1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦሮሚያ ክልል አሁናዊ የጸጥታ ይዞታና የህብረተሰብ ፍላጎት

ዓርብ፣ ሰኔ 7 2016

በኦሮሚ ክልል ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የጸጥታ ሁኔታ አንጻራዊ መረጋጋት አሳይቷል ቢባልም ፤አሁንም ግን አልፎ አልፎ በሚስተዋል የተፋላሚዎች ግጭት የክልሉ ማኅበረሰብ ከስጋት አለመውጣቱ እየተነገረ ነው፡፡

https://p.dw.com/p/4h3Hi
Äthiopien Oromia-Region West Shoa
ምስል Seyoum Getu/DW

የኦሮሚያ ክልል አሁናዊ የጸጥታ ይዞታና የህብረተሰብ ፍላጎት

በኦሮሚ ክልል ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አንጻራዊ መረጋጋት አሳይቷል የተባለው የጸጥታ ይዞታ አሁንም ግን አልፎ አልፎ በሚስተዋል የተፋላሚዎች ግጭት የክልሉ ማህበረሰብ ከስጋት ውጪ አለመሆኑ ይነገራል፡፡ የተጥታ ችግሩ አሁንም ጎልተው ከሚስተዋልባቸው አከባቢዎች ተጠቃሽ ነው የሚባልለት እንደ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ያሉ ዞኖች አሁንም አልፎ አልፎ በሚፈጠር መደበኛ ውጊያ እና ከዚያም ውጪ ባሉ የታጣቂዎች እንቅስቀሴ የማህበረሰቡ መደበኛ ኑሮ ክፉኛ እንደሚፈተን እየተነገረ ነው፡፡


በግጭቱ አለመቋጨት የሚደርሱ ሰብኣዊ ፈተናዎች

ከደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን አስተያየታቸውን የሰጡን ነዋሪ ለደህንነታቸው ስባል ትክክለኛ የመኖሪያ አድራሻቸውን ከመግለጽ ብቆጠቡም በዞኑ በተለያዩ ወረዳዎች ይፈጸማል ባሉት የመንግስት እና የታጣቂዎች ፍልሚያ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚወርደውን የግጭቱ ዳፋን በተመለከተ ትዝብታቸውን አጋርተውናል፡፡ እንደ አስተያየት ሰጪው ባለፉት ሁለት ዓመታት የደፈረሰው በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች የጸጥታ ይዞታ አሁንም ተረጋጋ ለማለት የሚያስደፍር አልሆነም፡፡ አልፎ አልፎም በመንግስት እና በታጣቂ ኃይሎች መካከል የሚደረግ መደበኛ ውጊያ መኖሩን በአስተያየታቸው ጠቁመው፤ ከመደበኛ ውጊው ይልቅ ግን በሁለቱም ወገን ሌላውን ወገን በመደገፍ ሚጠረጠሩ የህብረተሰቡ ክፍሎች ላይ የሚደርሰው ጫና ጉልህ ነው ብለዋል፡፡“ለኦሮሞ ሰላም ይገባዋል” ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ

“በዞኑ አሁንም ተረጋጋ የሚባለው ነገር ብዙም የለም፡፡ ከሁለት ዓመታት በፊት በዞኑ የተጀመረው ግጭት አሁንም አለ፡፡ በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች እና በታጠቁ አካላት መካከል የሚደረጉ ግጭቶች ጋፋው የሚወርደው ሰላማዊ ህብረተሰቡ ላይ ነው፡፡ መደበኛ ግጭት ከሚደረግበት ወቅትም ውጪ ቀን ቀን የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ሌሊት ላይ ደግሞ በሌላ በኩል ታጥቀው ሸምቀው የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ አካላት አንዱ ሌላኛውን በመደገፍ ህብረተሰቡ ላይ ጫና ያሳድራሉ፡፡ ከዚህ የተነሳ የትኛውንም የታጠቀ አካል ሲያይ ማህበረሰቡ ከፍተኛ ጫና ውስጥ ይወድቃል” ነው ያሉት፡፡

