1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ውዝግቦችኢትዮጵያ

በአማራ ክልል የቀጠለው ውጊያ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 28 2016

አማራ ክልል ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል አሁንም ውጊያ መኖሩን ዶቼ ቬለ በስልክ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገለፁ።

https://p.dw.com/p/4YZTx
ፎቶ ከማኅደር፤ ላሊበላ ቤተ ጊዮርጊስ
በላሊበላ አካባቢ በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የቀጠለው ውጊያ ታሪካዊ ቅርሶችን ለጉዳት እንዳይዳርግ ስጋት አለ። ፎቶ ከማኅደር፤ ላሊበላ ቤተ ጊዮርጊስምስል Solan Kolli/AFP/Getty Images

ከእማኞች አንደበት

 

አማራ ክልል ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል አሁንም ውጊያ መኖሩን ዶቼ ቬለ በስልክ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገለፁ። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ ባለፈው ሳምንት በሰጡት መግለጫ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ  ባደረገው ግምገማ «ሊፈርስ ተቃርቦ የነበረውን ክልል ከመፍረስ መታደግ መቻሉ ተረጋግጧል፤ አብዛኛው የክልሉ አካባቢዎች ወደ ሰላማዊ ሁኔታ ተመልሰዋል» በማለት ክልሉን የሚገኝበት ያሉትን ነባራዊ ሁኔታ ገልፀው ነበር። በጎጃም- ቡሬ ፣ በሰሜን ሸዋ - ሸዋ ሮቢት ፣ በወሎ - ላሊበላ ፣ በጎንደር - ወረታ ከተሞች ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች በከተሞች አካባቢ የመከላከያ ሠራዊት አባላት እንደሚገኙ ፣ የፋኖ ታጣቂዎች ደግሞ ከከተሞች ወጣ ባሉ ገጠራማ ስፍራዎች እንደሚገኙ ገልፀው ግጭቶችና ውጊያዎች አሁንም መኖራቸውን ተናግረዋል። 

ለዚህ ዘገባ ካነጋገርናቸው ሰዎች መካከል የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪው፤ «ባሕር ዳር ላይ ያለው ነገር አሁን ፀጥ ያለ ነው። ሰሞኑን በጢስ ዐባይ አካባቢ ነበረ [ ውጊያ]።» በማለት የገለጹ ሲሆን
በጎጃም መከላከያ ሠራዊት እናፋኖ ብርቱ ውጊያ ውስጥ ስለመሆናቸው የቡሬ ከተማ ነዋሪው ደግሞ ተናግረዋል። «ከባድ መሣሪያ ቀጥታ የሚተኮሰው ቤት ላይ ማረፍ ጀምሯል። ዜጎች ላይ ነው ማረፍ የጀመረው። ሕፃናትና አረጋዊያን ሳይቀሩ ነው እየተመቱ ያሉት።» ነው የሚሉት።
የሸዋሮቢት ከተማ ነዋሪው እንደሚሉት ደግሞ አንፃራዊ ሰላም የነበረ ቢሆንም ትናንት ምሽት «ያልታወቁ ተኩሶች ነበሩ ፣ ዛሬ ጠዋት መንገድ ተዘግቷል።» ይላሉ።
በደቡብ ጎንደር የወረታ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ሴት እንደነገሩን ከሆነ ደግሞ የከተማው የመስተዳድር አካላት ሕዝብ ግብር እንዲከፍል ቢጠይቁም የፋኖ ታጣቂዎች ያንን ከልክለዋል። ሕዝብ ገንዘብ ከባንክ ማውጣትም ተቸግሯል ብለዋል።

Israel rescues some 200 citizens and Jews from Ethiopia conflict region
ምስል AP/picture alliance


የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ ባለፈው ሳምንት በሰጡት መግለጫ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ ባደረገው ግምገማ «ሊፈርስ ተቃርቦ የነበረውን ክልል ከመፍረስ መታደግ መቻሉ ተረጋግጧል፤ አብዛኛው የክልሉ አካባቢዎች ወደ ሰላማዊ ሁኔታ ተመልሰዋል» በማለት ክልሉን የሚገኝበት ያሉትን ነባራዊ ሁኔታ ገልፀው ነበር።
ጦርነቱ በታጣቂ ኃይሎች ብቻ ሳይሆን በሰላማዊውና ባልታጠቀው ህዝብም ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ ነው ሲሉ ሰሞኑን በጽሑፍ የገለፁት የላሊበላ ተወላጅ የሆኑት ታዋቂው ፖለቲከኛ አቶ ልደቱ አያሌው «ጥንቃቄ በጐደለው ሁኔታ በአካባቢው በስፋት እየተተኮሰ ያለው ከባድ መሣሪያ ጥንታዊ ቅርሶች ላይም ከፍተኛ የደህንነት ስጋት ፈጥሯል» ብለዋል። ያነጋገርናቸው ሌላ የላሊበላ ከተማ ነዋሪም ይህንኑ አረጋግጠዋል። ምንም እንኳን መንግሥት ውድቅ ቢያደርገውም በአማራ ክልል ለወራት በቀጠለው የትጥቅ ግጭት ምክንያት «ድሮንን ጨምሮ በከባድ መሣሪያዎች በተሰነዘሩ ጥቃቶች በሲቪል ሰዎች ላይ ሞት እና የአካል ጉዳት መድረሱን» የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሰሞኑን ማስታወቁ ይታወሳል።

ሰሎሞን ሙጬ 

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