1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምጣኔ ኃብት ማሻሻያ በዋና ዋና የንግድ ማሳለጫ መስኮች ምን አስከተለ?

ሐሙስ፣ ነሐሴ 9 2016

ነጋዴዎች ከጉምሩክ ቀረጥ ባሻገር ምርቶችን ለማስመጣት የትራንስፖርት አገልግሎትን ይጠቀማሉ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ትኬት ዋጋ በብሔራዊ ባንክ ዕለታዊ የምንዛሪ ተመን እንደሚያስብ ማስታወቁን ተከትሎ የቲኬት ዋጋው የፖሊሲ መሸሻያው ከመደረጉ በፊት ከነበረው በእጥፍ ጨምሯል።

https://p.dw.com/p/4jVp0
Äthiopien Merkato
ምስል Solomon Much/DW

የምጣኔ ሃብቱ ያስከተለው የግብይት ማዕከላት የገበያ ሁኔታ

የዋና ዋና የንግድ ማሳለጫ መስኮች ቅኝት

መንግሥት የውጭ ምንዛሪ ግብይት በገበያው እንዲመራ መወሰኑን ተከትሎ የዋና ዋና የንግድ እና የግብይት ማሳለጫ አገልግሎቶች፣ ብዙ ብር ወጪ የሚደረግባቸው ግዢ እና ሽያጮች ዋጋ ምን ይመስላል ?

 

አስመጪዎች የጉምሩክ ቀረጥ እንደጨመረ እየገለፁ ነው

በጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ስም ተፈርሞ የወጣ ደብዳቤ ከሐምሌ 22 ቀን 2016 ጀምሮ የጉምሩክ ቀረጥ "በብሔራዊ ባንክ ዕለታዊ ተመን" እንዲሆን መደረጉን ይገልፃል። ይህ የውሳኔ ደብዳቤ መንግሥት የውጭ ምንዛሪ ግብይት ማሻሻያ ከማድረጉ በፊት በነበረው ተመን ከውጭ ምርቶችን አስጭነው ላስገቡ አስመጪዎች አስጨናቂ ሆኗል።

«የኤኮኖሚ ማሻሻያው» የብር አቅም መዳከም ለብዙኀኑ ሕዝብ ምን ማለት ይሆን?

"ቀረጥን በ 58 ብር ስንከፍል ነበር የመጣነው። [በመሃል] አዲስ ሕግ ወጣ። በ110 ብር እና በላይ እንድንከፍል ነው ያደረጉን። ይህ ማለት አንድ አስመጪ ወይም ደግሞ አንድ ነጋዴ ለቀረጥ 2 ሚሊየን መክፈል ካለበት እየከፈለ ያለው 4 ሚሊየን ብር ነው።"

የአዲስ አበባ ከተማ
በጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ስም ተፈርሞ የወጣ ደብዳቤ ከሐምሌ 22 ቀን 2016 ጀምሮ የጉምሩክ ቀረጥ "በብሔራዊ ባንክ ዕለታዊ ተመን" እንዲሆን መደረጉን ይገልፃል።ምስል Solomon Much/DW

 

ያስገባናቸው ዕቃዎች አንድም በነባሩ ተመን ታስበው ተሽጠዋል፣ በሌላ በኩል በአዲሱ ዕለታዊ ምንዛሪ ቀረጥ ተሠርቶ ሲያበቃ ሽያጭ ላይ ዋጋ አትጨምሩ መባሉም ግራ እንዳጋባቸውም እኒሁ አስመጪ ገልፀዋል።

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ያጸደቀው የኢትዮጵያ የተራዘመ የብድር አቅርቦት የፖሊሲ አላባዎች የሚሳኩ ናቸው?

