1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ2023 የኮንጎ ምርጫ ታሪካዊነትና የተወዳዳሪዎች ብዛት

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 11 2016

ዴሞክራቲክ ሪፑብሊ ኮንጎ ክትናንት ጀምሮ የፕሬዝዳንታዊ፣ የፓርላማና የአካባቢ ምርጫዎችን እያክሄደች ነው። ምርጫው ትናንት ረቡዕ ታኅሣሥ 10 ተጀምሮ እንዲያበቃ ታስቦ የነበር ቢህንም፤ በብዙ አካባቢዎች የምርጫ ጣቢያዎች ዘግይተው በመከፈታቸው ለዛሬ እንድተራዘመ ተገልጿል።

https://p.dw.com/p/4aRsI
የኮንጎ ምርጫ
በርካቶች የሚወዳደሩበት የኮንጎ ምርጫ ድምፅ አሰጣጥ ከታሰበበት ቀን ተራዝሟል። ምስል ARSENE MPIANA/AFP

የ2023 የኮንጎ ምርጫ

 

ዴሞክራቲክ ሪፑብሊ ኮንጎ ክትናንት ጀምሮ የፕሬዝዳንታዊ፣ የፓርላማና የአካባቢ ምርጫዎችን እያክሄደች ነው። ምርጫው ትናንት ረቡዕ ታኅሣሥ 10 ተጀምሮ እንዲያበቃ ታስቦ የነበር ቢህንም፤ በብዙ አካባቢዎች የምርጫ ጣቢያዎች ዘግይተው በመከፈታቸው ለዛሬ እንድተራዘመ ተገልጿል።  ይህ ምርጫ፤ በኮንጎ ታሪክ ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ከተደረገበት እ እ እ 2018 ም ወዲህ ለመጅመሪያ ግዜ የተደረገ ነው። የወቅቱን ፕሬዝድንት ፌሊክስ ሺሴከዲን ጨምሮ 18 እጩዎች ለፕሬዝዳንትነት የተወዳደሩ ሲሆን፤ ሊሎች ስድስት እጩዎችም ከምርጫው እራሳቸው ማግለላቸው ታውቋል።

የመራጮች ብዛትና የዲያስፖራዎች የመምረጥ ዕድል

በጎንጎ ዴሞክራቲክ የፕሬዝዳንታዊ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቅረብ የማይመለስ 60 ሺ ዶላር መከፈል ግዴታ እንደሆነም ተገልጿል። ከጠቅላላው 100 ሚሊዮን የኮንጎ ህዝብ 44 ሚሊዮኖቹ ለምርጫ መመዝገባቸውም የታወቀ ሲሆን፤ ለመጀመሪያ ግዜም በተመረጡ ማለት በቤልጅየም፤ ፈረንሳይ፤ ካናዳ፤ አሜሪካና ደቡብ አፍርካ የሚገኙ የዴሞክራቲክ ኮንጎ ዲይስፖርዎች በምርጫው ተሳትፈዋል። ሆኖም ግን  በምሥራቁ የአገሪቱ ክፍል እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት ሰባት ሚሊኖች እንደተፈናቀሉና በርካታዎችም መምረጥ እንደማይችሉ ነው የሚታወቀው ።

ዴሞክራቲክ ኮንጎ የሀብታም ድሀዋ አገር

ዴሞክርቲክ ኮንጎየቆዳ ሳፋቷ የምዕራብ አውሮፓን ወይም የፈርንሳይን አራት እጥፍ የሆነች፤ ከሰህራ በታች ካሉት የአፍርካ አገሮች ትልቋ  አገር ናት። በክበሩ ማዕድናትና የተፈጥሮ ሀብት የበለጸገች ብትሆንም፤ የተረጋጋ የፖለቲካ ስርአት ግን ኑሯት የማያውቅና ሰላም የራቃት፤ እያላት ያጣችና የብጥብጥና አመጽ ማዕክል በመሆን የምትጠቀስ ነች። በአገሪቱ ባለው የመገናኛና የመሰረተ ልማት ችግር ምክንያት የአገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን በ 175 ሺ የምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቆሳቁሶችን ለማድረስ የተባበሩት መንግሥታትን፣ የግብጽንና የኮንጎ ባራዛቫሊን የአየር ትርንስፖርት እርዳታ እንደተጠቀመ ተገልጿል።

ፎቶ፤ የኮንጎ ምርጫ 2023
ድምጽ ለመስጠት የተገኙ መራጮች የዕጩዎችን ዝርዝር እየተመለከቱ፤ ፎቶ፤ የኮንጎ ምርጫ 2023ምስል Mosa'ab Elshamy/AP/picture alliance

