1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን መንግስት ለሳዑዲ አረቢያ ጦር መሳሪያ እንዲሸጥ መወሰኑ

ሐሙስ፣ ጥር 2 2016

ያኔ ጦር መሳሪያ እንዳይሸጥ የጀርመን መንግስት የወሰነዉ የሳዑዲ አረቢያ ነገስታት እዉቁን ሳዑዲ አረቢያዊ ጋዜጠኛ ጀማል ኻሾጂን አስገድለዋል በሚል ጥርጣሬና የሰብአዊ መብት ይረግጣሉ፣ በየመኑ ጦርነት ሰላማዊ ሰዎችን አስገድለዋል በሚል ምክንያት ነበር

https://p.dw.com/p/4b8gk
የጀርመን መንግስት 150 ኢሪስ ቲ ሚሳዬሎች ለሳዑዲ አረቢያ እንዲሸጥ ወስኗል
ኢሪስ ቲ ኤስ ኤል ኤም የተባለዉ ጀርመን ሠራሽ የዓየር ለአየር ተምዘግዛጊ ሚሳዬልምስል Diehl Defence

ጀርመን ዳግም ለሳዑዲ አረቢያ ጦር መሳሪያ ለመሸጥ መወሰኗ እያነጋገረ ነዉ

 

ጀርመን ዳግም ለሳዑዲ አረቢያ ጦር መሳሪያ እንድትሸጥ የሐገሪቱ መንግስት መወሰኑ ትናንት በይፋ ተነግሯል።የጀርመን የጦር መሳሪያዎች ለሳዑዲ አረቢያ እንዳትሸጡ የሐገሪቱ መንግስት ከ5 ዓመት በፊት ወስኖ ነበር።ያኔ ጦር መሳሪያ እንዳይሸጥ የጀርመን መንግስት የወሰነዉ የሳዑዲ አረቢያ ነገስታት እዉቁን ሳዑዲ አረቢያዊ ጋዜጠኛ ጀማል ኻሾጂን አስገድለዋል በሚል ጥርጣሬና የሰብአዊ መብት ይረግጣሉ፣ በየመኑ ጦርነት ሰላማዊ ሰዎችን አስገድለዋል በሚል ምክንያት ነበር።አሁን በሥልጣን ላይ ያለዉ የጀርመን ተጣማሪ መንግስት  150 ኢሪስ ቲ የተባሉ የዓየር-ላየር ተመዝግዛጊ ሚሳዬሎችና 48 ተዋጊ ጄቶች ለሳዑዲ አረቢያ እንዲሸጥ ወስኗል።ያለፈዉ ዉሳኔ የተሻረበት ምክንያት እያነጋገረ ነዉ።

ይልማ ኃይለሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