1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስደተኞች ምላሽ ማዕቀፍ ተግባራዊነት በኢትዮጵያ

ማክሰኞ፣ የካቲት 21 2015

ኢትዮጵያ ውስጥ የስደተኛ ተቀባይ ክልሎች የአካባባቢ አስተዳደሮች ከዓለማቀፍ የስደተኞች ምላሽ ማዕቀፍ አንጻር ሚናቸው አናሳ መሆኑን ጥናቶች አመለከቱ ።

https://p.dw.com/p/4O59j
Äthiopien | Mai Aini Flüchtlingscamp
ምስል EDUARDO SOTERAS/AFP/Getty Images

በስደተኞች እና ተገን ጠያቂዎች አቀባበል እና አስተዳደር በኢትዮጵያ እና አንድምታው

ዓለማቀፍ የስደተኞች እና የተገን ጠያቂዎች አያያዝ እና አስተዳደር ወጥ በሆነ ማዕቀፍ ባለመመራቱ እና ድንበር ተሻጋሪ ስደተኞች እና ተገን ጠያቂዎች አያያዝ እየተባባሰ መምጣቱን ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተቀናጀ የስደተኞች በጎርጎርሳውያኑ አጠቃላይ የስደተኞች ምላሽ ማዕቀፍ አዘጋጅቶ ከጎርጎርሳውያኑ 2018 ጀምሮ በሁሉም አባል ሀገራት ተግባራዊ ይደረግ ዘንድ ይሁንታውን ሰጥቷል።  
የኒውዮርኩ ስምምነት ስደተኞች እና ተገን ጠያቆዎችን የሚያስተናግዱ ሃገራት እና ማህበረሰቡን በአግባቡ ለመደገፍ እና እነዚሁ አካላት ከመንግስታት፣ ዓለምአቀፍ የሲቪል ፣ የገንዘብ እና የረዲኤት ተቋማት ጋር በአጋርነት የሚሩበትን መንገድ ያመላክታል።
ትናንት እዚህ ቦን የተካሄደው የባለሞያዎች ምክክር መድረክ ከስደተኞች እና ተገን ጠያቂዎች አያያዝ እና አስተዳደር አንጻር ይታዩ የነበሩ ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት ከዓለማቀፉ የፖሊሲ ማዕቀፍ አተገባበር አንጻር የኢትዮጵያን ተጨባጭ ሁኔታ የተመለከቱ  ጥናቶችን አድምጧል።
ኢትዮጵያ ከአጎራባች ሀገራት ተቀብላ እያሰተናገደች ካለው 840 ሺ በላይ ስደተኞች እና ተገን ጠያቂዎች ውስጥ ከ360 ሺ  በላይ ወይም ከ44  በመቶ በላይ ስደተኞች እና ተገን ጠያቂዎችን ተቀብሎ እያስተናገደ የሚገኘው የጋምቤላ ክልል ነው። ክልሉ በዘርፈ ብዙ የጽጥታ እና አስተዳደራዊ ችግሮች ውስጥ ሆኖም አስርት ዓመታት የተሻገረውን ስደተኞች ተቀብሎ እያስተናገደ ነው። ነገር ግን በክልሉ ከሚገኙ የስደተኞች እና ተገን ጠያቂዎች አንጻር ዓለማቀፉ አጠቃላይ የስደተኞች ምላሽ ማዕቀፍ ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር ተግዳሮቶች ገጥመውታል። ትኩረት ለአፍሪቃውያን ስደተኞች
አቶ ግዛቸው ተሾመ በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የሰላም እና ደህንነት ረዳት ፕሮፌሰር ናቸው ። ከዓለማቀፍ የስደተኞች እና ተገን ጠያቂዎች አያያዝ እና አስተዳደር አንጻር በጋምቤላ የስደተኞች ምላሽ ማዕቀፍን ተግባራዊ ለማድረግ በየደረጃ ያሉ የመንግስት አካላት በሂደቱ የነበራቸው ተሳትፎ አነስተኛ መሆኑን  በጥናቱ መለየቱን ይናገራሉ። 
«የክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የአካባቢ ባለስልጣናት ምን ያህል ትርጉም ያለው ተሳትፎ አላቸው ሚለው ላይ ነው።  እና በአጠቃላይ  በሂደቱ ላይ ብዙም የአካባቢ ተቋማት እና ባለስልጣናት ብዙም ያሳተፈ አካሄድ እንዳልነበረ  መገንዘብ ችለናል። »
 ይህን መሰል ዓለማቀፍ ፖሊሲዎች እንደ ጋምቤላ ባሉ በመሰረተ ልማት ወደ ኋላ በቀሩ እና በውስን አስተዳደራዊ አቅም በሚንቀሳቀሱ ክልሎች ላይ ተግባራዊ ለማድረግ ተጨባች ሁኔታዎችን ታሳቢ በማድረግ የስደተኞች አስተዳደር ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት እንደመፍትሄ መቀመጡን አቶ ግዛቸው ተናግረዋል። 
