደርሳበት የነበረው የውጭ ጫና ከፍተኛ እንደነበር ይታወቃል። ቃል ዐቀባዩ በተደረሰው ስምምነት ግጭት በመቆሙ ምክንያት ሻክረው የነበሩ ግንኙነቶች አሁን መልካቸው ስለመቀየር አብራርተዋል። ይሁንና የምልሶ ግንባታ እና የጦርነቱ ሰለባዎችን መልሶ በማቋቋም ረገድ እጥረት መኖሩን ቃል ዐቀባዩ አልሸሸጉም። ዉይይት፤ የፕሪቶርያዉ ስምምነት በርግጥ ተፈጻሚ እየሆነ ነዉ?

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር መለስ አለም በጦርነቱ ምክንያት ሻክሮ የነበረው የሀገራትና ተቋማት ግንኙነት ተለውጧል ሲሉ ገጥሞ ለነበረው የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መሻከር መነሻው ምክንያት ጦርነት ከነበረ ኢትዮጵያ አሁንም የአስቸካይ ጊዜ ዐዋጅ ያስደነገገ ጦርነት ውስጥ ሆና እንዴት ምዕራባዊያኑና አለም አቀፍ ተቋማት ግንኙነታቸውን ለመሻሸል ያንን መመልከት አልቻሉም ? መንግሥትስ የዲፕሎማሲ ግንኙነቱ ችግር እንዲገጥመው ምክንያት የነበረው ጦርነት በሌላኛው የሀገሪቱ አካባቢ እየቀጠለ ባለበት ግንኙነት ተሻሻለ ሲል አይጋጭም ወይ በሚል ከዚህ በፊት ዶቼ ቬለ ላቀረብንላቸው ጥያቄ ምላሽ አልሰጡም።

ሰለሞን ሙጬ

ነጋሽ መሐመድ 

ኂሩት መለሰ