1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የውጭ ምንዛሪ ተመን በገበያ እንዲመራ ስለመደረጉ የሕዝብ አስተያየት

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 23 2016

መንግሥት የውጭ ምንዛሬ ተመን በገበያ እንዲመራ ማድረጉን ካሳወቀበት ግዜ አንስቶ የተለያዩ አስተያየቶች ይሰማሉ ። ገሚሱ ሲጠብቁት የነበር ነው እሰየው ሲሉ፤ ገሚሱ ደግሞ አሁን በሀገሪቱ ያለውን የኑሮ ውድነት ያባብሰዋል የሚል ስጋት አላቸው ። ውሳኔው ሀብታሙን እንጂ ድሀውን የበለጠ ድሃ የሚያደርግ ነው ይላሉ ። አስተያየቶቹን አሰባስበናል ።

https://p.dw.com/p/4iuwb
  Ethiopia / Addis Ababa 02.01.2024
ምስል Seyoum Getu/DW

«ሀብታሙን እንጂ ድሀውን የበለጠ ድሃ የሚያደርግ ነው» አስተያየት ሰጪዎች

በኢትዮጵያ  መንግሥት የውጭ ምንዛሬ ተመን በገበያ እንዲመራ ማድረጉን ካሳወቀበት ግዜ አንስቶ  የተለያዩ አስተያየቶች ይሰማሉ ። ገሚሱ ሲጠብቁት የነበር ነው እሰየው ሲሉ፤ ገሚሱ ደግሞ አሁን በሀገሪቱ ያለውን የኑሮ ውድነት ያባብሰዋል የሚል ስጋት አላቸው ።

ውሳኔው  ሀብታሙን የሚጠቅም እንጂ ድሀውን የበለጠ ድሃ የሚያደርግ ነው  ይላሉ ። በኢትዮጵያ ደሀ የደሀ ደሀ እና ፍፁም ደሀ በሚል የኑሮ ደረጃ  ባለባት ሀገር መንግስት ይህንን  ከዓለማቀፍ የገንዘብ ተቁዋም ጋር የብድር እዳ መግባቱ ከድጡ ወደማጡ ነው የሚሉም አሉ ። 

72 ሰአታት ያስቆጠረውን የውጭ ምንዛሬ ተመን ውሳኔን ተከትሎ  በአዲስ አበባ የተለያዩ ቦታዎች ነዋሪዎችን አስተያየት አሰባስበናል ። «ዶላሩ ዋጋው ሲጨምር በኑሯችን ላይም» ጫናው መጨመሩ አይቀርም የሚል አስተያየት የሰጡ አሉ ።

ውሳኔው ጥቅምም ጉዳትም አለው ያሉ ሌላ አስተያየት ሰጪ ደግሞ «በተለይ እያደጉ ላሉ ሃገራት እደዚህ ማድረጉ በጣም ከባድ ነው» ያሉት ሌላ አስተያየት ሰጪ፦ የዶላር ምንዛሬ መጨመሩ በሸቀጦች ላይ ከፍተኛ ጭማሪ ስለሚያሳይ ተጎጂው ኅብረተሰቡ ነው የሚል አስተያየት አክለዋል ። ሌሎች አስተያየቶችንም አካተናል ። 

ለዶቸቨሌ ሀሳባቸውን የገለፁ ኗሪዎች አሁን ካለው አስቸጋሪ የኑሮ ውድነት የባሰ እንዳይጨምር መንግስት እና ነጋዴዎች መምከር አለባቸው ብለዋል ። የኢትዮጵያ መንግሥት የኤኮኖሚ ማሻሻያ በማድረጉ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ብድር ያገኛል ተብሏል ። 

ሐና ደምሴ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አዜብ ታደሰ