1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ሕግ እና ፍትሕዓለም አቀፍ

ትራምፕ የምርጫ ውጤትን ለመቀልበስ በመጣር ተከሰሱ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 27 2015

የዜጎች የዳኝነት ጉባኤ ትራምፕን ጥፋተኛ ያለባቸው የክስ ጭብጦች አሜሪካንን ለማጭበርበር በማሴር፣የዜጎችን የመምረጥ መብት ለመንሳት በማሴርና ሕጋዊ የም/ቤት ስርዓትን ለመገልበጥ በማሴርና በመሞከር የሚሉ ናቸው።ክሱን ይፋ ያደረጉት ልዩ አቃቢ ህግ ጃክ ስሚዝ በም/ቤቱ ላይ የተቃጣውን ጥቃት በሃገሪቷ ሕግና ስርዓት ላይ የተቃጣ ጥቃት ብለውታል።

https://p.dw.com/p/4UgP7
USA Greensboro | Donald Trump bei der North Carolina Republican Party convention
ምስል Allison Joyce/AFP/Getty Images

የቀድሞው የዩናያትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጎርጎሮሳዊው 2022 የምርጫ ውጤትን ለመቀልበስ በመጣርና በአሜሪካ ም/ቤቶች ላይ የደረሰውን ጥቃት በማስተባበር ክስ ተመስርቶባቸዋል። በልዩ አቃቢ ህጉ ጃክ ስሚዝ መሪነት በዋሽንግተን ዲሲ የተሰየመው የዜጎች የዳኝነት ጉባኤ ዶናልድ ትራምፕን ያስከስሳቸዋል ያለው በአራት ወንጀሎች ነው።ጠበቃቸው በበኩላቸው ክሱ የዶናልድ ትራምፕን የመናገርና ሃሳብን የመግለጽ መብት እንደወንጀል የቆጠረ መሰረተ ቢስ ክስ ነው ብሎ አጣጥሎታል። ዝርዝሩን አበበ ፈለቀ ከዋሽንግተን ዲሲ ልኮልናል።
የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጎርጎሮሳዊው 2022 የምርጫ ውጤትን ለመቀልበስ በመጣርና በአሜሪካ ም/ቤቶች ላይ የደረሰውን ጥቃት በማስተባበር ክስ ተመስርቶባቸዋል። በልዩ አቃቢ ሕጉ ጃክ ስሚዝ መሪነት በዲሲ የተሰየመው የዜጎች የዳኝነት ጉባኤ ዶናልድ ትራምፕን ጥፋተኛ ያለው በአራት የወንጀል ክሶች ነው። ጠበቃቸው በበኩላቸው ክሱ የዶናልድ ትራምፕን የመናገርና ሃሳብን የመግለጽ መብት እንደወንጀል የቆጠረ መሰረተ ቢስ ክስ ነው ብሎ አጣጥሎታል። የዶናልድ ትራምፕ ክስ
የዶናልድ ትራምፕን ክስ እንዲከታተሉ የተሾሙት ልዩ አቃቢ ሕግ  ጃክ ስሚዝ፤ ዶናልድ ትራምፕ ከስድስት ስማቸው ክሱ ላይ ካልተጠቀሰ ግብረአበሮቻቸው ጋ ሆነው ምርጫ መሸነፋቸውን አልቀበልም ብለው፣ በስልጣን ላይ ለመቆየት ሲያሴሩ፣ ተጸዕኖ ሲፈጥሩ፣ ሕግ ሲጥሱ መቆየታቸውን ገልጸው፤ በመጨረሻም በታህሳስ 28 ቀን 2013 ዓ/ም በአሜሪካ ተወካዮች ም/ቤት ላይ የደረሰው ጥቃት ምክንያት መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ዲሲ ውስጥ የተሰየመው የዜጎች የዳኝነት ጉባኤ ዶናልድ ትራምፕን ጥፋተኛ ያለው በአራት የክስ ጭብጦች ነው። የክሱ ጭብጡ ዶናልድ ትራምፕን፤ አሜሪካንን ለማጭበርበር በማሴር፣ የዜጎችን የመምረጥ መብት ለመንሳት በማሴር፣ እንዲሁም ሕጋዊ የም/ቤት ስርዓትን ለመገልበጥ በማሴርና በመሞከር ይከሳል። ክሱን ይፋ ያደረጉት ልዩ አቃቢ ህግ ጃክ ስሚዝ በተወካዮች ም/ቤት ላይ የተቃጣው ጥቃት በሃገሪቷ ሕግና ስርዓት ላይ የተቃጣ ጥቃት ነው ብለውታል።ከትራምፕ የፍርድ ሂደት ምን ይጠበቃል?
ልዩ አቃቢ ሕጉ ለዚሁ ክስ ፈጣን የችሎት ስርዓትን እንደሚጠብቁ ገልጸዋል። የዶናልድ ትራምፕ ጠበቃ ጆን ላውሮ በበኩላቸው ክሱ በመናገር ነጻነት ላይ ያነጣጠረ፣ ፖለቲካዊ ጫና እንጂ አንዳችም መሰረት የለውም ይላሉ። ዶናልድ ትራምፕ ምርጫው መጭበርበሩንና እሳቸውም አለመሸነፋቸውን ስላመኑ፣ ያመኑበትን ካመናገር ያለፈ ምንም አላጠፉም ባይ ናቸው። ያም ሆኖ የህግ ባለሞያዎች ጥፋቱ መናገራቸው ሳይሆን፣ እምነታቸውን ተከትለው የምርጫውን ውጤት ለመገልበጥ ህገወጥ መንገዶችን መከተላቸው ነው ይላሉ። የትራምፕ «ቅሌት»
ይሄው ሶስተኛውና ከሁሉም ከባድ እንደሆነ የሚነገርለት ክስ ዶናልድ ትራምፕን ከሚወዷቸው ደጋፊዎቻቸው አላራቃቸውም። የፖለቲካ ተቀናቃኞቻቸውና ሌሎች የሪፐብሊካን ፖለቲከኞችም ሰለሳቸው ክፉ አለመምናገርን መርጠውል። የም/ቤቱ ጥቃት ኢላማ፣ የዶናልድ ትራምፕ ጫና ሰለባ የነበሩት ማይክ ፔንስ ግን ጠንከር ያለ መግለጫ አውጥተዋል። ማይክ ፔንስ ራሱን ከሃገሪቷ ሕገ መንግስት በላይ አድርጎ የሚያስብ ሰው መቼም ቢሆን ፕሬዝዳንት መሆን እንደሌለበት ይሄው ክስ ምስክር ነው ብለዋል። ዶናልድ ትራምፕ የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡ ሐሙስ በዋሽንግተን ዲሲ ፍ/ቤት እንዲቀርቡ ታዘዋል። 
አበበ ፈለቀ 
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ
 

Visual Story 1. Jahrestag der Erstürmung des Kapitols
ምስል Leah Millis/REUTERS
USA Staatsanwalt Jack Smith
ምስል Jacquelyn Martin/AP Photo/picture alliance