 "የተሸጠን ዕቃ ድጋሚ ተደውሎ የከፈልከው ብር ይሄን ያህል ነው መጨመር አለብህ እየተባለ ነው እየተደወለ የነበረው።"

 

የትራንስፖርት ዋጋ ሁኔታ

ነጋዴዎች ከጉምሩክ ቀረጥ ባሻገር ምርቶችን ለማስመጣት የትራንስፖርት አገልግሎትን ይጠቀማሉ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ትኬት ዋጋ በብሔራዊ ባንክ ዕለታዊ የምንዛሪ ተመን እንደሚያስብ ማስታወቁን ተከትሎ የቲኬት ዋጋው የፖሊሲ መሸሻያው ከመደረጉ በፊት ከነበረው በእጥፍ ጨምሯል። ምልከታ ያደረግንባቸው የሌሎች ሀገሮች አየር መንገዶችም ይህንኑ ተግባራዊ ማድረግ የጀመሩት ውሳኔው ይፋ በሆነ ማግስት ነበር። ዛሬ በኢሚሬትስ አየር መንገድ የትኬት ቢሮ ባደረግነው ምልከታ አርባ ሺህ ብር አይፈጅ የነበረው የዱባይ የደርሶ መልስ ትኬትን እስከ 90 ሺህ ብር ከፍላ ትኬት ቆርጣ መውጣቷን አንድ ያነጋገርናት ሴት ገልጻለች። ሁኔታውንም "ከፍተኛ ልዩነት የተስተዋለበት" ብላዋለች።

መንግሥት ነዳጅ ላይ ድጎማ እንደሚያደርግ በማስታወቁ የከተማው የመደበኛም ይሁን የሜትር ታክሲ አገልግሌት ዋጋ ላይ እስካሁን የተስተዋለ የዋጋ ጭማሪ የለም። 

አዲስ አበባ ከተማ መርካቶ
መንግሥት ነዳጅ ላይ ድጎማ እንደሚያደርግ በማስታወቁ የከተማው የመደበኛም ይሁን የሜትር ታክሲ አገልግሌት ዋጋ ላይ እስካሁን የተስተዋለ የዋጋ ጭማሪ የለም።ምስል Solomon Much/DW

በኢትዮጵያ ያለው ግጭት፤ የኢኮኖሚ ማሻሻያው አተገባበር ስጋት

የሆቴል አገልግሎት፣ የቤት ኪራይና ሽያጭ ሁኔታ

 

በሌላ በኩል አገልግሎት የሚሰጡት ሆቴሎች ላይ በተወሰነ መጠን የዋጋ ጭማሪ ስለመኖሩ መመልከት ችለናል።

አንድም አትራፊ በመሆኑ፣ በሌላ በኩል ሀገሪቱ ውስጥ ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት የምርት ኢንዱስትሪዎችን እና ማምረቻ ድርጅቶችን ከመትከል ይልቅ፣ አዲስ አበባ ውስጥ የቤት ልማት በከፍተኛ ሁኔታ መሠረት እየያዘ መሆኑ ይታያል። ለመሆኑ በዚህ ወቅት የቤት ግብይት ምን ይመስላል? የሚለውን አንድ በማገበያየት ሥራ ላይ የተሰማራን ሰው ጠይቀናል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲው፤ ተስፋና ስጋቱ

"ካሽ ያለው ሰው ጠፋ። አሁን ቀንሷል [ሽያጭ]።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ምንም እንኳን የቤት ክራይ ውል እና አሠራር የራሱ መመርያ ቢወጣለትም ለንግድም ይሁን ለመኖሪያ የሚውሉ ቤቶች ኪራይ ከመጨመር ወደኋላ አላለም። በዚህ ላይ የውጭ ምንዛሪ ተመን ማሻሻያው የራሱን ተጽእኖ አሳርፏል።

መንግሥት በአገልግሎትም ይሁን በሸቀጦች ዋጋ ላይ ጭማሪ የሚያደርጉትን ድርጅቶችን ማሸግን እንደ መፍትሔ እየወሰደ ነው። የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ ትናንት "ያላግባብ ዋጋ የጨመሩ" ያሏቸው 4408 ተቋማት መታሸጋቸውን እና 31 ምርት የደበቁ ያላቸው የንግድ ተቋማት የታሽጉ መሆኑን አስታውቀዋል።

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ

ኂሩት መለሰ