ግጭት የተስፋፋባቸው አከባቢዎችና የግጭቱ ዳፋ በኢኮኖሚው ላይ

ሰደን ሶዶ፣ በቾ፣ ቀርሳ፣ እንደ መቂ ካሉ የምስረሰቅ ሸዋ ዞኖን ወረዳ ጋር የሚያያዘው ሶዶ ዳጪ እና ቶሌ የሚባሉ የዞኑ ወረዳዎች ግጭቱ ከሚጎላባቸው አከባቢዎች ስለመሆናቸውም ተጠቅሷል፡፡ ከምእራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ጋር የሚገናኘው ሌላናው የዞኑ ወረዳ አመያም ግጭቱ ከምጎላባቸው የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ወረዳዎች እንደሚጠቀስ ተጠቁሟል፡፡ በነዚህ አከባቢዎች አልፎ አልፎ ከሚስተዋለው መደበኛ ውጊያ ይልቅ በየጊዜው የሚደረጉ አንዱ ወገን የሌላውን ወገን በመደገፍ ህብረተሰቡን ስጠረጥር የሚፈጸም ጥቃት ማህበረሰቡን የሚያስመርር ነው ተብሏልም፡፡

ይህ ደግሞ የአከባቢውን ማህበረሰብ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቀሴ ክፉኛ ስለመጉዳቱ ተነግሯልም፡፡ “ለምሳሌ ገበሬው ማዳበሪያ በሚፈልግበት ባሁን ወቅት ተሽከርካሪዎች ከዋናው አስፓልት ወደ ውስጥ ለመግባትበማይደፍሩበት ባሁን ወቅት ከፍተኛ መጉላላት ነው የሚስተዋለው” የሚሉት አስተያየት ሰጪው ድሮ በብዛት የሚንቀሳቀሰው የህዝብ ትራንስፖርት አሁን ላይ ሾፈሮችን ጨምሮ በተጓዦች ላይ በሚደርስ ጥቃት ምክንያት እምብዛም የሚንቀሳቀስ ትራንስፖርት አለመኖሩን አመልክተዋልም፡፡ ይህ ደግሞ በኢኮኖሚው በተለይም ደግሞ በንግድና ግብርናው ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ እያሳደረ እንደሚገኝ ነው የተጠቆመው፡፡ በታጣቂዎች በኩል ገንዘብ የሚጠቀየቁ ነጋዴዎች በመንግስትም በኩል ታጣቂውን አካል ደግፋችዋል በሚል ስለሚጠየቁ በርካታ ነጋዴዎች በተሌም ከገጠር ከተሞች ለቀው መውጣታቸውንም አስተያየት ሰጪ እማኙ የታዘቡትን በሃሳባቸውን አካፍለውናል፡፡

በኦሮሚ ክልል ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አንጻራዊ መረጋጋት አሳይቷል የተባለው የጸጥታ ይዞታ አሁንም ግን አልፎ አልፎ በሚስተዋል የተፋላሚዎች ግጭት የክልሉ ማህበረሰብ ከስጋት ውጪ አለመሆኑ ይነገራል፡፡
በኦሮሚ ክልል ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አንጻራዊ መረጋጋት አሳይቷል የተባለው የጸጥታ ይዞታ አሁንም ግን አልፎ አልፎ በሚስተዋል የተፋላሚዎች ግጭት የክልሉ ማህበረሰብ ከስጋት ውጪ አለመሆኑ ይነገራል፡፡ ምስል Seyoum Getu/DW

