1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጋምቤላ የሚገኙ ተፈናቆዮች ተማፅኖ

ረቡዕ፣ ኅዳር 16 2013

ከኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ሙጊና አንፊሎ ከተባሉ ቀበሌዎች ተፈናቀለዉ ጋምቤላ ከተማ የተጠለሉ  ሰዎች መንግስት ርዳታ እንዲያደርግላቸዉ ተማፀኑ።በአብዛኛዉ የአማራ ብሔር አባላት እንደሆኑ የሚናገሩት ተፈናቃዮች እንደሚሉት ከመኖሪያ አካባቢያቸዉ የሸሹት የኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች ጉዳት ያደርሱብናል በሚል ስጋት ነዉ።

https://p.dw.com/p/3lpFp
Äthiopien | Stadt Gambella
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

ጋምቤላ የሚገኙ ተፈናቆዮች ተማፅኖ

ከኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ሙጊና አንፊሎ ከተባሉ ቀበሌዎች ተፈናቀለዉ ጋምቤላ ከተማ የተጠለሉ  ሰዎች መንግስት ርዳታ እንዲያደርግላቸዉ ተማፀኑ።በአብዛኛዉ የአማራ ብሔር አባላት እንደሆኑ የሚናገሩት ተፈናቃዮች እንደሚሉት ከመኖሪያ አካባቢያቸዉ የሸሹት የኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች ጉዳት ያደርሱብናል በሚል ስጋት ነዉ።ከ300  የሚበልጡት ተፈናቃዮች ካለፈዉ ጥቅምት ማብቂያ ጀምሮ ጋምቤላ አንድ ትምሕርት ቤት ዉስጥ እንደሰፈሩ ነዉ።ተፈናቃዮቹ እስካሁን ድረስ ከጋምቤላ ሕዝብ ዉጪ ከመንግስት ርዳታ አለማግኘታቸዉን አስታዉቀዋል።አንድ የጋምቤላ  ክልል የአደጋ መከላከያ ባልደረባ ግን የተፈናቃዮቹን ስሞታ «ሐሰት» ይላሉ።

ዓለምነዉ መኮንን

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