1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ውዝግቦችአፍሪቃ

የቫግነር እጣ ፋንታ በአፍሪቃ

ዓርብ፣ ነሐሴ 19 2015

ሩስያ ውስጥ በተከሰከሰ አውሮፕላን ውስጥ የቫግነሩን መሪ ይቭጌኒ ፕሪጎዥን ጨምሮ አስር ሰዎች መሞታቸውን የሩሲያ የ አቪዬሽን ባለስልጣን ገልጿል። ይህንን ተከሎ እሳቸው የሚመሩት የቫግነር ወታደራዊ ቡድን እጣ ፋንታ እያነጋገረ ነው። በአፍሪቃ ቀጣይነት ይኖረዉ ይሆን?

https://p.dw.com/p/4Vatx
የቫግነር እጣ ፋንታ በአፍሪቃ
የቫግነር እጣ ፋንታ በአፍሪቃ ምስል Leger Kokpakpa/REUTERS

በተለያዩ ሀገራት በተለይም በምዕራብ እና መካከለኛው አፍሪቃ የቫግነር ቡድን በሚያደርጋቸው የቅጥረኛ እንቅስቃሴዎች ሩሲያ በአፍሪካ ያላት ተፅእኖ በጣም ሰፊ ነው። ነገር ግን የዋግነር መሪ የፍገኒ ፕሪጎዥን ሩስያ ውስጥ በተከሰከሰ አውሮፕላን ሳይሞት እንዳልቀረ የሚገልጹ ዘገባዎች መውጣታቸውን ተከትሎ  ወታደራዊ ቡድኑ በአፍሪቃ ሀገራት በሚያደርገውን  ወታደራዊ ድጋፍ መልኩን ሊለወጥ ይችላል የሚል ግምት በብዙዎች ዘንድ አሳድሯል። ቫግነር ግሩፕ በአፍሪቃ አሁን ያለዉ ተፅእኖ ምንድን ነው?
የማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ  የሲቪል ማህበረሰብ አባል የሆኑት ክርስቲያን አሚ ንዶታህ  ግን ፕሪጎዥን መሞቱ ከተረጋገጠ ምንም ለውጥ አያመጣም ብለው ያምናሉ።እሳቸው እንደሚሉት  «የእሱ ሞት ከተረጋገጠ በሩሲያ ወይም በዋግነር እና በማዕከላዊ አፍሪቃ መካከል ያለውን ትብብር አይጎዳውም።.ምክንያቱም ዋግነር ለበርካታ ዓመታት በእነዚህ ሀገራት ጥሩ መሰረት አለው።» ይላሉ።
በአፍሪካ የዋግነር ስራዎችን የሚከታተሉት የአደጋ እና የደህንነት ባለሙያ ዶክተር አዳሙ ካቢሩን  ተመሳሳይ ሀሳብ አላቸው። 
«በጣም አስደናቂ  ጥያቄ ነው ብዬ አስባለሁ። የፑቲንን አስተዳደር በመቃወም የመጀመርያውን የአመፅ እርምጃ የተመለከትን ይመስለኛል። ያ ሙከራ  ሲከሽፍ ቢያንስ ተመልሶ እንዲሰራ ጥሪ  ተደርጎለታል።ነገር ግን በአፍሪካ አህጉር  ባለው የዋግነር እንቅስቃሴ ላይ  ምንም አይነት ለውጥ አላመጣም ነበር ።»ማሊ ከምዕራባውያኑ ያላትን የሻከረ ግንኙነት
የቭላድሚር ፑቲን የቅርብ ሰው እና ምግብ አብሳይ እንደነበሩ የሚነገርላቸው እኝህ የዋግነር መሪ  ከጥቂት ወራት በፊት  የፑቲንን አስተዳደር  በሚፃረር መልኩ የከሸፈ የአመፅ  ሙከራ አድርገዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃም ለሩሲያ የግል ወታደራዊ  ኃይል በማደራጄት እንደ ጨካኝ የቅጥረኛ  ቡድን መሪ ተደርገው ይታያሉ።ያም ሆኖ የእሳቸው ወታደሮች አፍሪካ ውስጥ ደኅንነትን ለመጠበቅ እና ወታደሮችን ለማሰልጠን ተሰማርተዋል።በመሆኑም  የእኝህ ሰው አለመኖር በአፍሪቃ ውስጥ የሚደረገውን ወታደራዊ አገልግሎት ያዳክመው ይሆን? ዶክተር አዳሙ ካቢሩን።  የሩሲያዉ የቅጥረኛ ወታደሮች ኩባንያ ባለቤት ፕሪጎዥን ሞተዋል?
«የቫግነርን ቡድን አወቃቀር በተለያዩ ሀገራት ማለትም በማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ፣ ማሊ ሱዳን እና ሊቢያ በቡሪኪናፋሶ ስንመለከት  ሀገራዊ ኮማንድ በሚባሉት እና በፑቲን አስተዳደር  መካከል ያለው ግንኙነት መቻቻል ነበር። ተልዕኳቸውንም ያለ ምንም ችግር  ሳያቋርጡ ያከናውኑ ነበር። ፕሪጎዥን ተልዕኮውን በሚታይ ሁኔታ እየመራ ባልነበረበት ወቅትም፤ ወታደራዊ ሀይሉ በገባባቸው የአፍሪቃ ሀገሮች ሁሉ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች እና ዘመቻዎች በተለመደ መልኩ ይካሄዱ ነበር።» በጎርጎሪያኑ 2014 ዓ.ም የተመሰረተው የቫግነር ወታደራዊ ቡድን የሞስኮን አጋር ሀገሮች ወታደራዊ እና የደህንነት ድጋፍ ይሰጣል።ቡድኑ እስካሁን  ሶርያ፣  ሊቢያ እና ማዕከላዊ አፍሪቃን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት ተሰማርቷል።ያም ሆኖ የቫግነር ቡድን በዩ ኤስ አሜሪካ ማዕቀብ የተጣለበት እና በሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚወቀስ ቡድን ነው። 

የቫግነር እጣ ፋንታ በአፍሪቃ
የፍገኒ ፕሪጎዢን፤የብላድሚር ፑቲን የቅርብ ሰው እና ምግብ አብሳይ እንደነበሩ የሚነገርላቸው እኝህ የዋግነር መሪ  ከጥቂት ወራት በፊት  የፑቲንን አስተዳደር  በሚፃረር መልኩ የከሸፈ የአመፅ  ሙከራ አድርገዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃም ለሩሲያ የግል ወታደራዊ  ኃይል በማደራጄት እንደ ጨካኝ የቅጥረኛ  ቡድን መሪ ተደርገው ይታያሉምስል PMC Wagner/Telegram/REUTERS
የቫግነር እጣ ፋንታ በአፍሪቃ
የዋግነር መሪ የፍገኒ ፕሪጎዢን ሩስያ ውስጥ በተከሰከሰ አውሮፕላን ሳይሞት እንዳልቀረ የሚገልጹ ዘገባዎች መውጣታቸውን ተከትሎ  ወታደራዊ ቡድኑ በአፍሪቃ ሀገራት በሚያደርገውን  ወታደራዊ ድጋፍ መልኩን ሊለወጥ ይችላል የሚል ግምት በብዙዎች ዘንድ አሳድሯልምስል AP Photo/picture alliance

ፀሀይ ጫኔ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