ይህ ደግሞ የንግድ እንቅስቃሴውን በአከባቢው ክፉኛ አቀዝቅዞታልም ነው ያሉት፡፡ “ማታ ማታ አልፎ አልፎ ግጭቶች ውጊያዎች ይኖራሉ፡፡ ይህ ደግሞ ማህበረሰቡ በምኖርበት አከባቢ ስለሚደረግ ከፍተኛ የደህንነት ስጋት ላይ ነው የሚጥላቸው” ብለዋልም፡፡ “አልፎ አልፎ በስጋትም ብሆን ከሚገበያይበት ውጪ ማህበረሰቡ ገበያም ወጥቶ ለመንቀሳቀስ በብርቱ ይፈተናል” የሚሉት አስተያየት ሰጪው አንዴ ሰላም እየሰፈነ ሌላ ጊዜ ደግሞ ግጭት እየተነሳ ማህበረሰቡ የስጋት ኑሮ እንደሚገፋም ነው በአስተያየታቸው ያመለከቱት፡፡

ግጭቱ የፈጠረው ማህበራዊ ቀውስ

ለደህንነታቻው ስባል ስማቸውም ሆነ ድምጻቸውን እንዳንጠቀም ጠይቀው አስተያየታቸውን የሰጡን ሌላው የአከባቢው ነዋሪ በተለይም ወደ ትምህርት እና ሌሎች ዘርፎች መሰማራት የነበረባቸው ወጣቶች በዚህ የእርስበርስ ግጭት ውስጥ ተሳታፊ መሆናቸው እጅጉን አስጊ መሆኑን አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ አጋርተዋል፡፡በኦሮሚያ እና አማራ ክልል አዋሳኝ ለዳግም መፈናቀል የዳረገ ግጭት

በአንጻሩ ግን ከሰሞኑ በይፋዊ ማህበራዊ ገጻቸው “አንድነት ይታደስ! ሰላም ይስፈን” የሚል ርዕስ በሰጡት ዘለግ ያለ ጽሁፍ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ክልሉ የሰላም አየር የሰፈነበትና “የህዝባችን ሰላም ስያደፈርሱ የነበሩ አካላት” ያሏቸው “ወደ ቀልባቸው ተመልሰው ለሰላም የተገዙበት” ነው ብለዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ በጽሁፍ ባሰፈሩት አስተያየታቸው ይህ ወር በክልሉ በስፋት በጸጥታ ችግር ምክኒያት የተቋረጡ የማህበራዊ አገልግሎት ሁሉ ዳግም የተጀመሩበት ነው ብለው በክልሉ ሰፍኗል ላሉት ሰላም አስተዋጽኦ ያበረከቱ ያሏቸው አካላትንም አመስግነዋል፡፡

በኦሮሚ ክልል  አልፎ አልፎ በሚስተዋል የተፋላሚዎች ግጭት የክልሉ ማህበረሰብ ከስጋት ውጪ አለመሆኑ ይነገራል፡፡
በኦሮሚ ክልል አልፎ አልፎ በሚስተዋል የተፋላሚዎች ግጭት የክልሉ ማህበረሰብ ከስጋት ውጪ አለመሆኑ ይነገራል፡፡ምስል Seyoum Getu/DW

እየተሻሻለ ነው ያሉት የክልሉን የጸጥታ ይዞታ ዘላቂ የማድረግ ስራ ቀጣዩ የቤት ስራቸው መሆኑን ያልሸሸጉት ርዕሰ መስተዳድሩ ለሰላም የተዘረጋ ያሉት የመንግስታቸው እጅ አለመንጠፉን ገልጸው ሰላማዊ መንገድን ተቀብለው ወደ ማህበረሰቡ የተመለሱ የቀድሞ ታጣቂዎችን ከማህበረሰቡ ጋር የማዋሃድ ስራ እንደሚጠብቃቸውም ጠቁመዋል፡፡ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ታጥቀው በክልሉ ለምንቀሳቀሱ ታጣቂዎችም በአንድነት በሰላማዊ መንገድ አብሮ የመስራት ጥሪን አቅርበዋል፡፡

ሙሉ ዝግጅቱን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።

ስዩም ጌቱ

ፀሀይ ጫኔ

ሂሩት መለሰ