1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ትግራይ:- የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ሰላማዊ ህይወት የመመለስ እቅድ

ዓርብ፣ ግንቦት 9 2016

በቀጣዮቹ ሁለት ወራት 75 ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎች ወደ ሰላማዊ ሕይወታቸው ለመመለስ መታቀዱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የተሃድሶ ኮምሽን አስታወቀ። የቀድሞ ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ሕይወት የመመለስ ስራ በበጀት እጥረት እንደተፈለገዉ አለመከወኑም ኮምሽኑ ገልጿል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ተሃድሶ ኮምሽን እስካሁን በበጀት እጥረት ወደ ትግበራ አለመግባቱን አስታዉቋል።

https://p.dw.com/p/4g0Xt
የቀድሞ ትግራይ ተዋጊዎችን ወደ ሰላማዊ ሕይወታቸው ለመመለስ እቅድ
የቀድሞ ትግራይ ተዋጊዎችን ወደ ሰላማዊ ሕይወታቸው ለመመለስ እቅድ ምስል Million Hailesilassie/DW

ትግራይ:- የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ሰላማዊ ህይወት የመመለስ እቅድ

በቀጣዮቹ ሁለት ወራት 75 ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎች ወደ ሰላማዊ ሕይወታቸውለመመለስ እቅድ መያዙ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የተሃድሶ ኮምሽን አስታወቀ። የቀድሞ ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ሕይወት የመመለስ ስራ በበጀት እጥረት ምክንያት በሚፈለገው ልከሰ አለመከወኑም ኮምሽኑ ገልጿል። ከፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት በኃላ የተመሰረተው እና የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደሰላማዊ ሕይወት የመመለስ ሐላፊነት የተሰጠው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ተሃድሶ ኮምሽን እስካሁን በበጀት እጥረት ምክንያት ወደ ትግበራ አለመሸጋገሩ ይገልፃል። አሁን ላይ ሀብት የማሰባሰብ ስራ ላይ መሆኑ የሚገልፀው ብሔራዊ ተሃድሶ ኮምሽን በአጠቃላይ 371 ሺህ የሚሆኑ በመላ ሀገሪቱ ያሉ የቀድሞ ተዋጊዎች፥ በተለያየ ዙር ድጋፍ በማድረግ ወደ ሰላማዊ ሕይወት ለመመለስ እየሰራ መሆኑ አስታውቋል። 

በሀገርአቀፍ ደረጃ ለሚተገበረው የቀድሞ ተዋጊዎች ወደ ሰላማዊ ሕይወት የመመለስ ስራ በአጠቃላይ 750 ሚልዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ኮምሽኑ የሚገልፅ ሲሆን ይሁንና እስካሁን ባለው የዓለምአቀፍ ተቋማት ድጋፍ የሚፈለገው ያክል አለመሆኑ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮምሽን ምክትል ኮምሽነር አቶ ተስፋኣለም ለዶቼቬለ ተናግረዋል። በትግራይ ያሉ የቀድሞ ተዋጊዎች ወደ ሰላማዊ ሕይወት የመመለስ ትግበራ ላይ ከክልሉ አስተዳደር ባለስልጣናት፣ ከሰራዊቱ መሪዎች፣ ከአፍሪካ ሕብረት ተወካዮች ጋር በመሆን በመቐለ ውይይት ላይ መሰንበቱ የሚገልፀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ተሃድሶ ኮምሽን፥ ለትግበራው ይረዳሉ በተባሉ ነጥቦች ላይ ንግግር መደረጉም አስታውቋል። ኮምሽኑ እንደሚለው በመጪዎቹ ሁለት ወራት ውስጥ በመጀመርያ ዙር 75 ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎች ድጋፍና ስልጠና በመስጠት ወደ ሰላማዊ ሕይወት ለመመለስ እቅድ መያዙ ይገልፃል። ከወራት በፊት በትግራይ 50 ሺህ የቀድሞ ታጣቂዎች በክልሉ አስተዳደር ውሳኔ ከትግራይ ሀይሎች ተሰናብተው የነበረ ሲሆን ይሁንና ድጋፍ ይሁን ማቋቋሚያ አለማግኘታቸው በመግለፅ ቅሬታ ያቀርባሉ።

 

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ 

አዜብ ታደሰ 

ታምራት ዲንሳ