 «ጋምቤላ እንደሚታወቀው  ከሌሎች ክልሎች ጋር በመሰረተ ልማትም ሆነ  በህዝብ አስተዳደር ሲነጻጸር ደካማ የሚባል ነው።   እና በዚያ ላይ ይሄን ሁሉ ከፍተኛ ሃላፊነት ስትቀበል የአካባቢውን አቅም ሳታሳድግ ስለተተገበረ ይሄ አይነት ችግር አለ ማለት ነው። ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ተደራሽ ማድረግ ያስፈልጋል።»የስደተኛ ተፈናቃይ ቁጥር ማየል
በኢትዮጵያም ይሁን በተቀረው ዓለም የስደተኞች ጉዳይ የሚስተናገደው በዓለም አቀፍ ተቋማት ነው የሚሉት ደግሞ በጀርመን የስደተኞች ጉዳይ ጥናት ማዕከል ተመራማሪ የሆኑት አቶ ሳሙኤል ዘውዴ ናቸው ።  በትናንቱ የቦኑ ጥናታዊ የውይይት መድረክ የእርሳቸው የጥናት ማዕከል ከሌሎች የጀርመን የጥናት ማዕከላት የስደተኞች ተቀባይ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ  የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አጥኚዎች ጋር  በመሆን ስደተኞችን የሚያስተናግዱ የአካባቢ  ባለስልጣናት በስደተኞች አስተዳደር ውስጥ ሚናቸው ከፍ እንዲል የሚያበረታታውን የፖሊሲ አተገባበር መመልከታቸውን ገልጸውልናል። 
« ከአካባቢዎች አንጻር ስናይ ክልሉ ከተቋማዊ አደረጃጀት የመሰረተ ልማት አንጻር በጣም የተሟላ ነገር የለውም ። ያንን በማስፋት እንደገና አካባቢያዊ ተቋማትን ከመገንባት ባሻገር  ተቋማቱም ያለባቸውን ችግሮች አምጥተው እነዚያ ችግሮች የሚፈቱበት ሂደት ውስጥ በሚገባ ተሳታፊ የሚኮንበት ፣የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ያለው የውሃ አገልግሎት አሰጣጥ የስደተኞች ብቻ ሳይሆን ለአካባቢውም የሚተገበርበት ሁኔታ መፍጠር ተገቢ እንደሆነ አይተናል።   »
በጀርመን ቀጣይነት ላለው ልማት የጥናት ማዕከል በእንግሊዘኛ ምህጻሩ IDOS ለአመታት በተመራማሪነት የሰሩት ወ/ሮ ያና ኩንድ እንዳሉት የጥናት ማዕከላቸው በአዲስ አበባ ፣ ጂግጂጋ እና ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲዎች ከሚገኙ የሰላም እና ደህንነት ጥናት ክፍሎች ጋር በመተባበር ዓለማቀፉን የስደተኞች ፖሊሲ አተገባበር በማጥናት በየደረጃው ላሉ የአካባቢ እና ዓለማቀፍ መንግስታት እና ተቋማት የፖሊሲ ግብአቶችን ለማቅረብ በመስራት ላይ ይገኛሉ።የአውሮጳ ኅብረትን ያሰጋው የስደተኞች ቀውስ
«ጥናታዊ መረጃውን ለማሰባሰብ ጀምረን አንዴ ስናቆም ደግሞ ስንጀምር  አንድ ዓመት ገደማ ያህል ወስዶብናል። በመጨረሻም መረጃውን ማሰባሰብ ችለናል። ከዚያም የተሰበሰበውን መረጃ ተንትነን ካጠናቀርን በኋላ ግኝታችን ይመከርበት ዘንድ ይዘን ወጣን ማለት ነው። ይህም  እዚህ ጀርመን በአውሮጳ ህብረት ደረጃ ያሉ የፖሊሲ አውጭዎች እንዲሁም ኢትዮጵያ ውስጥ በአፍሪቃ ህብረት ደረጃ ያሉ የፖሊስ አውጭዎችን ይመለከታል »
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን የጎርጎርሳውያኑ 2022 መረጃ እንደሚመለክተው ኢትዮጵያ 842,360 ስደተኞች እና 2,229 ተገን ጠያቂዎችን ተቀብላ በማስተናገድ ላይ ትገኛለች። 
በ2018 የጸደቀው የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ምላሽ ማዕቀፍ በእንግሊዘኛው ምህጻር CRRF በስደተኛ እና  ተገን ጠያቂ ተቀባይ ሀገራት ላይ ያለውን ጫና ከመቀነስ ባሻገር ፤ ስደተኞች ራሳቸውን እንዲችሉ ፤ በሶስተኛ ሀገራት አማካኝነት የመልሶ ማቋቋም መንገድ እንዲያገኙ እንዲሁም በፈቃደንነት ወደ ትውልድ ሀገራቸው እንዲመለሱ የሚያስችል ሁኔታ እንዲፈጠር የአካባቢ ባለስልጣናት ሚና እንዲያድግ ይጠይቃል። 

Garman Immigration stud institutions researchers
ምስል Tamirat Dinssa/DW
Garman Immigration stud institutions researchers
ምስል Tamirat Dinssa/DW

ታምራት ዲንሳ

ነጋሽ መሐመድ