1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ነቀምቴ የእንቅስቃሴ ዕገዳ እና የህዝቡ ምሬት

ሐሙስ፣ ጥር 30 2016

በኦሮሚያ ክልል ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን የገበያ እና የመጓጓዣ አድማ ከጠራ 10 ቀናት በኋላ የነቀምቴ ከተማ ነዋሪዎች ለተለያዩ ማኅበራዊ እና ኤኮኖሚያዊ ችግሮች መዳረጋቸውን ተናገሩ።

https://p.dw.com/p/4c8Ph
Ethiopia , Oromia regional state Nekemt city
ምስል Negasa Desalegn/DW

ነቀምቴ የእንቅስቃሴ ዕገዳ የነዋሪውን ምሬት አባብሷል

በኦሮሚያ ክልል ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን የገበያ እና የመጓጓዣ አድማ ከጠራ 10 ቀናት በኋላ የነቀምቴ ከተማ ነዋሪዎች ለተለያዩ ማኅበራዊ እና ኤኮኖሚያዊ ችግሮች መዳረጋቸውን ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። ነዋሪዎቹ እንዳሉት አድማው በክልሉ በአብዛኛው አካባቢ ቢያበቃም በነቀምቴ ከተማ ግን አሁንም ድረስ መቀጠሉ ለከፋ ችግር አጋልጧቸዋል።

ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁን አንድ የከተማዋ ነዋሪ በታጣቂዎች የተላለፈውን አድማ ተባብራችኋል በሚል በመንግሥት ባለሥልጣናት በተሽከርካሪ  እና በንግድ ተቋማት ባለቤቶች ላይ እየወሰዱ ያሉት  አስተዳደራዊ እርምጃዎች ችግሩ በከተማዋ  እንዲቀጥል ምክንያት ሆኗል። የተላለፈውን አድማ ተባብራችኋል በሚል በመንግሥት ባለሥልጣናት በተሽከርካሪ  እና በኦሮሚያ የቀጠለው የጸጥታ ስጋትበንግድ ተቋማት ባለቤቶች ላይ እየወሰዱ ያሉት  አስተዳደራዊ እርምጃዎች ችግሩ በከተማዋ  እንዲቀጥል ምክንያት ሆኗል።  በኦሮሚያ የቀጠለው የጸጥታ ስጋት


«ያው ነቀምቴ ከተማ ከባለፈው እሑድ ጀምሮ ለሳምንታት ተጽዕኖ እንፈጥራለን ጦርነት ይቁምልን በሚል ሁኔታ መንገድ እንዲዘጋ ተሽከርካሪዎችም እንዳይሄዱ እገዳ በራሳቸው ፈቃድ ፤ ነዋሪም እነርሱን አግዞ ለሳምንታት ያህል ዝግ ነበር ፤ ከዚያ በኋላ ግን መንግሥት እርምጃ እየወሰደ ነበር፤ እርምጃውም ደግሞ ሱቅ ማሸግ ፣ የተወሰኑ ተሽከርካሪዎች ከአሁን በኋላ እንዳይሄዱ ብሎ በሱቅ ላይ ለአንድ ሰው 50 ሺህ እንዲቀጣ ፣ ባጃጆች እና ታክሲ ላይም እንደዚሁ በየእንትናቸው ቅጣት ተሰጥቷል። ያን ቅጣት ደግሞ ሰው ለመወጣት ሥራ የለም ። በዚህ ላይ ደግሞ እንደም የወለጋ መንገድና የበኒ ሻንጉል ፀጥታታውቀው ነው። በዚያ ሁኔታ ሱቅም ታሽጎ ነው ያለው ። እንቅስቃሴ ምንም የለም። እንዳለ ጨልሞብን ነው ያለው ። »
ሌላው ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የነቀምቴ ከተማ ነዋሪ እንደሚሉት በከተማዋም ሆነ ከከተማዋ ውጪ ያለው ሁኔታ በነጻነት መንቀሳቀስ የሚያስችል አይደለም። 
ሁኔታዎች ያልገደቧት «ሰቃይዋ» ተማሪ እና ህልሟ

«ምን ይጠየቃል፤ ምን አንተ ወጣ ብለህ  ሁሉ ነገር በስጋት ነው ፤ ነጻ ሆነህ የምትንቀሳቀስበት ሁኔታ የለም። ገበሬው ማምሁኔታዎች ያልገደቧት «ሰቃይዋ» ተማሪ እና ህልሁኔታዎች ያልገደቧት «ሰቃይዋ» ተማሪ እና ህልሟሟረት አልቻለም፤ ያመረተውንም ወደ ገበያ ማውጣት አልቻለም።»


