1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብት ጥሰት በአማራ ክልል

እሑድ፣ ኅዳር 2 2016

ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ ግጭቶች እና ጦርነቶች እየተደጋገሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችም ከጊዜ ወደ ጊዜ እጅግ እየተባባሱ መምጣታቸው በተደጋጋሚ ተዘግቧል ። ጦርነቱ በቀጠለበት የአማራ ክልል የሰብአዊ መብት ጥሰቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱም ይነገራል ። ሙሉውን ውይይት ከድምፅ ማእቀፉ ማድመጥ ይቻላል።

https://p.dw.com/p/4YgJ6
ታሪካዊቱ የላሊበላ ከተማ
ታሪካዊቱ የላሊበላ ከተማ ውስጥ ጦር መሣሪያ ያነገበ ታጣቂምስል Solan Kolli/AFP/Getty Images

ከምንም በላይ ሕጻናት፤ ሴቶችና አረጋውያን ተጎጂዎች ናቸው

ኢትዮጵያውስጥ በተለይ ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ ግጭቶች እና ጦርነቶች እየተደጋገሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችም ከጊዜ ወደ ጊዜ እጅግ እየተባባሱ መምጣታቸው በተደጋጋሚ ተዘግቧል ። በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ጦርነት በቀጠለበት የአማራ ክልል የሰብአዊ መብት ጥሰቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱም ይነገራል ።

ሰሞኑን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ባወጣው መግለጫ፦ በአማራ ክልል ድሮንን ጨምሮ በከባድ ጦር መሣሪያዎች በተሰነዘሩ ጥቃቶችበሲቪል ሰዎች ላይ ሞት እና የአካል ጉዳት መድረሱን እንዲሁም 200 ሴቶች መደፈራቸውን ገልጿል ። ኢሰመኮ፦ በድሮን ጥቃት «የአንድ ዓመት ከሰባት ወር ሕፃንን ጨምሮ በርካታ ሲቪል ሰዎች እንደተገደሉ እና የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው» መገለጹ የሰብአዊ መብት ጥሰት ጥልቀቱን የሚያሳይ ነው ሲሉ በርካቶች ሥጋታቸውን ገልጸዋል ።

መግለጫውን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት «ትክክለኛ መረጃ ላይ ያልተመሰረተና ሚዛናዊነት የጎደለው ነው» ሲል ውድቅ አድርጎታል ። ለመሆኑ ጦርነቱ በቀጠለበት በአማራ ክልል የሰብአዊ መብቶች አያያዝ እና ጥሰቱ ምን ይመስላል? የዛሬው የእንወያይ መሰናዶዋችን የሚያተኩርበት ነጥብ ነው ። 

በዚህ ውይይት ተሳታፊ እንዲሆኑ ለመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ (ዶ/ር) እንዲሁም ለመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ በዶይቸ ቬለ በኩል የላክነው የኢሜል ግብዣም ሆነ የስልክ ጥሪ ውይይቱን እስካደረግንበት ጊዜ ድረስ ምላሽ አላገኘም ። ሦስት ተወያዮች ሐሳባቸውን የሚያቀርቡበት ሙሉውን ውይይት ከድምፅ ማእቀፉ ማድመጥ ይቻላል ።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