1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ትምህርትአፍሪቃ

ንባብን ባህል ለማድረግ ያለመው የንባብ ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ተከፈተ

ቅዳሜ፣ ሰኔ 29 2016

በኢትዮጵያ እየዳሸቀ ነው የተባለውን የንባብ ልማድ ባህል ለማድረግ ያለመ የንባብ ፌስቲቫል ተሰኘ መርሃግብር አዲስ አበባ ውስጥ ተከፈተ፡፡ መሰል መርሃግብር ስካሄድ ዘንድሮ ለዘጠነኛ ጊዜ ነው የተባለለት መርሃግበሩ የማህበረሰብን የማንበብ ፍላጎት ለማነሳሳት ያለመ ነው ተብሎለታል፡፡

https://p.dw.com/p/4hvwX
Äthiopien Buchmesse
ምስል Seyoum Getu/DW

የንባብ ሳምንት በአዲስ አበባ ተከፈተ

በኢትዮጵያ እየዳሸቀ ነው የተባለውን የንባብ ልማድ ባህል ለማድረግ ያለመ የንባብ ፌስቲቫል ተሰኘ መርሃግብር አዲስ አበባ ውስጥ ተከፈተ፡፡

መሰል መርሃግብር ስካሄድ ዘንድሮ ለዘጠነኛ ጊዜ ነው የተባለለት መርሃግበሩ የማህበረሰብን የማንበብ ፍላጎት ለማነሳሳት ያለመ ነው ተብሎለታል፡፡

አሁን ላይ የተማሪዎች የትምህርት ጊዜ ተጠናቆ ወደ ወርሃ ክረምት እየተገባ በመሆኑ በዚህ ወቅት ተማሪዎች መጽሃፍትን በማንበብ በእውቀት እራሳቸውን እንዲያጎለብቱ ማስገንዘብም ሌላው የመርሃግሩ ዓላማ ነው ተብሏልም፡፡

Addis ABABA City education head
የአዲስ አበባው ትምህርት ቢሮ ኃላፊው ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ደግሞ የንባብ ባህል ማሸቆልቆልን መገንዘባቸውን ገልጸው፤ መፍትሄ ያሉትን ሃሳብ አስቀምጠዋል፡፡ምስል Seyoum Getu/DW

ከዛሬ ጀምሮ አዲስ አበባ ውስጥ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል የተከፈተው የንባብ ፌስቲቫል የተሰኘው መርሃ ግብር በይፋ ሲከፈት የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነጥበብ እና ቱሪዝም ባለስልጣናትን ጨምሮ ጸሃየንባብ ባሕላችንን እንዴት እናዳብር?ፊዎች እና የደራሲ ማህበራት ኃላፊዎች ታድመዋል፡፡ የንባብ ፌስቲቫሉም “ንባብ ለትውልድ ግንባታ” የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

የንባብ ባሕላችንን እንዴት እናዳብር?

ማንበብ ለትውልድ ግንባታ ያለው ሚና

በመርሃግብሩ የመክፈቻ ስነስርዓት ላይ ተገኝተው ንግግር ደረጉት የኢትዮጵያ ደራሲን ማህበር ፕሬዝዳንት አበረ አዳሙ በኢትዮጵያ ተምሳሌት ሚሆኑ በንባብ የተፈጠሩ ሰዎች ብኖሩም፤ አሁን አሁን የማንበብ ባህል እጅጉን ወድቆ ውጤቱም ታይቷል ብለዋል፡፡ “ሀዲስ ዓለማየሁ እና ተክለጻዲቅ መኩሪያ የ7ኛ ክፍል ተማሪ መሆናቸውን፣ አቤ ጉበኛው 12ኛ ክፍል አለማተናቀቃቸውና ጳውሎስ ኞኞም ብሆን የአራተኛ ክፍል ተማሪ ሆነው በንባብ እራሳቸውን በማብቃት ብቁ ሙያተኞች ሆነዋል፡፡ ያላነበበ ትውልድ ያመጣ ማዕበል ሁሉ ወዳሻው አቅጣጫ እንደሚመራው መልእቅ እንደሌላት መርከብ ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስርዓተ ትምህርታችን ከንባብ ጋር የተፋታ ይመስላል፡፡ ተማሪም ሆነ መምህሩ አያነቡም፡፡ በዚህም ምክንያት ተማሪው የተማረውን ተጠይቆ ግማሹን መመለስ እየተሳነው ነው፡፡ 900 ሺህ ተማሪዎች ፈተና ተፈትነው 29 ሺህ ብቻ የተጠየቀውን ግማሽ ያህል እና ከዚያ በላይ ስመልሱ መመልከት የስርዓተ ትምህርቱ ከንባብ መራቅን ያስረዳል” ብለዋል፡፡

የንባብ ሳምንት በአዲስ አበባ
በኢትዮጵያ እየዳሸቀ ነው የተባለውን የንባብ ልማድ ባህል ለማድረግ ያለመ የንባብ ፌስቲቫል ተሰኘ መርሃግብር ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ተከፈተ፡፡ምስል Seyoum Getu/DW