አስተያየት ሰጭው እንደሚሉት ነዋሪው በየአካባቢው ለደህንነቱ በመፍራት በታጣቂው ኃይል በሚተላለፉ ትዕዛዞችን ተግባራዊ ማድረጉ ለመንግሥት ባለሥልጣናት አስተዳደራዊ እርምጃ አጋልጦታል ። ችግሩ ከነቀምቴ ከተማ ውጭ በሌሎች የኦሮሚያ ከተሞችም መከሰቱን ተረድተዋል። 
« አሁን መንገድ ዝጉ ፣መኪና እንዳይንቀሳቀስ ተብሎ ተዘጋ አይደል ? ህዝቡ ፈርቶ ትራንስፖርት በያለበት ቆመ ። ለምሳሌ ዝዋይ አካባቢ ከተማ ውስጥ ተኮልኩሎ ቆመ የሀገር አቋራጭ መኪና ከዚያ የመንግሥት አካል ደግሞ መጥቶ ለምን ቆማችሁ ፤ ተነሱ ውጡ ፣ ከወጡ እዚያጋ ይቃጠልባቸዋል፣ እዚህጋ ለምን ትቆማለህ ይባላል። መኪና መንቀሳቀስ ሲጀምር ደግሞ እስካሁን ለቆማችሁበት ክፈሉ ይባላሉ።  »
በነቀምቴ ከተማ የእንቅስቃሴው መታቀብ እና የመንግሥት ባለሥልጣናት ጎን ለጎን እየወሰዱ ያሉት አስተዳደራዊ እርምጃ እዝቡን ለከፋ ምሬት እየዳረገ እንደሚገኝ የሚገልጹት አስተያየት ሰጪዎች ፤ በዚህ ሂደት የመንግሥት የማኅበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ጭምር ተጎጂዎች እንደሆኑ ያመለክታሉ። 
« በጣም ችግር ላይ ነው ያለነው እና እንቅስቃሴ የለም በሆቴሎቹም ፤ እንቅስቃሴ በመታቀቡ ሰው በእግሩ ለመሄድ ተገዷል፤ ለምሳሌ ልንገርዎት እና ከወለጋ ዩኒቨርሲቲ ሰው ሪፈራል ሆስፒታል በእግሩ ነው እየሄደ ያለው በትንሹ ወደ ስድስት ኪሎ ሜትር ይሆናል ማለት ነው። »ሜትር ይሆናል ማለት ነው። »

 ለምዕራብ ኦሮምያው ግጭት የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የሰላም ጥሪ


በነቀምቴ ከተማ የተፈጠረው የእንቅስቃሴ ገደብ እና እርሱን ተከትሎ በሚሰዱ እርምጃዎች ነዋሪው ለስነ ልቦና ቀውስ ጭምር እየተዳረገ መሆኑን የሚገልጹት አስተያየት ሰጪው ችግሩ ከነዋሪው አቅም በላይ መሆኑን ያስረዳሉ ። 
« ሰው በስነ ልቦና ራሱ ጭንቀት ውስጥ ገብቷል። በዛ ሁሉ ነገር ፤ እንቅስቃሴ ከሌለ ፣ ሰው ወጥቶ ሸምቶ መብላት ካልቻለ ምንድነው ፤ አንደኛው አካል እንዲህ አታርጉ ይላል ፤ አንደኛው አካል ደግሞ ለምን እንደዚህ አደረጋችሁ ይላል ። መሃል ላይ ህዝቡ በጣም ተቸገረ በቃ ።»
በነቀምቴ ከተማም ሆነ በኦሮሚያ ክልል በአጠቃላይ የእንቅስቃሴውን ዕቀባ ተከትሎ በህዝቡ ላይ እየደረሱ ስላሉ ማኅበራዊ እና ኤኮኖሚያዊ ችግሮች መፍትሄ ለመጠየቅ ለነቀምቴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ  እና ለኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ስልክ  ብንደውልም ስልኮች ባለመነሳታቸው ሊሳካልን አልቻለም ። 
 የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ከአራት ቀናት በፊት በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ « አሸባሪው የሸኔ ቡድን የሽብር ተግባሩን አጠናክሮ በመቀጠል የክልሉን ሰላም እና መረጋጋት ለማናጋት የመጓጓዣ እና የገበያ ዕቀባ ቢጠራም በመንግሥት እና በህዝብ ተሳትፎ ከሽፏል » ብሎ ነበር። 
ነገር ግን የነቀምቴ ከተማን ጨምሮ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የየብስ የመጓጓዛ አገልግሎቶች ከታጣቂዎች የሚሰነዘር ጥቃትን ሽሽት መስተጓጎላቸውን ከየአካባቢው ያገኘናቸው መረጃዎች ያመለክታሉ።
ታምራት ዲንሳ
ሸዋዬ ለገሠ