1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዶናልድ ትራምፕ ክስ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 6 2015

ትራምፕ የተከሰሱት በዘመነ ሥልጣናቸዉ ከእጃቸዉ የገባ ብርቱ የመንግስት ሚስጥርን የያዙ በርካታ ሰነዶች አከማችተዋል በሚል ነዉ

https://p.dw.com/p/4SX3b
USA, Miami | vor dem Trump Prozess
ምስል Win McNamee/Getty Images

«ክሱ ለዩናይትድ ስቴትስ ታሪካዊ» ተብሏል

የቀድሞዉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በተከሰሱበት 37 የወንጀል ጭብጥ እምነት ክሕደታቸዉን ለመስጠት ዛሬ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ።ትራምፕ የተከሰሱት በዘመነ ሥልጣናቸዉ ከእጃቸዉ የገባ ብርቱ የመንግስት ሚስጥርን የያዙ በርካታ ሰነዶች አከማችተዋል በሚል ነዉ።ትራምፕና ደጋፊዎቻቸዉ ክሱን በተደጋጋሚ ነቅፈዉታል።የዋሽግተኑን ወኪላችንን አበበ ፈለቀን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።በነገራችን ላይ በዩናይትድ ስቴትስ ሕግ መሰረት አንድ ሰዉ በወንጀል ተፍርዶበት ምርጫ የሚደረግ ቀን እስካልታሰረ ወይም ከእስር ቤት እስከተፈታ ድረስ በምርጫ ከመወዳደር አይታገድም።

አበበ ፈለቀ

ነጋሽ መሐመድ

ታምራት ዲንሳ