1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ትምህርትኢትዮጵያ

የ12ኛ ክፍል ፈተና እና ስጋት

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 8 2016

በኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ዓመታት በሀገር አቀፍ ደረጃ በ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የተመዘገቡ የፈተና ውጤቶች በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆል አንድ ሰሞን ሲያነጋግር ሰንብቷል። ባለፈው ዓመት ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ማለፊያ ነጥብ ያመጡት ተማሪዎች 3.2 በመቶ ብቻ መሆናቸው፤ ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ፈተና በሚወስዱ ተማሪዎች ላይ ስጋት እና ጭንቀት ፈጥሯል።

https://p.dw.com/p/4aJQP

ይህ ስሜት ከመንግስት ትምህርት ቤቶች ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ውጤት ሲያስመዝገቡ በቆዩት የግል ትምህርት ቤት ተማሪዎች ላይ ጭምር የሚታይ ነው። የቅዱስ ዩሐንስ መጥምቅ ደላሳል ካቶሊክ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆነችው የአብስራ መላኩ፤ ከእነዚህ ተማሪዎች መካከል አንዷ ናት። 


በትምህርቷ ጥሩ ውጤት ስታመዘግብ የቆየችው የአብስራ፤ የ11ኛ ክፍል ተማሪ እያለች ወደ ዩኒቨርስቲ የማለፊያ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር አነስተኛ መሆኑን ስትሰማ ለጉዳዩ እምብዛም ትኩረት አልሰጠችውም ነበር። ለ12ኛ ክፍል ፈተና እየተዘጋጀች ባለችበት በዚህ ዓመት ይፋ የተደረገውን ውጤት ስትስማ ግን የነበራት ስሜት የተለየ ነበር። 


“የአሁኑን ውጤት ስሰማ፤ ያለፈው ተማሪ ጭራሽ [ካለፈው ዓመት] በሆነ ነጥብ ቀንሷል። በዚህ በጣም ተደናግጬ ነበር። ‘ባላልፍስ’ የሚል ጭንቀት ውስጥ ከትቶኝ ነበር” ስትል በወቅቱ የነበራትን ስሜት ትገልጻለች። በእርሷ ትምህርት ቤት የሂሳብ መምህር የሆኑት ማርታ ዋቅጅራ፤ የ12ኛ ክፍል ውጤት በጣም ዝቅ እያለ በመምጣቱ በተማሪዎች ዘንድ ጭንቀት መኖሩን ያረጋግጣሉ።


አንዳንድ ወላጆች በጣም ከመጨነቃቸው የተነሳ ወደ ትምህርት ቤት በመምጣት አስጠኚ አስተማሪዎችን እንደሚቀጥሩ መምህሯ ያክላሉ። በተፈታኝ ተማሪዎች ላይ የሚታየውን ይህን ጭንቀት ለመቅረፍ የትምህርት ቤቱ መምህራን “የአጠናን ቴክኒኮችን” ከመንገር ጀምሮ የተለያዩ መንገዶችን የማስተማሪያ መንገዶችን በመጠቀም የማስተማሪያ መንገዶችን እየተጠቀሙ ከወትሮው የተለየ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደሚገኙም ያብራራሉ።  #77ከመቶው


ቪዲዮ: ተስፋለም ወልደየስ