1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤርትራ መንግሥት የበረራ አገልግሎት እግድና ኢትዮጵያ አየር መንገድ ምላሽ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 18 2016

የኤርትራ መንግሥት የአቪየሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ ወደ አስመራ በረራ እንዳያደርግ ያገደበት ውሳኔ ላይ ለመነጋገር እና ለመመካከር ሙከራ እያደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ። አየር መንገዱ የተፈጠረው ችግር በሰላም ተፈትቶ ወደነበረበት እንደሚመለስ ተስፋ ያደርጋል።

https://p.dw.com/p/4ijJa
Äthiopien | Ethiopian Air Lines unterzeichnete eine Vereinbarung mit Boeing über den Kauf von 777X-9
ምስል Seyoum Getu/DW

የኤርትራ አቪዬሽን ባለስልጣን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ዕግድ ጣለ

የኤርትራ መንግሥት የበረራ አገልግሎት እግድ፣ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ምላሽ

የኤርትራ መንግሥት የአቪየሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ ወደ አስመራ በረራ እንዳያደርግ ያገደበት ውሳኔ ላይ ለመነጋገር እና ለመመካከር ሙከራ እያደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተፈጠረው ችግር በሰላም ተፈትቶ ወደነበረበት ይመለሳል ብሎ እንደሚያስብም የተቋሙ የሥራ ኃላፊ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።

የመጀመሪያው የአስመራ በረራ

ሀገራት የበረራ አየር ክልላቸውን የመቆጣጠር ሙሉ ሥልጣን እንዳላቸው የገለፁ አንድ የበረራ አገልግሎት ባለሙያ፣ እንዲህ ያሉ ውሳኔዎች ሊወሰኑ የሚችሉት "ከፍተኛ የሆነ የደህንነት ሥጋት የሚጥል ነገር በአየር መንገዱ ተደርጎ ቢገኝ ነው" በማለት ጉዳዩ "የፖለቲካ ውሳኔ ካልሆነ በስተቀር ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በቀጥታ የሚገናኝ ነው ብየ አላምንም" ብለዋል።//

የጎረቤት ሀገር ኤርትራ ሲቪል አቪዬሽን ከአዲስ አበባ ወደ አስመራ የሚደረጉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎች ከመስከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እንዲቋረጡ ወይም በረራ እንዳይደረግ እግድ ጥሏል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞች ማስተናገጃ ማስፋፊያ

ጋዜጣ ላይ ታትሞ በማሕበራዊ የትስስር ዐውታሮች የተዘዋወረው ይህ የእግድ ትእዛዝ በደብዳቤ በግልጽ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዳልደረሰው የአየር መንገዱ የኮርፖሬት ኮምዩኒኬሽን ኃላፊ ወይዘሮ ሐና አጥናፉ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።

"ሲዘዋወሩ የነበሩ መልእክቶች አሉ። እነሱ ለእኛ ቀጥታ የተላኩልን አይደለም። እኛም እንደሌላው ሰው ማህበራዊ ሚዲያው ላይ ነው እንጂ ያየነው ለእኛ የተላከልን ደብዳቤ ከእሱ የተለየ ነው"።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ ከተማ አድርጎ የነበረው የመጀመሪያው በረራ
የጎረቤት ሀገር ኤርትራ ሲቪል አቪዬሽን ከአዲስ አበባ ወደ አስመራ የሚደረጉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎች ከመስከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እንዲቋረጡ ወይም በረራ እንዳይደረግ እግድ ጥሏል።ምስል Reuters/T. Negeri

 መንገደኞችን ያሳፈረዉ የመጀመርያዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዉሮፕላን አስመራ ገባ

የኤርትራ ሲቪል አቭዬሽን ለእግዱ መነሻ ያላቸው ጉዳዮች

የኤርትራ ሲቪል አቭዬሽን ይህንን ውሳኔ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተጓዦች ላይ ምክንያታዊ ያልሆነ የበረራ ቲኬት ዋጋ ጨምሯል፣ ስልታዊ እና የተደራጀ ያለው የሻንጣ ስርቆት ተፈጽሟል፣ ተገቢነት የሌላቸው ያላቸውን የንግድ ተግባራትን ተከትሏል፣ ተደጋጋሚ የበረራ እና የሻንጣዎች መዘግየት ታይቶበታል፣ ለእነዚህም ካሳ እየከፈለ አይደለም ሲል ጠቅሷል። የኤርትራ መንግሥት የኢትዮጵያ አየር መንገድ እነዚህን ችግሮች እንዲያርም እድል ቢሰጠውም ያንን ማድረግ አልቻለም በሚል ወቀሳ ቢቀርብበትም፣ አየር መንገዱ ግን ይልቁንም የበረራ ማስፋፊያ እንድናደርግ ነው ተነግሮን ስንዘጋጅ የነበረው ሲሉ የኮሙኒኬሽን ኃላፊዋ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ አውሮፕላን ግዢ

"ከሰኞ እስከ እሑድ ያሉት ቀናት በቀን ሁለት በረራ እንድናደርግ አርብ አርብን በቀን ሦስት በረራ እንድናደርግ 15 በረራዎችን በሳምንት የሚፈቅድ ደብዳቤ ከዚሁ ከሲቪል አቪየሽን ደርሶን እዛ ላይ ዝግጅት ላይ ነው የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ"።

የአቪየሽን ባለሙያ አስተያየት

ለመሆኑ የኤርትራ መንግሥት የአቬሽን ዘርፍ ያቀረባቸው ምክንያቶች በረራ እስከማገድ የሚያደርሱ ናቸው? ስንል 

የኢትዮጵያ ኢሮክለብ መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት የአቬሽን ባለሙያ ዮናታን መንክርን ጠይቀናቸዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ነቀምቴ የጀመረው በረራ

ሀገራት የበረራ አየር ክልላቸውን የመቆጣጠር ሙሉ ሥልጣን እንዳላቸው የገለፁ አንድ የበረራ አገልግሎት ባለሙያ፣ እንዲህ ያሉ ውሳኔዎች ሊወሰኑ የሚችሉት "ከፍተኛ የሆነ የደህንነት ሥጋት የሚጥል ነገር በአየር መንገዱ ተደርጎ ቢገኝ ነው" በማለት ጉዳዩ "የፖለቲካ ውሳኔ ካልሆነ በስተቀር ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በቀጥታ የሚገናኝ ነው ብየ አላምንም" ብለዋል

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ችግሩ ተሻሽሎና ተፈትቶ ወደ ነበረበት እንመለሳለን የሚል ተስፋ እንዳለውም ወይዘሮ ሐና ተናግረዋል።

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ

እሸቴ በቀለ