1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«ዕገታ» ከመንግስት ቁጥጥር ውጭ ሆኖ ወይስ በቸልተኝነት እዚህ ደረሰ?

እሑድ፣ ሐምሌ 14 2016

አሁን አሁን ግጭት ጦርነት በሚደረግባቸውም ይሁን አንጻራዊ ሰላም ባለባቸው አካባቢዎች ለዜጎች የየዕለት ስጋት ሆኖ የቀጠለው እና ምናልባትም ችግሩ በዚህ ከቀጠለ በሀገር ህልውና ላይ የሚያስከትለው መዘዝ አሳሳቢ እየሆነ የመጣው የሰላማዊ ሰዎች ዕገታ ጉዳይ ነው ።

https://p.dw.com/p/4iYSe
Infografik GRAPHIC Karte Amuru Woreda, Äthiopien
ምስል DW

ኢትዮጵያ ውስጥ ተባብሶ የቀጠለው የእገታ መፍትሄ ያገኝ ይሆን?

ከአንዱ ግጭት ወደ ሌላው ፤ አንዱ ጦርነት ጋብ ሲል ሌላው እየቀጠለ ፖለቲካዊ ቀውስ የፈጠረው አለመረጋጋት የሰፈነባት ኢትዮጵያ ለዘርፈ ብዙ ችግሮቿ  ዘላቂ መፍትሄ ሳይገኝላት ቀጥላለች። በሀገሪቱ ፖለቲካው የወለደው ቀውስ አሁን አሁን ኤኮኖሚውን እና ማህበራዊውን ህይወት በእጅጉ እንደጎዳ ነው የሚነገረው ። ችግሮቹን ለመቅረፍ በሰለጠነ መንገድ በመነጋገር እና በውይይት ከመፍታት ይልቅ መንግስትን ጨምሮ ሁሉም ወገኖች  የጦር መሳሪያን እንደመፍትሔ መውሰዳቸው ሁለተንናዊውን ችግር ከድጡ ወደ ማጡ አድርጎታል።

የታጋች ተማሪ ቤተሰቦች ጭንቀት

አሁን አሁን ግጭት ጦርነት በሚደረግባቸውም ይሁን አንጻራዊ ሰላም ባለባቸው አካባቢዎች ለዜጎች የየዕለት ስጋት ሆኖ የቀጠለው እና ምናልባትም ችግሩ በዚህ ከቀጠለ በሀገር ህልውና ላይ የሚያስከትለው መዘዝ አሳሳቢ እየሆነ የመጣው የሰላማዊ ሰዎች ዕገታ ጉዳይ ነው ። በሀገሪቱ ለውጥ መጣ ከተባለ ማግስት ጀምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚፈጸሙ ዕገታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጠነን እና በስልት እየጨመሩ የዜጎችን የዕለት  ተዕለት እንቅስቃሴ በጉልህ ደረጃ አስተጓጉለዋል።

በቢሾፍቱ ከተማ በግድያ በዝርፊያና በእገታ የተሰማሩ ሁለት ሽፍቶች ተገደሉ

ነፍጥ ያነገቡ እና በተደራጀ መንገድ የሚንቀሳቀሱ አጋቾች ከግለሰቦች ጀምሮ በቡድን የሚንቀሳቀሱ ሰላማዊ ሰዎችን በማገት እና የማስለቀቂያ ቤዛ ከመቶ ሺዎች እስከ ሚሊዮኖች ሲጠየቅባቸው ይሰማል ። አቅም ያለው የታጋች ቤተሰብ ከአጋቾች ጋር ተደራድሮ እና የተጠየቀውን ከፍሎ ታጋቹን ሲያስለቅቅ አቅም የሌለው እስከ መለመን ደርሷል። በዚህ ሁሉ ያልተሳካላት ታጋች የመጨረሻ ዕጣ ፈንታው ሞት ሊሆን ይችላል። በዚህም በርካቶች ዘመድ አዝማዶቻቸው እንደወጡ ቀርተውባቸዋል። በሀገሪቱ ቀውስ እያስከተለ ያለው የዕገታ ተግባር ከመደበኛው ጦርነት ባልተናነሰ የሀገሪቱን ኤኮኖሚ እና ማህበራዊ መስተጋብር ጭምር ብርቱ አደጋ ላይ ጥሏል።

የማስለቀቂያ ገንዘብ ህይወቱን ያልታደገው ታጋች - በከሚሴ

ከታጋቾች ቤተሰቦች እንደሚሰማው ከሆነ አስገራሚው ነገር አጋቾች የሚጠይቁትን ቤዛ በመደበኛ የባንክ ስረዓት እንዲተላለፍላቸው ማድረጋቸው ነው። ሁኔታው በአንድ በኩል በየአካባቢው የሚፈጸመው የዕገታ ተግባር መንግስት በመደበኛ የህግ ማስከበርም ሆነ በወታደራዊ ዕርምጃ መግታት እንዴት ተሳነው የሚል ጥያቄ ሲያስነሳ በሌላ በኩል ደግሞ የባንክ ስረዓቱ በወንጀለኞች የሚከናወኑ የገንዘብ ዝውውሮችን መቆጣጠር እንዴት አልተቻለም? ያጠያይቃል። « በሀገሪቱ ቀውስ እያስከተለ ያለው የዕገታ ተግባር ከመንግስት ቁጥጥር ውጭ ሆኖ ወይስ በቸልተኝነት እዚህ ደረሰ ?» የሳምንቱ የውይይት ርዕሰ ጉዳይ የአራት እንግዶችን ውይይት አስተናግዷል። 

ታምራት ዲንሳ