የማዳም ቤትዋ ገጣሚ - ከሳዉዲ አረብያ - ፎዝያ ጀማል

የንባብ ባህል ማሽቆልቆል አሳሳቢነት

የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ፕሬዝዳንቱ አቶ አበሬን የንባብ መቀዛቀዝ ለምንስ ያሳስባል የሚል ጥያቄም ከዶቼ ቬለ ቀርቦላቸው፤ “ከ900 ሺህ ተማሪዎች ግማሽና ከዚያ በላይ ትያቄ የመለሱ 29 ሺኅ ተማሪዎች ብቻ ናቸው መባሉ ስርዓተ ትምህርቱ ያመጣ ውርደት መሆኑ የሚያሳስበኝ ቀዳሚው ጉዳይ ነው” ብለዋል፡፡ ከዚያም ባሻገር ግን ላሉ ባለሙያው፡ በብሔር በሃይማኖት የምንጋጨው በእውቀት ማነስ ነው፡፡ ህም የሆነው በንባብ ባህል መመናመን ነው ብለው ሃሳባቸውን አከሉ፡፡ አንብቦ በእውቀት የታነጸ ትውልድ ግን እንደ አንድ ቆማል እንጂ በረባ-ባልረባ ስጋጭ አይውልም ብለው አስተያየታቸውን ሰጥተውናልም፡፡ ኢትዮጵያ ውስት አንዱ ተፈናቃይ ሌላው አፈናቃይ፤ አንዱ ተሳዳጅ ሌላው አሳዳጅ የሆነውም በእውቀት ማነስ ነው ብለው ተችተዋል፡፡ ንባብ የአእምሮ ደዌን ያድሳል ሉት የደራሲያን ማህበር ፕሬዝዳንቱ የእውቀት ማነሱ ወንድም ወንዱሙ ላይ ሴፍ እንዲመዝ ማድረጉንም በአስተያየታቸውን ጠቁመዋል፡፡

የንባብ ሳምንት በአዲስ አበባ
የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ፕሬዝዳንቱ አቶ አበሬን የንባብ መቀዛቀዝ ለምንስ ያሳስባል የሚል ጥያቄም ከዶቼ ቬለ ቀርቦላቸው፤ ምስል Seyoum Getu/DW

´´የከተማው መናኝ´´ ኤልያስ መልካ ሕይወት

የስርዓተ ትምህርት እና ማንበቢያ ስፍራዎች ትኩረት መሻት

በዛሬው መርሃግብር ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሂሩት ካሳው ግን በዚህ የተስማሙ አይመስልም፡፡ “አንባቢዎች የሉንም በሚል ሰፊ ክስ አልስማማም፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ ባሉ ቤተመጽሃፍት እንኳ ብንሄድ በአንባቢን ተሞልቶ እናገኛቸዋለን፡፡ ሆኖም ግን የላቀ አንባቢ ትውልድ እንዲኖረን ማንበቢ ቦታ እና የሚነበበውን ለማዘጋጀት በጋራ መስራትም ይገባል” ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ሥነ-ጽሑፎቻችን በዉጭ ቋንቋዎች ምን ያሕል ተተርጉመዋል?

የአዲስ አበባው ትምህርት ቢሮ ኃላፊው ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ደግሞ የንባብ ባህል ማሸቆልቆልን መገንዘባቸውን ገልጸው፤ መፍትሄ ያሉትን ሃሳብ አስቀምጠዋል፡፡ “የንባብ ባህላችን መድከም ለውጤት ሚና ብኖረውም ንባብ ያለስርዓተ ትምህርት ስርዓተ ትምህርትም ለንባብ መኖር ኤችሉም፡፡ እልባቱም ሁለቱን ማቆራኘት ነው” ብለዋል፡፡

የንባብ ሳምንት በአዲስ አበባ ተከፈተ
የስነጽሁፍ ባለሙያ እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቲያትር አርት መምህር አያልነህ ሙላቱ ደግሞ የንባብ ባህልን ለማዳበር መሰል መድረኮችን ማዘጋጀቱ ጠቃሚ ሆኖ ትልቁ ስራ ግን ቤተሰብ እና ትውልድ ላይ ብሰራ ባይ ናቸው፡፡ ምስል Seyoum Getu/DW

አንባቢ ትውልድን ለመፍጠጠር የቤተሰብና ት/ቤቶች ሚና

የስነጽሁፍ ባለሙያ እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቲያትር አርት መምህር አያልነህ ሙላቱ ደግሞ የንባብ ባህልን ለማዳበር መሰል መድረኮችን ማዘጋጀቱ ጠቃሚ ሆኖ ትልቁ ስራ ግን ቤተሰብ እና ትውልድ ላይ ብሰራ ባይ ናቸው፡፡ “የንባብ ባህል መሰረቱን መታል ለበት ህጻናት ላይ ነው፡፡

የኪነጥበብ ምሽቶች ፋይዳ

ለዚህ ደግሞ ቤተሰብ ላይ መስራትን ይጠይቃል፡፡ የኔን ታሪክ ብነግሪህ አባቴ ማንበብ የማይችሉ አርበኛ ስለነበሩ ሁል ጊዜ መጽሃፍ እንዳነብላቸው አድርገው እኔን ማሳደጋቸው ዛሬ እኔን ፈጥሮኛል፡፡ ትምህርት ቤቶችም ቀለም ከማስተማር በተጨማሪ ትውልዱ አንባቢ እንዲሆን መቅረፅ ይጠበቅባቸዋል” በማለት በኢትዮጵያ የተፈጠሩ አብዛኛ ደራሲያን በንባብ መፈጠራቸውን በማሳያነት አንስተዋል፡፡    

ሥዩም ጌቱ

ታምራት ዲንሳ

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር