1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከስምምነቱ አፈጻጸም ምን እንማር?

እሑድ፣ መጋቢት 8 2016

አፈራራሚዎቹ በግጭቱ የተጎዱትን መልሶ ማቋቋምን ጨምሮ ተጎጂዎችን ያማከለ የሽግግር የፍትሕ ሂደት እና ተጠያቂነትን ለማስፈን የስምምነቱ ፈራሚዎች መገናኘታቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ አድርገዋል።እነዚህ የበለፀጉ እንዲሁም በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች የተከሰቱት ቀውሶች በተመሳሳይ ቁርጠኝነት ችግሩ እንዲፈታ ጥሪ አቅርበዋል።

https://p.dw.com/p/4deg7
Äthiopien Friedensabkommen Tigray
ምስል PHILL MAGAKOE/AFP/Getty Images

``ከፕሪሪቶሪያ የግጭት ማቆም ስምምነት ምን እንማር``

የፕሪቶሪያ ስምምነት አፈጻጸም ለመገምገም የአፍሪቃ ሕብረት፣ ኢጋድ፣ የተባበሩት መንግስታት፣አውሮፓ ህብረትና  አሜሪካ ተወካዮች በተገኙበት መጋቢት 2 ቀን 2016 በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

በኢትዮጵያ የአውሮፓ ሕብረትን ጨምሮ የሰባት ሀገራት ተልዕኮዎች አፍሪካ ሕብረት ያሰናዳው የመጀመሪያው የፕሪቶሪያ የተኩስ ማቆም ስምምነት አፈፃፀም ግምገማ መጠናቀቅን ተከትሎ ባወጡት የጋራ መግለጫ ቀሪ የአተገባበር ሥራዎችን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በግጭቱ የተጎዱትን መልሶ ማቋቋምን ጨምሮ ተጎጂዎችን ያማከለ የሽግግር የፍትሕ ሂደት እና ተጠያቂነትን ለማስፈን  የስምምነቱ ፈራሚዎች መገናኘታቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ አድርገዋል።

የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ ለማስፈታት፣ ለመበተን እና ወደ ማህበረሰቡ መልሶ ለማዋሃድ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ የገለፁት እነዚህ የበለፀጉ ሀገራት በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች የተከሰቱት ቀውሶች በተመሳሳይ ቁርጠኝነት ችግሩ እንዲፈታ ጥሪ አቅርበዋል።ሁለቱ ተዋናዮች በቀጣዮቹ ጥቂት ወራት ውስጥ ተመሳሳይ ውይይት ለማድረግ ስለመወሰናቸውም ተነግሯል።

በፌደራል መንግስት በኩል ይህ ውይይት እስከተካሄደበት ጊዜ ድረስ የተባለ ነግር የለም። ሕወሐት ከውይይቱ በኋላ ባወጣው መግለጫ 

  • ተክስ ሙሉ በሙሉ መቆሙ
  • ሕዝባዊ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሥራ መጀመራቸውን
  • በተወሰነ መልኩ የዕርዳታ እህል እየቀረበ መሆኑን በአወንታዊ መልኩ የገለጸ ሲሆን

አልተፈጸሙም ያላቸው ደግሞ

  • የስምምነቱ ዋነኛውናመሰረታዊው ክፍል ሙሉ በሙሉ እንዳልተገበረ በመግለጽ ከነዚህም
  • የኤርትራና የአማራ ሃይሎች ከትግራይ አለመውጣታቸውን ስለሆነም ከትግራይ ክልል 40 በመቶው አሁንም በነሱ ቁጥጥር ስር መሆኑን
  • በዚህ ምክንያት 1 ሚልዮን ተፈናቃዮችና በ10 ሺ የሚቆጠሩ በስደት የሚገኙ መመለስ እንዳልተቻለ
  • የትግርይ ሰራዊት አባላት ለማሰነባት የሚያስችል በጀት ስላልተለቀቀ ማሰናበት እንዳልተቻለ
  • የ2014 በጀት እስከ አሁን ስላልተለቀቀ የመንግስት ሰራተኞችና የጡረተኞች ደመወዝ መክፈል እንዳልተቻለ በመጥቀስ ከፌደራል መንግስት ጋር ተፈጥሮ የነበረውን የመተማመን መንፈስ እየተሸረሸረ መሆኑን ይህም ለቀጣይ ሰላም እንዳማያግዝ ገልጿል።

``ከፕሪሪቶሪያ የግጭት ማቆም ስምምነት ትግበራ ምን እንማር`` በሚል ርስ የተካሄደውን ውይይት የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን እንዲያዳምጡት በአክብሮት እንጋብዛለን።

ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር