አሸናፊ ያልተለየበት የፈረንሳዩ የምክር ቤት ምርጫ እና አንድምታዉ
ሰኞ፣ ሐምሌ 1 2016አሸናፊ ያለየበት የፈረንሳዩ የምክር ቤት ምርጫ
የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኤማኑኤል ማክሮ ከሦስት ሳምንት በፊት በተካሄደዉ በአውሮጳ ህብረት የምክር ቤት ምርጫ ፓርቲያቸዉ ከባድ ሽንፈት ከገጠመዉ ወዲህ ካቢኔያቸዉን በትነዉ ለዳግም የምክር ቤት ምርጫ፤ መጥራታቸዉ ይታወቃል። በፈረንሳይ ባለፈዉ ሳምንት እሁድ የተካሄደዉን የመጀመርያ ዙር ምርጫ ተከትሎ ትናንት እሁድ በተካሄደዉ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ምርጫ፤ ዉጤት አስደናቂ እና ያልተጠበቀ ተብሎለታል። ይፋ በተደረገዉ ዉጤት መሰረት፤ ፖፑላር ፍሮንት (NPF) የተሰኘዉ የግራ ዘመም ፓርቲዎች ጥምረት በአስደናቂ ሁኔታ አብላጫውን ድምፅ ማግኘቱ ተመልክቷል። በዚህም የግራ ዘመም ፓርቲዎች ጥምረት በምክር ቤት 171 ወንበሮችን ፤ የፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮ ማዕከላዊ ፓርቲ 152 ወንበሮችን እንዲሁም በመጀመርያ ዙር አብላጫ ድምፅን አግኝቶ የነበረዉ፤ ስደተኛ ጠል የሚባለዉየማሪን ለፐን ፓርቲ ናሽናል ራሊ ፓርቲ ደግሞ 134 ወንበሮችን በማግኘት ሦስተኛ ደረጃን መያዙ ታዉቋል። ይሁንና ሁሉም ፓርቲዎች መንግሥትን ለመመስረት በቂ መቀመጫን አላገኙም። በምርጫዉ ዉጤት መሰረት አብላጫ ወንበሮችን ያገኙ እና መንግሥት ለመመስረት በቂ ዉጤት ያላገኙት እነዚህ ፓርቲዎች በጥምረት ለመስራት ለድርድር እና ለስልጣን ክፍፍል ለመቀመጥ መስማማት እንዳለባቸዉ ተመልክቷል። የፈረንሳዩን የህግ መወሰኛ ምክር ቤት የሁለተኛ ዙር ምርጫ ዉጤትን በተመለከተ ፈረንሳይ ፓሪስ የምትገኘዉን ወኪላችን አነጋጋረናታል።
ሃይማኖት ጥሩነህ
አዜብ ታደሰ
ፀሃይ ጫኔ