1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ምርት

ረቡዕ፣ ሰኔ 3 2012

የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ የሚጠቅሙ የንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘሮችን ለማዘጋጀት የሚያግዝ 11 ሚሊዩን ሊትር ኢታኖል  እና 1.1ሚሊዩን  ኩንታል  ስኳርም በዘንድሮ ዓመት ማምረቱን የፋብሪካው ዋና ስራ አስኪጅ አቶ ደረጀ ጉርሜሳ ተናግረዋል

https://p.dw.com/p/3daEs
Äthiopien Ficha Zuckerfabrik
ምስል DW/N. Dessalegn

የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ

ሆሮ-ጉድሩ ወለጋ ዞን የሚገኘዉ የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ባለፉት ስድት ዓመታት ካመረታቸዉ ሁሉ የበለጠ ስኳር እና ኤታኖል ማምረቱን የፋብሪካዉ ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ።ሥራ አስኪያጅ ደረጀ ጉርሜሳ እንደሚሉት ፋብሪካዉ ዘንድሮ በተለይ የኮሮና ተሕዋሲን ለመከላከል የሚረዳ ንፅሕና መጠበቂያ ሳኒታይዘር ለማዘጋጀት የሚረዳ 11 ሚሊዮን ሊትር ኢታኖል አምርቷል።ኢትዮጵያ የፊንጫን ጨምሮ አስር የስኳር ፋብሪካዎች ቢኖርዋትም የስኳር ተጠቃሚዉን ሕዝብ ፍላጎት የሚረካ ስኳር ማምረት ግን አልቻሉም።የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ የሚጠቅሙ የንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘሮችን ለማዘጋጀት የሚያግዝ 11 ሚሊዩን ሊትር ኢታኖል  እና 1.1ሚሊዩን  ኩንታል  ስኳርም በዘንድሮ ዓመት ማምረቱን የፋብሪካው ዋና ስራ አስኪጅ አቶ ደረጀ ጉርሜሳ ተናግረዋል፡፡  በኢትዩጵያ ስኳር ኮርፖሬሽስር ከሚገኙት አስር የስኳር ፋብሪካዎች መካከከል የፊንጫ ስኳር ፍብሪካ ለሳኒታዘይር  የሚገለግል የኢታኒል ምርት በማምረት በመጀመሪያ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የኮርፖሬሽኑ  የሰራተኞች ማህበር ሊቀ መንበር አቶ ጋድሳ ደሳለኝም ገልጸዋል፡፡ በሀገር ዓቀፍ ደረጃ በዘንድሮ ዓመት ከተመረቱዉ 2.8 ሚሊዩን ኩንታል ስኳር መካከል 1.1 ሚሊዩን ኩንታል ከዚው ፋብሪካ መሆኑም ተገልጸዋል፡፡ለስኳር ምርቱ የሚሆን ግብዓት በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አምስት ወረዳዎች ውስጥ 20ሺ ሄክታር የሚሸፍን የአገዳ ምርት እንዳለም ጠቁመዋል፡፡ 
በሆሮ ጉደሩ ወለጋ ዞን አባይ ጮንመን በተባለ ወረዳ ውስጥ የሚገኘው የፊጫ ስኳር ፋብርካ ስራ ከጀመረ ሁለት አስርት ዓመታትን ማስቆጠቱን ከስኳር ኮርፖሬሽን የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡ በዘንድሮ ዓመት ከአንድ ሚሊዩን በላይ ኩንታል ስኳር ማምረቱን የፍብሪካው ስራ አስኪጅ አቶ ደረጀ ጉርሜሳ ተናረዋል፡፡ 
ከዚህ በፊት ኢታኖል ለመኪና፣ ለፍብርካዎች ግብዓትነት ብቻ ሲውል እንደነበር የተናገሩት አቶ ደረጀ በአሁኑ ጊዜ ደግሞ ለንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይሮች ግብአትነት በዋናነት እያዋለ እንደሚገኝ ጠቀሙዋል።የስኳር ምርቱ ጨምረዋል ቢባልም በተለያዩ ስፍራዎች  የስኳር እጥረት እየተስተዋለ ይገኛል፡፡ ለዚህም እጥረት ሌሎች ፋብሪካዎች በታቀደላቸው ጊዜ መሰረት ስራ ባለመጀራቸው ምክንያት እንደሆነ አቶ ደረጀ ገልጸዋል፡፡ 
የኢትዩጵያ ስኳር ኮረፖሬሽን መሰረታዊ የሰራተኞች ማህበር ሊቀመንበር አቶ ጋድሳ ደሳለኝ በበኩላቸው በኮርፖሬሽኑ ስር ከሚገኙት የስኳር ፋብርካዎች መካከከል እስካሁን ኢታኖል የሚመረተው በመተሀራ እና ፍንጫ ስኳር ፍብሪካዎች ብቻ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ አስካሁን ከተመረተው 60 በመቶው የኢታኖል ምርት የተገኘውም ከፍጫ ስኳር ፍብሪካ ነው ብለዋል፡፡ፍብሪካው 13 ሺ ሰራተኞች ያሉት ሲሆን  በዘንድሮ ዓመት ደግሞ ከ600 በላይ ሰዎች የስራ ዕድል ማግኘታቸው ተገልጸዋል፡፡

Äthiopien Ficha Zuckerfabrik
ምስል DW/N. Dessalegn

ነጋሳ ደሳለኝ 

ነጋሽ መሐመድ 

አዜብ ታደሰ