በምርጫ ሂደቱ የሚነሱ ጥያቄዎችና የምርጫ ታዛቢዎች

ከምርጫው በፊት በነበረው የምርጫ ዘመቻ፤ በአንዳንድ አካባቢዎች መለስተኛ ሁከቶች ከመታየታቸው ውጭ ሰላማዊ እንደነበር ቢገለጽም፤ በአገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ገለልተኝነትና ብቃት ላይ ግን ጥያቄዎች እንዳሉ ነው በብዙዎች ዘንድ የሚነገረው። በአገሪቱ የሚገኙ የሃይማኖትና የሲቪል ማሕበራት ድርጅቶች በሺህ የሚቆጠሩ የምርጫ ታዛቢዎችን ያሰማሩ ሲሆን፤ አውሮፓ ሕብረት ግን ለምርጫ ታዛቢው ቡድን  ለሥራው የሚያስፈልጉ የመገናኛ መሳሪያዎች እንዲገቡ አልተፈቀደም በሚል ምክንያት ታዛቢዎቹን እንዳላከና በዋና ከተማዋ ኪንሳሻ ብቻ የባለሙያዎች ቡድን እንዳስቀመጠ ተገልጿል።

የምርጫ አጀንዳዎችና ታሳቢ አሸናፊዎች

 

ዋና ዋናዎቹ የምርጫ አጀንዳዎችና ትኩረት የሚሹ የሀገሪቱ ችግሮች፤ የደህንነትና የጸጥታ ሁኔታ፤ የኢኮኖሚ ቀውስና የኑሮ ውድነት፤ የሙስና ችግርና የተቋማት ግንባታ ጉዳይ፤ እንዲሁም በመንግሥትና ህዝብ መካከል ያለ አለመተማመን እንደሆነ በሰፊው ሲነገር ሰንብቷል።

የኮንጎ ምርጫ 2023
ከእጩ ፕሬዝደንታዊ ተወዳዳሪዎቹ አንዱ ፊሊክስ ቼሴኬዴምስል AFP

ክዚህ አንጻር የትኛው ተወዳደሪ የበርካታ ኮንጎሊዞችን ድጋፍ ያገኛል የሚለው ጥያቄ አነጋጋሪ ቢሆንም፤  በደቡብ አፍሪካው  ኤስ ቢ ሲ ቴሌቪዥን የአፍሪካ ተንታኝ የሆነው ኒክሶን ካቴምቦ ግን፤ አሸናፊው በዋናው የሀገሪቱ ችግር ተጨባጭና ግልጽ ፕሮግራም ያቀረበው ነው በማለት በዚህ በኩል ፕሬዝዳንት ሼኬሴዲ የተሻለ አማራጭ ሳያቀርቡ እንዳልቀሩ ነው የሚናገረው። «በኮንጎ ፖለቲካ የጸጥታ ጉዳይ ዋናው አጀንዳ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ፕሬዝድንት ሼኬሴሴዲ ሲያደርጉ የነበረውን የምርጫ ዘመቻ ካየን የኮንጎችግር ከፕሬዝድናት ካጋሜ ፍላጎት ጋር ቁርኝት ያለው መሆኑን በግልጽ ተናግረዋል» በማለት ይህም የበርካታ ኮንጎዎችን ድጋፍ ሳያስገኝላቸው እንዳልቀረና የኮንጎን የጸጥታ ችግር ዋና አጀንዳው ያላደረገ  እጩ ተወዳዳሪ ግን የማሸነፍ ዕድሉ አነስተኛ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ተስፋና ስጋት

አመጽና ሁከት ተለይቷት የማያውቀው ኮንጎ በዚህ ምርጫም ችግር እንዳይፈጠርና ብጥብጥም እንዳይነሳ የብዙዎች ፍላጎት ነው። የምርጫው መራዘምና የምርጫ ቆሳቁሶች እጥረት ግን በምርጫው ውጤት ላይ ችግር ሊያስክትል እንደሚችል ከወዲሁ እይተነገረ ነው። በለንደን ዩንቨርስቲ የፖለቲክ ሳይንስ ፕሮፌሰርና የአፍሪካ ተንታኝ የሆኑት ዶክተር ሚኬል አሞቺ ግን ጠንካራ ተወዳዳሪዎች መቅረባቸውንና ህዝቡም በአንጻራዊነት በነጻ መምረጥ መቻሉን በመጥቀስ፤ ዋናው ጥያቄ ከድምፅ ቆጠራው ላይ እንደሆነ ነው የሚናገሩት ፤ «ዋናው ጥያቄ የምርጫ ኮሚሽኑ ምን ያህል ይታመናል የሚለው ነው። የሁሉም ፓርቲዎች ተወካዮች በተገኙበት የምርጫ ቆጠራው ይካሄዳል፤ ውጤቱም በትክክል ይገለጻል ብለን ተስፋ እንድርግ» በማለት ተስፋና ስጋታቸውን ገልጸዋል። እንደ ምርጫ ኮሚሽኑ ፕሮግራም ከሆነ  የምርጫው ውጤት ከ10 ቀን በኋላ የሚገለጽ ሲሆን፤ አብላጫ ድምፅ ያገኘው አሸናፊ ፕሬዝዳንት በዓለ ሲመትም በመጪው ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት ጥር 20 ቀን 2024 የሚካሄድ ነው የሚሆነው።

ገበያው ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

እሸቴ በቀለ